Which one you first choose? በቅድሚያ የሚፈልጉት

Tuesday, May 22, 2018

ሐሰተኛው ነቢይ እስራኤል ዳንሳ የብዙ ሰዎችን ገንዘብ ያጭበረበርበት ሰነድ ይፋ ሆነ*

ሐሰተኛው ነቢይ እስራኤል ዳንሳ የብዙ ሰዎችን ገንዘብ ያጭበረበርበት ሰነድ ይፋ ሆነ**
**የኢትዮጵያ መንግስት እስራኤል ዳንሳን ካላሰረ ታምራት ገለታን ይፍታው ሁለቱም የሕግ የበላይነትን የሚቃረን ማጭበርበር የፈጸሙ ወንጀለኞች ናቸው ።***
መ/ር ታሪኩ አበራ
ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ራሱን ነቢይ ነኝ ብሎ ሕዝብ ሲያጭበረብር የነበረውና ሐሰተኛነቱ ሲታወቅበት ደግሞ ሐዋርያ ነኝ በማለት በቅሰጣ ሥራ ላይ የተሰማራው እስራኤል ዳንሳ ቀድሞ ይሰራበት ከነበረው ወላይታ ሶዶ ባንክ ቤት በተለያየ ጊዜ ሲፈጽም በነበረው የስርቆትና የማጭበርበር ወንጀል ከመስሪያ ቤቱ በከፍተኛ ውርደት የተባረረበት ሰነድ ከተደበቀበት ይፋ ሆኗል።
ይህ ግለሰብ ከፍተኛ በሆነ ፍቅረ ንዋይ ኅሊናው የደነዘዘበት ሰው ሲሆን ሰይጣን በገንዘብ ፍቅር የማረከውን ልቡን ለማርካት የተለያዩ ዘዴዎችን ሲጠቀም የኖረና በቅርብ ጊዜ ደግሞ ከጠንቋዮች ባገኘው መተትና ድግምት በመታገዝ ብዙዎችን በእምነት ስም እያታለለ የጽድቅና የድኅነት መንገድ የሆነውን ወንጌልን በሐሰት በመሸቃቀጥ በአቋራጭ ለመክበር ሕዝብን በማተለል ላይ የተሰማራ ወንጀለኛ ነው።
የወንጌላውያን ኅብረት ጽ/ቤት በተደጋጋሚ እንዳሳወቀው ግለሰቡ በተለያዩ ጊዜያት የማጭበርበር ወንጀል ሲፈጽም ተገኝቶ ጥፋተኛነቱ በሰውና በሰነድ ማስረጃ የተረጋገጠበት በመሆኑ ሕብረቱ በይፋ ሐሰተኛ ነቢይነቱን ለሕዝብ አሳውቋል ።
የኢትዮጵያ መንግስት እንዲህ ዓይነቱን ለሀገርና ለወገን ጠንቅ የሆነን ወንጀለኛን በሕግ ጥላ ሥር በማዋል በሀገሪቱ የወንጀለኛ መቅጫ ሕግ መሰረት አስፈላጊውን እርምጃ በመውሰድ ሕዝብን ከዘረፋና ከመጭበርበር ሊጠብቅ ይገባል።
አጭበርባሪነት በሃይማኖት ኃጢአት፣በባህል ነውር፣በሕግ ወንጀል የሆነ እኩይ ምግባር በመሆኑ የሀገሪቱ ሕግ አስከባሪ አካል ሰንዶችን ሰብስቦ በአስቸኮይ ፍትሕ ሊሰጥ ይገባል።
እምነትን ከለላ አድርገው በሃገሪቱ ውስጥ ሕዝብን እያጭበረበሩና በሐሰት እያምታቱ ያሉት ሐሰተኛ ነቢያት ኢትዮጵያ ውስጥ ያለውን የሕግ ቸልተኝነት በመመልከት በአደባባይ በኢትዮጵያ የወንጀለኛ መቅጫ ሕግ ውስጥ የተደነገጉ ድንጋጌዎችን በመጣስ የሞራልና የሥነ ምግባር ብልሹነትን በሕብረተሰቡ ዘንድ በስፋት እያስፋፋ ይገኛሉ።
ስለሆነም የኢትዮጵያ የሕግ አስፈጻሚ አካላት የጎረቤት ሀገሮችን ተሞክሮ ከግንዛቤ በማስገባት በሐሰተኛ ነቢያት ላይ የማያዳግም ፍትሐዊ እርምጃ ሊወስዱ ይገባል።
እሥራኤል ዳንሳ ቀሳጢ የጥፋት ልጅ በመሆኑ እርሱን እውነተኛ ነቢይ ነው ብላችሁ
የምትከተሉ ሰዎች የወንጀሉ ተባባሪ በመሆን በእግዚአብሔር ላይ እያመጻችሁ ነውና ፈጥናችሁ ንስሐ ግቡ ራሳችሁንም ለዩ
No automatic alt text available.
እባካችሁ ይህንን መልህክት ሼር በማድረግ ለሚመለከታቸው አካላት እንዲደርስ እናድርግ።

Image may contain: 1 person, sitting
No automatic alt text available.

No comments:

Post a Comment

wanted officials