ዶ/ር ሽመልስ ተክለጻዲቅ መኩሪያ አረፉ
መስከረም ፲፫ (አስራ ሦስት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ዶ/ር ሽመልስ ከሌሎች ታዋቂ ምሁራንና ፖለቲከኞች ጋር በመሆን ቀስተደመናን ፓርቲ፣ ከዚያም ቅንጅት እንዲመሰረት ከፍተኛ አስተዋጽኦ አድርገዋል። የቅንጅት መሪዎች በታሰሩበት ወቅትም ዶ/ር ሽመልስ፣ ትግሉ እንዳይቀዛቀዝ ከፍተኛ ስራ ሲሰሩ የቆዩ ሲሆን፣ አንድነት ፓርቲ በተመሰረተበት ወቅትም ፓርቲውን በአመራር አባልነት አገልግለዋል። በኢትዮጵያ ውስጥ ነጻ የሬዲዮና ቴሌቪዥን ስርጭት ለመጀመር የተቋቋመውና በሁዋላ በስርዓቱ ሃላፊዎች እንዲፈርስ የተደረገውን አዲስ ብሮድካስቲንግ ኩባንያ ከሌሎች ምሁራንና ባላሀብቶች ጋር በመሆን መስርተዋል። ዶ/ር ሽመልስ የታዋቂው የታሪክ ተመራማሪ የተክለጻዲቅ መኩሪያ ልጅ ነበሩ።

No comments:
Post a Comment