Which one you first choose? በቅድሚያ የሚፈልጉት

Tuesday, September 1, 2015

"በ"ጀነራል" ሳሞራ የኑስ የተመራው የሰራዊቱ አዛዦች ግምገማ ያለ ውጤት ተበተነ፡

ህወሃት ከ40 አመት በሗላም እዛው ደደቢተ ነው!!
=============================================
"በ"ጀነራል" ሳሞራ የኑስ የተመራው የሰራዊቱ አዛዦች ግምገማ ያለ ውጤት ተበተነ፡ 
አንዳንድ አዛዦች ከስራቸው ታግደው በመቐለ ስታፍ ታግተዋል"
================================================
በጀኔራል ሳሞራ የኑስ እየተመራ በአዲስ አበባ ሲካሄድ የቆየው የመከላከያ ከፍተኛ አዛዦች ግምገማዊ ስብሰባ ያለመፍትሄ መበተኑን ለማወቅ ተችሏል።በመረጃው መሰረት- በአዲስ አበባ ከተማ በጀኔራል ሳሞራ የኑስ የተመራው የገዥው መንግስት ኢ.ህ.አ.ዴ.ግ የመከላከያ ሰራዊት ከፍተኛ አዛዦች ከነሃሴ 12 ቀን 2007 ዓ/ም ጀምሮ ሲካሄድ እንደቆየ የገለፀው መረጃው፤ የስብሰባው አጀንዳም መንግስት አዲስ የመከላከያ ሰራዊት አሰልጥኖ ይለቃል ወደ እናንተ ሲደርስ ግን በርካታው ሰራዊት ይጠፋል ምክንያቱ ምንድንነው? ስራችሁ ምንድንነው? የሚሉና ሌሎችም በመድረክ መሪው በሳሞራ የኑስ የቀረቡ ሲሆን በርካታዎቹ በተቃውሞ ድምፅ ስለተቃወሙት በመካከላቸው ልዩነት ተፈጥሮ ስብሰባው ያለ ፍሬ ነገር እንደተበተነ ለማወቅ ተችሏል።
መረጃው ጨምሮም- ግምገማው በከፍተኛ አዛዦች ዘንድ መረዳዳት ያልነበረው ስብሰባ እስከ ታች እዞች የወረደ ሲሆን በተለይ በሰሜን እዝ ከሚገኙ ሬጂመንቶች በሚጠናቀቀው አመት ብቻ በረከት ያለ ቁጥር ያላቸው ወታደሮች በመጥፋታቸው ዋና መነጋገሪያ አጀንዳ በመሆኑ አንዳንድ አዛዦች ከስራቸው ታግደው በመቐለ ስታፍ እንደሚገኙ ለማወቅ ተችሏል።
========================================
የይስሙላው የ12ኛው የህወሃት ጉባኤ የትግራይን ህዝብ አስደስቶ አባይ ወልዱንና የሙስና ተባባሪዎቹን አስደስቶ ተጠናቀቋል።
==============================================
የህወሃት የጉባኤ ተሳታፊዎች ነሃሴ 17 ቀን 2007 ዓ/ም አባይ ወልዱ ትግራይን የመምራት አቅም የለውም ድህነትና ሙስና እንዲስፋፋ አድርጎ ህዝባችንን እያሰቃየ ነው የሚል ሃሳብ እንዳቀረቡ ለማወቅ ተችሏል።
ለ12ኛ ጊዜ የተካሄደው የይስሙላ የህወሃት ጉባኤ የተሳተፉ ሰዎች ነሃሴ 17 ቀን 2007 ዓ/ም ካቀረቡት ሃሳብ መካከል አባይ ወልዱ የትግራይ ክልልን መምራት የለበትም በሱ ፋንታ አርከበ ዕቑባይ መምራት አለበት ካሉ በኋላ ምክንያቱም ህወሃት ስልጣን እስከያዘበት ጊዜ ድረስ ምንም ለውጥ የሚባል ነገር አልታየም በሙስና እሱ ተዘፍቆ ሌሎችም እንዲጨማለቁ ፈቅዷል ህዝቡም ችግሩን እንዲፈታለት በተደጋጋሚ አቤቱታ ቢያቀርብም ፈጣን ምላሽ አይሰጥም በአጠቃላይ አባይ ወልዱ አቅም ስለሌለው ይወገድ የሚል እንደነበር ምንጮቻችን ከስፍራው ያደረሱልን መረጃ አብራርቷል።
መረጃው ጨምሮም- በዞን ደረጃ ሙስና ከታየባቸው ዞኖች መካከል ምዕራብ ትግራይ መሬት ለሃብታሞች በማደል በርካታ ገንዘብ መቀበል በመቀለ ዞንም የቤት መስሪያ መሬት እንሰጣችኋለን ለግል ጥቅማቸው ገንዘብ መቀበል ማዕከላዊ ዞን ለከተማ ልማት የተመደበ በጀት ተባብሮ ማጥፋት በአጠቃላይ የትግራይ ክልል በልማት ኋላ ቀር እንድትሆን ያደረጉ ባለስልጣናት መቀየር እንዳለባቸው ቀርቦ መፍትሄ ሳይደረግበት እንደታለፈ ታወቋል።
============================================
ለአዲግራት ከተማ ተብሎ የተመደበውን በርካታ ገንዘብ የህወሃት ባለስልጣናት ተከፋፈሉት1
===============================================
ለአዲግራት ከተማ ተብሎ የተመደበውን በርካታ ገንዘብ በስራ ላይ ሳይውል በስርዓቱ ባለስልጣናት መበላቱን ምንጮቻችን ከስፍራው ገልፀዋል።በአዲግራት ከተማ ያለው ስር የሰደደ የመብራት አቅርቦት ችግር ለመፍታት ለዝርጋታና ለእድሳት በሚል የተመደበ 4 ሚሊዮን ብር በስራ ላይ ሳይውል በባለስልጣናት ስለተጠፋፋ መብራት ማግኘት የሚገባቸው የከተማዋ አካባቢዎች በጨለማ ተውጠው እንደሚገኙ ታወቋል።
መብራት ካላገኙ አካባቢዎች መካከል የተወሰኑትን ለመጠቅስ ያህል ከፒያሳ እስከ ሃዲሽ አዲ መብራት የሌለው ከየዶክተር መንገሻ አከባቢ እስከ ካምቦ፤ ከፒያሳ እስከ ሆስፒታል፤ ከመቐለ መንገድ እስከ ዛላምበሳ መስመር ያለውና ሜዳ አጋመ አካባቢ የሚገኙ ቦታዎች ጠቅልለው መብራት አግኝተው እንደማያውቁ መረጃው ጨምሮ አስረድቷል። ምንጭ ትህዴን

No comments:

Post a Comment

wanted officials