የአቡነ ጳውሎስ ሐውልት እንዲነሳ ተወሰነ
ትናንት የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ሲኖዶስ ባደረገው ስብሰባ ቦሌ መድኃኒዓለም ቤተክርስቲያን የሚገኘው ባለ ነሐሱ የአቡነ ጳውሎስ ሐውልት እንዲነሳ መወሰኑን መረጃዎች ጠቁመዋል፡፡የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን አምስተኛው ፓትርያርክ የነበሩት አቡነ ጳውሎስ በህይወት በነበሩበት ዘመን ከአንዲት ግለሰብ ተበረከተ በተባለ ገንዘብ ሐውልቱ ለበዓለ ሲመታቸው ድምቀት ተገንብቶላቸው መመረቃቸው አይዘነጋም፡፡
በህይወት እያሉ ሐውልቱ እንዲሰራላቸው በመደረጉና ከእርሳቸው በፊት የነበሩ ፓትርያርኮች እንዲህ አይነት ልማድ ያልነበራቸው በመሆኑ በሐውልቱ መሰራት ብዙዎች ቅሬታ ሲያሰሙ መቆየታቸው አይዘነጋም፡፡ሲኖዶሱ ከሐውልቱ በተጨማሪ የአቡነ ጳውሎስ ምስል ከየአብያተ ክርስቲያናቱ እንዲነሳ ትዕዛዝ ማስተላለፉም ተሰምቷል፡፡
ፓትርያርክ በህይወት እያለ ፓትርያርክ አይሾምም የሚለውን የቤተክርስቲያኒቱን ቀኖና በተጻረረ መልኩ የተሾሙት አባ ጳውሎስ በድንገተኛ ህመም ይህችን አለም ከዛሬ ሶስት አመት በፊት ከመሰናበታቸው አስቀድሞ አወዛጋቢ የተባለ የፕትርክና ዘመን አሳልፈዋል፡፡

No comments:
Post a Comment