“ወንድ ከወንድ፣ሴት ከሴት ጋር አላጋባም” ያሉ የህግ ሹም ወደ እስር ቤት ተወረወሩ
ከታምሩ ገዳ
አንዳንዴ የዚህች አማሪካን ‘ገደብ የለሽ ‘ የሰብአዊ መብቶች ጎተራነቷን ለተመለከተ መገረሙ እና መበረገጉ አይቀረም። ለምሳሌ ንብረቴን፣ቤተሰቤን እና እራሴን እጠብቃለሁ ያለ አሜሪካዊ የጦር መሳሪያ ለመታጠቅ እንደ እኛ አገር የግድ የፓርቲ ሰው አሊያም የድሮ አብዮት ጠባቂ(ሰላም እና መረጋጋት አባል) መሆን የለበትም ።ከአቅራቢያው መደብር ጎራ ብሎ ከቀላል እስከ አውቶማቲክ የጦር መሳሪያ በቀላሉ መግዛት ይችላል። የጦር መሳሪያ ነገር ከተነሳ ዘንዳ አብዛኞቹ ፖሊሶቿ ተጠረጣሪን አድኖ ከመያዘ “አልሞ መተኮስ “ይቀደማቸዋል ይባላል። ለድብርት እና ለዱካክ ማስታገሻ መድሃኒት የፈለገ እንዲሁ (ከጫት በሰተቀር) ያሻውን አደንዛዥ እጽ ከፋርማሲዎች መደረደሪያ ላይ ያገኛል ። በዲያስብሎስ ይሁን በድንጋይ አመልካለሁ ለሚልም መንገዱን ጨርቅ ያርግልህ/ሽ የባላል። ጽኦታዮን(ወንድ ወደ ሴትነት ፣ሴት ወደ ወንድንት ) አሰቀይራለሁ ላለም ምላሹ ገንዘብህን ይጭነቀው እንጂ… ነው ።
ታዲያ በሕጋዊ ገንዘቦቿ ላይ ሳይቀር የእግዜአሔርን ስም የለጠፈችው ፣ መሪዎቿም ቢሆኑም በንግግራቸው መጨረሻ ላይ “እግዜአብሔር እገራችንን ይባርክልን” የሚሉላት ይህቺ የአለማችን ቁጥር አንድ ሃያል አገር አማሪካን አንዳንድ ጊዜ ከፈጣሪ ህግጋት እና ከሞራል ደንቦች ጋር የሚጣረሱ ነገሮችን ሰትፈጽም “የዚህች የአሜሪካ ዲሞክራሲን የሚገደበው ምነው አንድ ሃይል ጠፋ?፣ ለመሆኑ አሜሪካ የትኛው እግዜአብሔርን ነው አመልካለሁ የምትለው?” በሎ መጠየቁ አይቀርም።
ባለፈው ሰኔ ወር መባቻ ላይ የአሜሪካው ፈደራል ፍርድ ቤት 5 ለ 4 በሆነ የድምጽ አብላጫ ያጸደቀው የተመሳሳይ ጾታ ጋብቻ(Same Sex Marriage) ውሳኔን ተከትሎ በረካታ አሜሪካኖች ከህጉ ጋር ሆድ እና ጀረባ ሆነዋል። አንዳንዶቹ የህግ ባለሙያዎች እና የሃይማኖት መረዎች ሳይቀሩ ውሳኔውን በአደባባይ ሲያወግዙ ተስተወለዋል ። የከንታኪ ግዛት ነዋሪ የሆኑት የ 49 አመቷ ወ/ሮ ኪም ዴቭስ የራውን ቀበሌ የውል እና ህጋዊ ሰንድ ሰጪ ተቋም ሃላፊ (ክላርክ) ሲሆኑ ይህንንም ሰልጣን ለማግኘት 53% የህዝብ ደጋፍ አግኝተው ነበር ።ታዲያ ወ/ሮ ኪም ሰሞኑን ሁለት ወንዶችን እንዲያጋቡ እና ለጋብቻቸወም በፊርማቸው እውቅና እና የጋብቻ ሰርተፊኬት እንዲሰጡ ቢጠየቁ ወ/ሮ ኪም ምላሻቸው “አይቻልም፣አይሞከርም ነበር”።ወ/ሮዋ ለእምቢታቸው ምክንያቱን ሲጠየቁ የሰጡት ምላሽም “እግዜአብሔር ወንድ (አዳምን) ከሴት(ከሔዋን) ጋር አጣመረ ፥ሰረጋቸውንም ባረከ እንጂ፣ ወንድ ከወንድ ፣ሴት ከሴት እንዲጋቡ አለፈቀደም” የሚል ነበር ።
ጉዳዮም ወደ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ሄዶ ወ/ሮ ኪምም አቋማቸውን እሰክ አለፈው ሰኞ ድረስ አንዲቀይሩ በዳኛው የቀን ገደብ ቢሰጣቸውም ከዛሬ አራት አመት ጀምሮ ሐይማኖታቸውን ጠበቅ ማድረግ የጀመሩት ወ/ሮ ኪም ማክሰኞ እለት በጽሁፍ በሰጡት ምላሽ”እኔ በማንም ሰው ላይ ጥላቻ የለኝም ፣ነገር ግን ጉዳዩ የ ወንድ (ከወንድ) ሴት (ከ ሴት) ጋር ማጋባት/ማፈራረም ሳይሆን ከመንግሰተ ሰማይ እና ከ ሴኦል አንዱን መምረጥ ሰለሆነ እኔም የመንግስተ ሰማያቱ ጉዳይን መርጫለሁ።” በማለት አቋማቸውን አስታውቀዋል።
ሓሙስ እለት በዋለው የፍ/ቤት ውሎ ዳኛው ዲቪድ ወ/ሮ ኪም ችሎቱን ተዳፍረዋል (ኮንተምፕት ኦፍ ኮርት) በሚል አንቀጽ በአመት ሰማኒያ ሺህ ዶላር የሚከፈላቸው፣የእርሳቸው ስም እና ፊርማ የሌለበት ሰንድ ዋጋ ቢስ የሆነው ወ/ሮ ኪም ዴቪስን በገንዘብ ቅጣት ሳይሆን ወደ እስር ቤት መጽሃፍ ቅዱሳቸውን ብቻ ይዘው እንዲወረዱ እና ወ/ሮዋም አቋማቸውን እስከ ሚቀይሩ ድረስ በእሰር ቤ/ት እንዲቆዩ ትእዛዝ አስተላልፈዋል። ዳኛውም ከወሳኔው በሁዋላ “ እኛ አሜሪካኖች ሁል ጊዜ ልዩነቶች አሉን ፣ነገር ግን ከሌሎች አገሮች የምንለየው እኛ አሜሪካኖች ለህግ የበላይነት ሰለምንገዛ ብቻ ነው “ብለዋል ።ውሳኔውም ወዲያውኑ በመቶዎች የሚቆጠሩ ደጋፊዎች እና ተቃዋሚዎች ከችሎት አደባባይ እንዲኮለኮሉ የገፋፋ ሲሆን የዳኛው ውሳኔን የደገፉ ወገኖች “ወ/ሮ ኪም የሕዝብ አገልጋይነቷን በመዘንጋት እራሷን ለወህኔ ቤ/ት ዳረገች” ሲሉ ተደምጠዋል። የዳኛውን ወሳኔ የተቃወሙ ወገኖች በበኩላቸው “የሃይማኖት ነጻነት ዛሬ በምድረ አሜሪካ አፈር ድሜ ግጧል፣ጋብቻ በወንድ እና በሴት መካከል ብቻ ነው ያለች አንዲት አሜሪካዊት ዜጋ ለመጀመሪያ ጊዜ እንደ ወንጀለኛ ተቆጥራ ወደ እስር ቤት ተወርወረች፣ወ/ሮ ኪም ወንጀለኛ ሳትሆን የህሊና እስረኛ ነች” በማለት ቅረታቸውን አሰምተዋል። ለሰላማዊ ሰልፍም ተዘጋጅተዋል። የወ/ሮ ኬም ባለቤት ሚስተር ጆእም ቢሆኑ “ሚስቴ የፈለገው ቢመጣ አቋሟን አትለውጥም” በማለት ለባለቤታቸው አጋርነታቸውን ገልጸዋል። ዜጎች የፈለጉትን ሃይማኖት ያለገደብ እንዲያመልኩ እና እንዲተገብሩ በህገመንግስቷ ወስጥ እንደ ቋሚ ምሰሶ የገነባችው አሜሪካ ዜጎቿ “ይህንን ለማድረግ ሃይማኖቴ አይፈቅድልኝም” ሲሉ ግን “እዚህ ጋር ወራጅ አለ!” ማለቷ ዲሞክራሲዋን የተሟላ አላደረገውም። ባራክ ኦባማ ባለፈው ወር ወደ ኢትዮጵያ በመጡ ጊዜ የዚህ የአወዛጋቢው የተመሳሳይ ጾታ ጋብቻን ጉዳይ “ያነሳሉ፣ፈቀዱላቸውም ይላሉ” ተብሎ ተጠብቆ ነበር ። ይሁን እና የዲሲው አራዳ ኦባማም ጉዳዩን አ/አ ላይ “በይለፈኝ” ዘለውት ሰለ “ዲሞክራሲያችን “ እና ሰለ ጀግንነታችን ብቻ ነግረውን በመጡበት መመለሳቸው አይዘነጋም።
- Source : http://www.zehabesha.com/
No comments:
Post a Comment