Which one you first choose? በቅድሚያ የሚፈልጉት

Friday, September 18, 2015

አሳዛኝ ዜና ኮተቤ በሚገኝ ድልድይ ውስጥ አንድ ግለሰብ ተገድሎ ተገኘ

አሳዛኝ ዜና
ሰው በሀገሩ ከሀገር ውጪ በባህሩ በየሜዳው በየገደሉ እንደቀልድ ሞቶ ተገኘ የሚል ዜና እየሰማን ሞትን ተላመድ ነው መሰለኝ ሰው ሞተ ሲባል የሚያስደነግጥ ዜና መሆኑ እየቀረ ነው። ከቀናት በፊት ሶሎሜ የተሰኘች ወጣት በአንድ የገዢው ፓርቲ ፖሊስ መገደሏን ሰምተን ሳንጭርስ አሜሪካ ውስጥ ኢትዮጵያዊ ወጣት መገደሉን አከሉልን ቀጠል አርገው ዱባይ ውስጥ አንዲት ኢትዮጵያዊ መገደሎን ሰማን አዘንን ሀዘናችንን ሳንጨርስ ዛሬ ሌሊቱን አዲስ አበባ ኮተቤ በሚገኘው ድልድይ ውስጥ ይህ ምስሉ የምትመለከቱት ግለሰብ ተገድሎ ተገኝቷል።
ከሥፍራው ባገኘሁት መረጃ መሰረት ይህ ጽሑፍ እስከተፃፈበት ሰአት ድረስ የሟች አስክሬን እዛው ድልድይ ውስጥ ወድቆ የሚያነሳው አጥቶ ሰው ከቦ እየተመለከተው ይገኛል።
ፍትህ በሌለበት ሀገር ፍትህ ለእገሌ አንበል ለፍትህ እራሱ ፍትህ በሉለት።
የሞቱትን ነብስ በገነት ያኑርልን ወንድምና እህቶቻችንን ።

No comments:

Post a Comment

wanted officials