የሰማያዊ ፓርቲ ብሔራዊ ምክር ቤት የስራ አስፈፃሚ እጩ የኮሚቴ አባላት ብቃት መርምሮ ውሳኔ አስተላለፈ፡፡የፓርቲው ሊቀመንበር ኢ/ር ይልቃል ጌትነት 10 የካቢን አባላትን ለብሔራዊ ምክር ቤት ያቀረቡ ሲሆን ከእንዚህም መካከል ፣ምክር ቤቱ ኃላፊነታቸውን ተቀብሎ ያፀደቃቸው ፡-
1ኛ. አቶ ነገሰ ተፋረደኝ፡- ም/ሊቀመንበር
2ኛ .አቶ አበበ አካሉ፡- የውጭ ጉዳይ ኃላፊ
3ኛ. አቶ እስክንድር ጥላሁን ፡-የጥናት እና ስትራቴጂ ኃላፊ
4ኛ. አቶ ዮናታን ተስፋዬ ፡-የህዝብ ግኑኙነት ኃላፊ
5ኛ. ወ/ሮ መዓዛ መሃመድ፡- የሴቶች ጉዳይ ኃላፊ
6ኛ. አቶ ጋሻው መርሻ፡- የድርጅት ጉዳይ ኃላፊ
7ኛ. አቶ አዲሱ ጌታነህ ፡-የሕግ ጉዳይ ኃላፊ ሆነው ፓርቲውን እንዲያገለግሉ የብሐራዊ ምክር ቤት ድጋፉን የሰጠ ሲሆን፣ ከቀረቡ እጩዎች መካከል ምክር ቤት ያልተቀበላቸው፤
1ኛ. አቶ እያስጴድ ተስፋዬ
2ኛ. አቶ ወረታው ዋሴ ሲሆኑ ፣የአባላት መረጃ እና ደህንነት ጉዳይ ኃላፊ ሆነው ለምክር ቤት የቀረቡት እጩ አቶ ስለሺ ፋይሳ ራሳቸውን ከእጩነት አግልለዋል፡፡
በጠቅላላ ጉባሄ የተመረጡት የኦዲት እና ምርመራ ኮሚሽን አባላት በመካከላቸው የሥራ ክፍፍ ያደረጉ ሲሆን፣
1ኛ. አቶ አበራ ገብሩ ፡- ሰብሳቢ
2ኛ. አቶ ሳምሶን ገረመው ፡- ምክትል ሰብሳቢ
3ኛ. አቶ ሀይለገብርኤል አያሌው ፡- ፀሃፊ
4ኛ. አቶ ብርሃኑ መሠለ ፡- አባል
5ኛ. አቶ ሀብታሙ ደመቀ ፡- አበል ፣
በቀጣይ በተጓደሉትን የሥራ ክፍልች፣የአባላት መረጃ እና ደህንነት፣ የወጣቶች እና የፋይናንስ ጉዳይ ኃላፊዎች፤ የፓርቲው ሊቀመንብር አቅርበው ያፀደቃሉ፡፡
No comments:
Post a Comment