የአራት ሴቶች ‹‹ባል›› የሆነችውን ‹‹ሴት›› ተዋወቋት
በኬንያ እንግዳና በጣም አስገራሚ የሆኑ የጋብቻ ልምምዶችን በአገሪቱ ማህበረሰቦች መካከል ሲከናወኑ ታገኛላችሁ፡፡በእነዚህ ያልተለመዱ የጋብቻ ልምምዶች መንስኤነትም ብዙዎች ከውሃ አጣጪዎቻቸው ለመለያየት መብቃታቸውን ትረዳላችሁ፡፡ ለምሳሌ ስቴሲ የተባለችን አንዲት ሴት እንውሰድ ከባሏ ጋር ጋብቻ ከመሰረቱ ስምንት አመታት ተቆጥረዋል፡፡ነገር ግን የባሏን ቤተሰቦች መጎብኘት የቻለችው ለስድስት ግዜያት ብቻ ነው፡፡ምክንያቱን ስታብራራም ‹‹ባህላቸውን እጠላዋለሁ፣እርሱ ከምዕራብ ነው፣እነርሱ አላስፈላጊ የሆኑና እንግዳ የሆኑ ልምምዶች አሏቸው፡፡
የእርሱ ሰዎች ወደቤታቸው እንዳልገባ አግደውኛል ምክንያቱም የሁለተኛ ልጃችንን የመጀመሪያ ጸጉር ማስላጨት ግዴታ እንዳለብኝ በመናገራቸውና እኔ ስላልተቀበልኳቸው ነው››ብላለች፡፡ ሴት ለሴት ጋብቻ ብዛት ያላቸው መሐን የኬንያ ሴቶች በትዳር አጋሮቻቸው ለእንዲህ አይነት ጋብቻ ተላልፈው ተሰጥተዋል፡፡ሴት ባሎች ለትዳር ለሚመርጧት ሴት ቤተሰብ ጥሎሽ ይሰጣሉ እናም በቁጥጥራቸው ስር ያደርጓቸዋል፣አንዳንድ ግዜም በድብቅ ሚስቶቻቸው ልጅ እንዲወልዱላቸው የወንድ ዘር የሚሰጧቸውን ወንዶች ይቀጥሩላቸዋል ወይም ያመጡላቸዋል፡፡ የሴት ባሏም ሚስቷ ልጅ ስትወልድ ህጋዊና በማህበረሰቡ ተቀባይነት ያላት ‹‹አባት›› ተደርጋ ትወሰዳለች፡፡እንዲህ አይነት ጋብቻ በካፕሱንዲ ፣ኡሲን ጊሹ ካውንቲዎች የተለመደ ነው፡፡በአካባቢው የምትኖር አንዲት ሴት ከተለመደው ወጣ ባለ መልኩ አራት ሴቶችን አግብታለች፡፡ ከወንድ ጋ ያልተሳካ ጋብቻ አሁን ኤልሳቤጥ ቼማሱንዴ የ92 ዓመት አሮጊት ናቸው፡፡በናሮክ ካውንቲ ትዳር መስርተው ይኖሩ ነበር፡፡ነገር ግን ለአስር አመታት የዘለቀው ትዳር ልጅ አላፈራም፡፡በዚህ ምክንያትም ከማህበረሰቡ የሚደርስባቸውን ነቀፋ መሸከም ባለመቻላቸው ወደ ናንዲ ካውንቲ ተሰደዱ፡፡
በናንዲ ማህበረሰብ ዘንድ መሀን ሴቶች የጾታ ተመሳሳያቸውን እንዲያገቡና ልጅ እንዲያገኙ የሚፈቀድ በመሆኑም ኤልሳቤጥ ይግረማችሁ ብለው አራት ሴቶችን አገቡ፡፡አናዳጁ ነገር ቼማሱንዴ ካገቧቸው አራት ሴቶች መካከል ሁለቱን ወንዶች የነጠቋቸው መሆኑ ነው፡፡ ለመጀመሪያዋ ሚስታቸው ጥሎሽ ስድስት ላሞችና አራት ፍየሎችን ጥለው የነበሩት ኤልሳቤጥ ከትዳራቸው አንድ ወንድና ሴት ተበርክቶላቸዋል፡፡የልጆቻቸው እናት ግን በአሁኑ ወቅት አብራቸው አትኖርም፡፡ከሁለተኛ ትዳራቸውም ሁለት ወንዶችና ሴቶችን ብያገኙም አብራ ለመዝለቅ አልፈቀደችም፡፡ሴቶቹ የወንድ ዘራቸውን የለገሷቸውን እውነተኞቹን የልጆቻቸውን አባቶች ተከትለው መሄዳቸው ደግሞ አሮጌቷን ባል ያበሳጫቸዋል፡፡
Dawit selomon
https://thevoiceofunity.wordpress.com/2015/09/25
No comments:
Post a Comment