Which one you first choose? በቅድሚያ የሚፈልጉት

Tuesday, May 8, 2018

ደቡብ ጎንደር ታች ጋይንት ሰጎዳ ማርያም እና ቤተልሔም ማርያም"



Image may contain: plant and outdoor
"ሰጎዳ ማርያም እና ቤተልሔም ማርያም"

Share በማድረግ ታሪካችንን እናሳውቅ!!
------------------------------------------
መገኘዋ ደቡብ ጎንደር ታች ጋይንት ወረዳ አርብ ገበያ በቅርብ ርቀት እንዥጥ ቀበሌ።ሰጎዳ ማርያም የተተከለችው በንጉሥ እለዓሜዳ ዘመነ መንግሥት(471-479) አቡነ ሙሴ(አባ ሚናስ 1ኛ) የተባሉ ከግብጽ የመጡ ቅዱስ አባት ነው።
አባ ሚናስ 1ኛ ግብጻዊ ሲሆኑ የኢትዮጵያ ከአቡነ ከሳቴ ብርሃን በመቀጠል ሁለተኛው ፓትርያርክ ናቸው።


አንዳዶች በአብርሃ ወአፅብሐ ዘመነ መንግስት (298- 324) ዓ/ም በ330 ዓ.ም እንደተመሰረተች ይገልጻሉ።ነገርግን አባ ሚናስ(አቡነ ሙሴ) የመጡት በአብርሃ ወአፅብሐ ጊዜ አይደለም።በዛ ጊዜ አቡነ ፍሬምናጦስ(አቡነ ከሳቴ ብርሃን) ነው የነበሩት።አቡነ ሙሴ ሁለተኛው ፓትርያርክ ናቸው።በሳቸው ጊዜ ደግሞ ንጉሥ እለዓሜዳ (471-479 አ.ም) የነገሱ ናቸው።ያም ሆነ ይሄ ሰጎዳ ማርያም እንደሌሎች ሁሌም ሁሉ በዛ ዘመን የተተከሉ ገዳማት እነ መርጡለማርያ፣ደብረወርቅ ማርያም እና የዘጠኙ ቅዱሳን ገዳማት በኢትዮጵያ ውስጥ ከሚገኙ አንገፋ ገዳማት ቀዳሚውን ስፍራ ይይዛሉ።

ሰጎዳ ማርያምን ከጥንታዊነቷ ባሻገር ምድር ውስጥ ከሚገኝ የተነጠፈ አለት ላይ ተፈልፍላ የተገነባች እፅብ ድንቅ ገዳም ናት።ውስጧ በማህሌትና በመቅደስ የተከፋፈለ ነው።ከማህሌቱ ጣራ ላይ የተጠረበ ከበሮ አለ።
ንግሷ ህዳር 21 ቀን ነው።

ሁለተኘዋ ቤተልሔም ማርያም ናት

አንዳዶች የድጓ ዩንቨርስቲ ሲሉ ይጠሯታል።
መገኘው በደቡብ ጎንደር ዞን ታችጋይንት ወረዳ ከአርብ ገበያ ከተማ በስተ ምዕራብ አቅጣጫ በ31 ኪ.ሜ ረቀት ላይ ነው ፡፡
ቤተልሔም ተክለሃይማኖት/ የግራኝ እመቤት /በአብርሃ ወአጽብሐ ዘመነ መንግስት(298-324) በ306 ዓ.ም በአጼ ዳዊት ልጅ ንግስት ድል ሞገሷ አማካኝነት እንደ ታነጸች ታሪክ ይናገራል፡፡ የአሰራር ጥበቡ ዛሬ ላይ ዝርያው በአካባቢው ከምድር ገጽ በጠፋው “ዞጲ” በተባለ የእንጨት ዝርያ እንደተሰራ ይነገራል፡፡ የቤተክርስቲያኑ አጥር በጨው ድንጋይ የተሰራ ነበር፡፡
ቤተ ልሔም የድጓ ማስመስከሪያዋ ናት።አያሌ የድጓ ሊቃውንቶችን አስመርቃለች። በአጼ ሠርጸድንግ ጊዜ ብቸኘዋ የድጓ ማስመስከሪያ ነበረች።

በግራኝ አህመድ የዘንዶ አይን ውስጥ ገብታም ነበር።አህመድ ግራኝ ቦታው ድረስ ተጉዞ ሊያቃጥላት ሞክረ።አልቻለም።እንደገና በንዴት ድንገይ አንስቶ ወርውሮ ሊመታ ሞከረ አሁንም ከሸፈበት።ቤተልሔም ማርያ በዚህ ተአምረኛ ጥበቧ "የግራኝ እመቤት" የሚል የማዕረግ ሥም ተሰጣት።ብዙ ነገሥታቶችም ስጦታ አበርክተዋል።በውስጧ የድጓ ድርሳናት ይገኛሉ።መንበሯ ሳይቀር በድንጋይ የተሰራ ተአምረኛ ገዳማ ናት።ንግሷ ጥር 24 ቀን ነው።

በዚሁ ወረዳ እንደ ደቃ ቂርቆስ እና ልዳ ጊዮርጊስ ያሉ ቀደመት ገዳማትም ይገኛሉ።

ታደለ ጥበቡ
Image may contain: sky and outdoor

No comments:

Post a Comment

wanted officials