Which one you first choose? በቅድሚያ የሚፈልጉት

Thursday, September 3, 2015

ሁለት ሕጻናት እና ሚስቱን በሰሞኑ የባህር ማዕበል የተነጠቀው አባወራ ሀዘን



አሳዛኙ የቤተሰብ ፍጻሜ
-
የሁለቱ ስደተኛ ህጻናት ወላጅ አባት ተፈጥሮ በጭካኔዋ ልጆቹን በውሃ ነጥቃ ህይወታቸውን ከመውሰዷ ቀደም ብሎ በህይወት ይቆዩለት ዘንድ ሁለት እጆቻቸውን በመያዝ የተቻለውን አድርጎ ነበር፤ ልጆቹ በውሃው ሲወሰዱም በአቅም ማጣት በውሃው እየተላተመ ተመልክቷቸዋል፡፡
የሶስት አመቱ አይላን ኩርዲና የአምስት አመቱ ጋሊፕ በሶሪያ የተቀሰቀሰውን ጦርነት ከሸሹ ሌሎች የአገራቸው ስደተኞች ጋር በጀልባዋ ተሳፍረው የግሪክን አይስላንድ ኮስን አቋርጠው ቱርክ ከገቡ ቀላል የማይባል ግዜ አሳልፈዋል፡፡
የአይላን አካል በባህሩ ዳርቻ አሸዋ ላይ ተደፍቶና የውሃው ግሳት እየገፈተረው በማህበራዊ ድረ ገጾች ለእይታ መቅረቡ አለምን በሐዘን እንድትመታ አድርጓታል፡፡በአገሪቱ የተፈጠረው ሰብአዊ ቀውስም ከየትኛውም ግዜ በላይ ትኩረት እንደሚሻው ማሳያ ተደርጎም እየተወሰደ ነው፡፡
ሁለቱ ህጻናት ከእናታቸው ሬሃን ጋር ይህችን አለም ተለይተዋል፡፡አባታቸው አብዱላህ በህይወት መትረፍ ቢችልም ቤተሰቦቹን ለማዳን ያደረገው ጥረት አንዳቸውን እንኳን በህይወት ሊያተርፍለት አልቻለም፡፡
አይላንና ጋሊፕ የህይወት መጠበቂያ ጃኬት ባለማግኘታቸው ከቦድረም ቱርክ የበዓል ዝግጅት መልስ ለ30 ደቂቃዎች ያህል ባህር ላይ ከቆየችው አነስተኛ ጀልባ በህይወት መትረፍ ሳይችሉ ቀርተዋል፡፡
በካናዳ የምትኖር የህጻናቱ አክስት ዘመዶቿ ወደ ካናዳ መግቢያ ቪዛ በመከልከላቸው ለደላሎች ገንዘብ በመክፈል አስቸጋሪውን ጉዞ ለመጀመር መገደዳቸውን መናገሯም ተሰምቷል፡፡

ዳዊት ሰሎሞን 

No comments:

Post a Comment

wanted officials