ለ5 ሚሊዮን ኢትዮጵያውያን የአስቸኳይ የምግብ እርዳታ ምላሽ አልተገኘም
ኢሳት ዜና (ጳጉሜ 2, 2007) የኢትዮጵያ መንግስት በሃገሪቱ ለአስቸኳይ የምግብ እርዳታ ለተጋለጡ ወደ አምስት ሚሊዮን ሰዎች ከዓለም አቀፍ ማህበረሰብ ምላሽ አለማግኘቱን ገለጠ። ከእርዳታ ሰጪዎች የታየውን ዝምታም ተከትሎ መንግስት ከአገር ውስጥ ገበያ የእህል ግዥ ለማከናወን መገደዱን የግብርና ሚኒስትር ባለስልጣናት ለጋዜጠኞች አስታውቀዋል። የእርዳታ ሰጪዎች በመካከለኛው ምስራቅ አገሮች በጸጥታ መደፍረስ ምክንያት ችግር ውስጥ ለገቡ እንዲሁም በመሬት መንቀጥቀጥ ለተጎዱ የኔፓል ህዝብ እርዳታ በማቅረብ ላይ በመሆናቸው ምክንያት ለኢትዮጵያ ምላሽ አለመስጠታቸውን የግብርና ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ምትኩ ካሳ ተናገረዋል። ክፍተኛ የመንግስት ባለስልጣናት ሃገሪቱ የተከሰተው የድርቅ አደጋ ካለውጭ እርዳታ ለብቻዋ ትቋቋማለች ሲሉ መግልጻቸው ይታወሳል። ይሁንና በድርቅ ለተጎዱ ሰዎች እርዳታውን እያስተባበረ የሚገኘው የግብርና ሚኒስቴር የዓለም አቀፍ ማህበረሰብ ለኢትዮጵያ የዕርዳታ ጥያቄ ምላሽ ባለመስጠቱ ምክንያት ከፍተኛ መጠን ያለው እህል ከአገር ውስጥ ገበያ እየተገዛ መሆኑን ይፋ አድርገዋል። አለም አቀፍ ግብረ-ሰናይ ድርጅቶች በበኩላቸው በኢትዮጵያ የተከሰተው የድርቅ አደጋ እየተባባሰ ሊሄድ እንደሚችል ዛረ ሰኞ አሳስበዋል። ሃገሪቱ በድርቅ ለተጎዱ ዜጎቿ በቂ የእርዳታ ምላሽ አላገኘችም የሚሉት ድርጀቶች ጉዳዩ የሚመለከታቸው አካላት የቅርብ ክትትል ማድረግ እንዳለባቸው ገልጸዋል። የተባበሩት መንግስታት ድርጀት የእርዳታ ማስተባበሪያ ጽ/ቤት በበኩሉ የድርቁ አደጋ በአፋርና በሶማሊ ክልሎች በእንስሶች ላይ ጉዳት እያደረሰ መሆኑን በድጋሚ አሳስቧል። መንግስት ከአገር ውስጥ ገበያ እህሎችን ለመግዛት መወሰኑ በዋጋና በአቅርቦት ላይ ተጽዕኖ ሊያስከትል እንደሚችሉ ተጠቃሚዎች በመግለጽ ላይ መሆናቸውን ከሃገር ቤት የደረሰን መረጃ አመልክቷል። ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በምግብ ነክ ሸቀጣሸቀት የታየው ከፍተኛ የዋጋ ጭማሪ የሃገሪቱ አጠቃላይ የዋጋ ግሽበት እንዲያሽቆለቁል ማድረጉ ይታወሳል።

No comments:
Post a Comment