Which one you first choose? በቅድሚያ የሚፈልጉት

Friday, September 11, 2015

የአይኤሱ ከፍተኛ ኮማንደር በአንዲት የወሲብ ባሪያው ተገደለ




ኢራቅ እና ሶሪያ ውስጥ በሰፋት የሚነቀሳቀሰው ፣ እራሱን “የእስላሚክ መንግስት” Islamic State ) በማለት የሚጠራው ፣ ነገር ግን ሃይማኖት እና መልካም ሰነ ምግባሮች የለሹ አክራሪ ቡደን በቁጥጥር ሰር ካደረጋቸው በርካታ የወሲብ ባሪያ (Sex slaves) እህቶች መካከል አንዷ በአክራሪው ቡድን ላለፉት ሶስት ወራት ከደረሱባት ተደጋጋሚ የወሲብ ጥቃቶች የተነሳ የቡድኑ ከፈተኛ ኮማንደር የነበረ ግለሰብን መግደሏ ተነገረ ።
የኩርዲስታን ዲሞክራሲ ፓርቲ አፈቀላጢ የሆኑት ሳይድ ሙሞዚኔ ሰኞ እለት አልሱማሪያ ከተባለው የኢራቅ የግል ቴሊቭዥን ጣቢያ ጋር ባደረጉት ቃለምልልስ ሰሟ ያልተጠቀሰው ነገር ግን አናሳ የሆኑት የኢዛዲ ጎሳ ተወላጅ እንደሆነች የተገመተች አንዲት በ አይኤስ ታጣቂዎች እጅ የወደቀች ሴት የቡድኑ ቁልፍ ሰው የሆነ እና በበረሃ ሰሙ አቡ አናስ የተባለ ኮማንደር ለተለያዩ ተዋጊዎች የወሲብ ፍላጎታቸው መወጣጫ ሲያደርጋት በመክርሙ ከደረሰባት ግፍ እና በደል የተነሳ ተጠቃሹ ኮማንደርን የኢራቅ ሁለተኛ ከተማ በሆነችው ሞሱል አቅራቢያ ቅዳሜ እለት መግደሏን ተናገረዋል።ምንም እንኳን አፈቀላጤው የአይኤስ የወሲብ ባሪያ የነበረችው እህት ኮማንደሩን እንዲት እንደገደለችው ባይናገሩም አንዳንድ ዘገባዎች ግን በጥይት ተኩሳ እንደገደለችው ገምተዋል። የዚህች ምስኪን ሴት እጣ ፈንታ ምን እንደሆነ ለጊዜው አልተገለጸም ።
ካለፈው 2014 እኤአ ጀምሮ በርካታ የኢራቅ እና የሶሪያ ከተሞችን የተቆጣጠረው አይኤስ ለወሲብ ባርነቱ መጠቀሚያ አንሆንም(አሽባሪዎችን አናገባም ) ያሉ ከ 150 በላይ ሴቶችን (እርጉዞችን ጨምሮ) እንደገደለ የተባበሩት መንገስታት ድርጅት ልዪ ተወካይ በቅርቡ ያወጣው ዘገባ ያትታል። አይ ኤስ እድሜያቸው ከ9 እስከ 40 አመታት የሚገመቱ የሺያት ሙስሊሞች፣ኢዚይድ እና ከርሲቲያኖችን ሴቶችን እርቃናቸውን በአደባባይ እንዲቆሙ በማደረግ መጀመሪያ ለቡድኑ መሪዎች፣ቀጥሎም ለኢሚሪዎች(ኮማንደሮች)፣ በሰተመጨረሻም ለተራ ተዋጊዎች ከ 165 ዶላር እሰከ 41 ዶላር ( እዚህ ላይ የትናንሾቹ ሴቶች ዋጋቸው ከፍ ይላል) እና እንዳንድ ሴቶች እሰከ 22 ጊዚያት እንደተሸጡ ተዘግቧል።አይ ኤስ ባለፈው ሜያዚያ መባቻ ላይ 28 ኢትዮጵያዊያን ሰደተኞችን ሊቢያ ውስጥ እጅግ ዘግናኝ በሆነ ሁኔታ አንገታቸውን በሰይፍ ቀልቶ ፣ በጥይት ደብድቦ መግደሉ እና ድርጅቱም ከፍተኛ ሕዝባዊ ቁጣ መቀስቀሱ አይዘነጋም።ይህ እቁይ ቡድን በሚሊዮን ለመቆጠሩ ሰላማዊ ዜጎች መፈናቀል እና በመቶ ሺዎች ሞት ምክንያት ሲሆን ቡድኑን ከሚዋጉት መካከል የሴቶች ሚና ከፍተኛ መሆኑ ይነገራል።

No comments:

Post a Comment

wanted officials