Which one you first choose? በቅድሚያ የሚፈልጉት

Saturday, September 19, 2015

በዐማሮች ላይ በሚፈፀመው አሰቃቂና ዘግናኝ ዕልቂት ላይ ለሚሣለቀው ለኢሕአፓ ፍኖተ-ዴሞክራሲ ሬዲዮ የተሰጠ አጸፋዊ መልስ



ዐማሮች ላይ በሚፈፀመው አሰቃቂና ዘግናኝ ዕልቂት ላይ መሣለቅ በታሪክና በሕዝብ ያስጠይቃል
በፍኖተ-ሞክራሲ ሬዮ ለቀረበው ውንጀላ ተሰጠ አጸፋ መልስ
ሠሞኑን የኢትዮጵያ ሕዝባዊ አብዮታዊ ፓርቲ (ኢሕአፓ) ንብረት የሆነው «ፍኖተ-ሞክራሲ» በመባል የሚታወቀው የሳተላይት ሬዲዮ ጣቢያ በዐማራው ነገድ ተወላጆች ላይ የጅምላ ክስ አቅርቧል። ክሱ «በአማራ ሕዝብ ስም ሌሎችን መዝለፍ የሚወገዝ ነው» በሚል ርዕስ ዘጋጀውን መግለጫ ነሐሴ ፳፪ ቀን ፪ሺህ፯ ዓ.ም. በሬዲዮ አስተላልፏል[1]፤ በጽሑፍ ደግሞ በተባባሪ ድረ-ገፆች «አሲምባ[2]» እና «ደብተራው[3]» ሠራጭቷል። ከሁሉም የሚያሣዝነው የ«አሲምባ» ድረ-ገፅ አስቀድሞ ለጥፎት የነበረውን የሞረሽ-ወገኔን መግለጫ ሲያነሣ እና የ«ፍኖተ-ሞክራሲን» መግለጫ ሲለጥፍ ለአንባብያን ሚዛናዊ አስተያዬት ሲባል እንኳን ሁለቱንም መግለጫዎች ጎን-ለጎን ያለማቅረቡ ነው። ይህም የድረ-ገፁ አስተዳዳሪዎች የወሰዱትን ሚዛናዊ ያልሆነ ውሣኔ በግልፅ ያመለክታል። የ«ፍኖተ-ሞክራሲ» መግለጫ ዓላማ ሞረሽ ወገኔ የዐማራ ድርጅት«በቤንሻንጉል ጉምዝ ክልል፣መተከል ዞን በሚኖሩ ዐማሮች ላይ የተፈፀመ የዘር ማጥፋት ወንጀል» በሚል ርዕስ ማክሰኞ ነሐሴ ፲፪ ቀን ፪ሺህ፯ ዓ.ም. የሰጠውን በሃቅና በተጨባጭ መረጃ የተደገፈውን ዘገባ ለማጣጣል ነው። ሆኖም «የፍኖተ-ሞክራሲ» ሬዮ ዝግጅት ክፍል ምንም ዓይነት የማጣራት ሙከራ ሣያደርግ፣ መግለጫ ያወጣውንም ሞረሽ-ወገኔን «እንዴት ነው? ምን መረጃ አላችሁ? መረጃው የቱን ያህል አስተማማኝ ነው? ሌላስ ሁለተኛ እና ሦሥተኛ አካል መረጃውን እንዴት ማግኘት ይችላል?» ብሎ ሣይጠይቅ «በጉምዝ ሕዝብ ላይ የተከፈተው ጸያፍ ዘመቻ የአማራን ሕዝብ ተገን አድርጎ በመሆኑ ሊወገዝ የሚገባው ነው።» በማለት በጭፍኑ ተበዳዩን ዐማራ መልሶ ወንጅሏል። «በደለኛ፣ በደለኛ ወታደር በደለኛ ነው፤ ነገር ግን ባላገር (ገበሬ) ይክሣል» ሆነና ነገሩ፣ «ፍኖተ-ሞክራሲ» በዳዮቹን የትግሬ-ወያኔ ሎሌ የሆኑትን የጉምዝ ልሂቃን ድርጊት ከማውገዝ ይልቅ በዐማራው ላይ በሚፈፀመው ዕልቂት ላይ ተሣልቋል።
 አንባቢያን ዕውነቱን ከሐሰቱ፣ እርጥቡን ከደረቁ ለመለየት ይችሉ ዘንድ፣ «ፍኖተ-ሞክራሲ» ሞረሽ-ወገኔን የወነጀለባቸውን ነጥቦች እና በዐማራው ላይ በሚፈፀመው ዕልቂት ላይ ያሠራጨውን ሥላቅ አንድ በአንድ እያነሣን እንተችባቸው።
 1          «በዐማራ ሕዝብ ስም ሌሎችን መዝለፍ የሚወገዝ ነው፣» ይህ የመግለጫው ርዕስ ነው።  ሞረሽ ወገኔ የዐማራ ድርጅት የተመሠረተው በዐማራው  ነገድ ላይ የሚፈጸመውን የዘር ማጥፋት እና የዘር ማጽዳት ወንጀል ለዓለም ማኅበረሰብ፣ በተለይም ለሰብአዊ መብት ተሟጋች ድርጅቶች ለማሰማት ነው። ድርጅታችን የሲቪክ ድርጅት እንጂ፣ የዐማራ ሕዝብ ውክልና አለን፣ አለኝ ያለ አይደለም። አባላቱ እና መሥራቶቹ ዐማራዎች በመሆናቸው፣ ለወገናቸው ችግር አጋዥ ኃይል እንዲፈጠር ድምፅ የሚያሰሙ ተቆርቋሪዎች እንጂ፣ ዐማራው በነቂስ ወጥቶ «ወክለውናል» አላሉም። የውክልና መረጋገጫ ሠነድም የለንም። ይህንም እንድናደርግ እስካሁን ባለው ሁኔታ የሚያስገድድም ሆነ፣ ስሕተት ነው የሚልም የሞራልም ሆነ የሕግ ማዕቀፍ የለም። «ያልተከለከለ ነገር ሁሉ ለማድረግ የተፈቀደ ነው» ይባላልና፣ ሞረሽ-ወገኔም በዚሁ ባልተከለከ መንገድ በመግባት፣ በፖለቲካዊ መንገድ «ትክክለኛ ነው» የሚያሰኘውን አካሄድ ሣንከተል፣ በዐማራው ላይ ጉዳት ያደረሱ ቡድኖችን ድርጊት ደረቁን ሃቅ እናቀርባለን። በመሆኑም ሞረሽ-ወገኔ የሚጨነቀው፦ «ነገሩ ተፈጽሟል ወይ? ከተፈጸመ፣ መቼ? እንዴት? በማን? በምን ምክንያት? እነማን ፈጸሙት?» ለሚሉት ጥያቄዎች አጥጋቢ እና ትክክለኛ መልስ ማግኘት ነው። በዚህም መሠረት በዐማራው ነገድ ተወላጆች ላይ አሠቃቂ እና አረመኔያዊ ጭፍጨፋ ያካሄዱት የጉምዝ ነገድ አባሎች መሆናቸውን በማረጋገጥ መግለጫው በሞረሽ ወገኔ ስም ተሠጥቷል። የ«ፍኖተ-ሞክራሲ» ዝግጅት ክፍል ግን ሃቁን ከማጣራት ይልቅ «የጅብ ችኩል---» ሆኑና ለአስተዛዛቢ ትችት ተጣደፉ፤ በዐማራው ላይ በተፈፀመው አሠቃቂ ዕልቂት ላይም ተሣለቁ።
2          « --ዝምታ ሕዝብን ለጥቃት አሳልፎ መስጠት በመሆኑ ግዳጅና ኃላፊነትን መካድ ይሆንብናል።» የ«ፍኖተ-ሞክራሲ» ዝግጅት ክፍል በግላቸው የወሰዱት ኃላፊነት እና ግዳጅ ካለ ያንን ኃላፊነታቸውን እና ግዴታቸውን መወጣት የእነርሱ ኃላፊነት ነው። ከዚህ ላይ አንባቢ እና አድማጭ ልብ ሊሉት የሚገባው ጉዳይ፣ ባወጡት መግለጫ መሠረት ለራሣቸው ከሰጡት ግዴታዎች እና ኃላፊነቶች መካከል፣ ምንጊዜም በዐማራው ላይ ጥቃት ሲፈፀም አጥፊዎቹን፦ «አይዟችሁ፣ እነዚህ ዐማሮች ጨፍጭፏቸው፣ ግደሉዋቸው» ማለት መሆኑን ነው። ሰብአዊነት የሚሰማው ሰው ጉዳት ለደረሰበት፣ ለተጠቃ ዋስ ጠበቃ ይሆናል እንጂ፣ በትግሬ-ወያኔ ተደራጅተው ዐማራውን ቆራርጠው ለገደሉት፣ ጠብሰው ለበሉት ለአጥቂዎቹ ጉምዞች ባልሆነ ነበር። እንዲህ ዓይነቱን ቅጥ ያጣ እብሪት በምንም ተዓምር የዐማራው ልጅ ሊታገሰው አይገባም። ጅልነቱ ትናንት ቀረ! «እኛም አውቀናል ጉድጓድ ምሰናል!» ሊባል ይገባዋል።
3          «የጉምዝ ሕዝብ/ ቤንሻጉሎች አማራውን ገድለው ጉበቱን፣ ኩላሊቱን፣ የታፋ ሥጋውን በሉ ብሎ ዓይንን በጨው አጥቦ ሕዝብን መዝለፍ አፍሪካን ከሚጠሉ ነጮች የሚጠበቅ እንጂ፣ ለዐማራ ተቆርቋሪ ነን ባዮች ሊሰጥ የሚገባው አደለም ።» ከዚህ ላይ መግለጫውን ያወጣው የ«ፍኖተ-ሞክራሲ» ዝግጅት ክፍል ያሳሰበው የዐማራውን ሥጋ ጠብሰው የበሉት ገዳዮቹ ጉምዞች፣ «ለምን የሰው ሥጋ በሉ ተባሉ?» ብሎ ነው። ሥጋቸው ተጠበሶ የተበሉት ዐማሮች ለእነርሱ ምናቸውም አይደሉም፤ ሰውም አይደሉም፤ በእነርሱ ቤት ሙክት ወይም ጠቦት ናቸው። ሥቃይ የተፈጸመባቸው ዐማሮች ሳያሳዝኗቸው፣ ሥቃይ አድራሾቹ ጉምዞች እንዴት ሊያሳዝኗቸው ቻሉ? በመሠረቱ የ«ፍኖተ-ሞክራሲ» ዝግጅት ክፍል በሬዲዮ ያስተላለፈውን ና በጽሑፍ ያዘጋጀውንመግለጫ ሲያሰራጭ ያጣራው አንዳችም ነገር የለም። ቢያጣሩ ኖሮ እንዲህ ያለ ከሃቅ ጋር የሚጣረስ መግለጫ ባላወጡ ነበር። ልብ ካላቸው መልካን እና አይጋሊ-ሞዛምቢክ ቀበሌዎች (መተከል) ስልክ ደውለው ጉምዞችን ቢያነጋግሩ፣ ጉምዞች በባህላቸው ውሸት ነውር ነውና፣ «አዎ ዐማሮችን አርደን በላናቸው! ሥጋቸው ይጥማል፤» እንደሚሏቸው አንጠራጠርም!
ሞረሽ ወገኔ የዐማራ ድርጅት ለሁለት ወገን፦ ለበዳዩም ሆነ ለተበዳዩ፣ ጥብቅና አይቆምም። የቆመው በአሁኑ ዘመን አንዳችም ተሟጋች ጠበቃ ለሌለው ለዐማራው ነው። በዐማራው ላይ የደረሱ ችግሮችን፣ ከነችግሩ ምንጮች እና ችግር አድራሾቹ በመረጃ በማስደገፍ የተለያዩ መግለጫዎችን አውጥቷል፣ ለወደፊቱም ያወጣል። ሥራችን ወንጀለኞችን ማጋለጥ እና ለፍርድ ማቅረብ ስለሆነ ወደፊትም ይህ አሠራራችን ይቀጥላል። እንደ ሞረሽ-ወገኔ እምነት በዐማራው ላይ በማንኛውም ዘመን ወንጀል የፈጸሙ የማናቸውም ነገዶች ልሂቃን እና ተወላጆች እንዲሁም የፖለቲካም ሆነ «የእገሌ ሕዝብ ነፃ አውጪ ነን» ባይ ድርጅቶች በሕግ መጠየቅ አለባቸው ብለን እናምናለን። ጉምዞችም በትግሬ-ወያኔዎች ጃዝ-ባይነት ወገኖቻችንን ዐማሮችን አርደው በልተዋቸዋልና እፋረዳቸዋለን። የዚያን ጊዜ የ«ፍኖተ-ምክራሲ» ዝግጅት ክፍል እና በባለቤትነት የያዘው ድርጅት ኢሕአፓ ጥብቅና መቆም  ይችላል።
4          «ሊደመጥ የማይገባውን  ትምክሕትም አንጸባራቂ ነው።» «ድመት መንኩሳ አመሏን አትረሳ» እንዲሉ፣ የ«ፍኖተ-ምክራሲ» ዝግጅት ክፍል ዛሬም ያ ሰዎችን ለማጥፋት የተለያዩ የማጥላያ ስሞች ይጠቀም የነበረው የግራ ዘመሙ የዓለም አመለካከት ካከተመ ከ፳፫(ሃያ ሦሥት) ዓመታት በኋላ፣ ለዐማራው ድምፅ ለመሆን የሚጥሩ ሰዎችን በትምክህተኛነት ሊከስ፣ ሊወነጅል ይፈልጋል። የተበላ ዕቁብ ነው እንላቸዋለን። ከዚህ ላይ አንባቢ ልብ እንዲልልን የምንፈልገው ጉዳይ አለ፦ የትግሬ-ወያኔም ዐማራውን «ትምክህተኛ፣ ነፍጠኛ፣ ጨቋኝ ገዥ መደብ፣ የትግራይ ሕዝብ ደመኛ ጠላት፣ የብሔር-ብሔረሰቦች ጠላት፣ ወዘተርፈ» እያለ በታሪክ በኢትዮጵያ ውስጥ ለተፈጠሩ ችግሮች ሁሉ ዐማራውን ተጠያቂ ያደርጋል። የዚህ አስተሣሰብ ቆስቋሽ የነበረው ደግሞ ዋለልኝ መኮንን የተባለው «የዐማራ ጠላት የሆነ ዐማራ» ነው። የዋለልኝ መኮንን የነፍስ አባት ደግሞ ከ፸(ሰባ) ዓመታት በፊት «ኢትዮጵያ፥ የባሩድ በርሚል (Abyssinia: The Powder Barrel)» በሚል ርዕስ ፀረ-ዐማራ እና ፀረ-ኢትዮጵያ መርዝ አሣትሞ ያሠራጨው አፍቃሬ-ናዚ ወፋሽስት-ጣሊያን የነበረው ሮማን ፕሮቻዝካ የተባለው የኦስትሪያ ዜጋ መሆኑ ይታወቃል። በዚህ ረገድ ከ፲፱፻፶`ዎቹ ጀምሮ በኢትዮጵያ ፖለቲካ ቀንደኛው አንቀሣቃሽ የሆነው እና ግራ-ዘመም ርዕዮተ-ዓለም የሚያራምደው ትውልድ፣ ዛሬም ኮሚኒዝም ተንኮታኩቶ ከወደቀ ከ፳፫(ሃያ ሦሥት) ዓመታት በኋላ ከዚሁ ፀረ-ዐማራ እና ፀረ-ኢትዮጵያ አመለካከት ያልጠራ መሆኑ ሊሠመርበት ይገባል።
ከዚህ የምንረዳው መሠረታዊ ሃቅ ቢኖር፣ የትግሬ-ወያኔ ኢትዮጵያን በነገድ እና በጎሣ ከፋፍሎ የማጥፋትን ተልዕኮ የወረሰው ከዚሁ ግራ-ዘመም የፖለቲካ እንቅስቃሴ መሆኑን ነው። አገሪቱ እና የዐማራ ነገድ ተወላጆችንም አሁን ላሉበት አጠቃላይ ችግር የዳረጋቸው የግራ-ዘመሙ የፖለቲካ ትውልድ በኢትዮጵያዊነት እና በዐማራው ላይ የዘሩት የጥፋት ዘር መሆኑን የአሁኑ ወጣት ትውልድ ሊገነዘብ ይገባል። ከግራ-ዘመሙ የፖለቲካ ትውልድ አባሎች መካከል የተወሰኑት ለሻዕቢያ ኤርትራን የማስገንጠል ዓላማ ዕውቅና ሰጥተው፣ ኢትዮጵያውያን በየጎሣቸው እና ነገዶቻቸው እንዲከፋፈሉ ታግለዋል። ስለዚህ በኢትዮጵያውያን መካከል ልዩነቶችን ጥላቻን ሲያራቡ የኖሩ ግለሰቦች እና የፖለቲካ ድርጅቶች እንደ «ፍኖተ-ሞክራሲ» ባሉ «በሬ-ወለደ» ባይ ልሣኖቻቸው አማካይነት «ለኢትዮጵያ ሕዝብ አንድነት እቆማለሁ፤ ለሕዝብ ልዕልና ድምፅ እሆናለሁ የሚሉበት የሞራል ብቃት የላቸውም። 
5          «ሕዝባችን ሰው አይበላም፤ ይህን ውሸት ማሰራጨት ኢትዮጵያ ላይ መዝመት ነው።» በመጀመሪያ ደረጃ ሞረሽ-ወገኔ ያሠራጨው መረጃ ሐሰት መሆኑን በተጨባጭ መረጃ ተመርኩዞ ለአንባቢ እና አድማጭ ሳያረጋግጡ «ውሸት ነው» ማለት ተገቢ አይደለም። ለመሆኑ የ«ፍኖተ-ሞክራሲ» ዝግጅት ክፍል በመሬት ያለውን ሃቅ ለማጣራት ምን ሙከራ አድርገዋል? ወይስ ሰው-አልባ የስለላ አውሮፕላን (drone) ወደሥፍራው ልከው አረጋግጠዋል? ካቀረቡልን ሐተታ ግን ይህንን ሃቅ ሊያስተባብሉበት የሚችሉበት አንድም መረጃ የለም። አልያ ሃቁን ለማስተባበል ወያኔያዊ ሥራ መሥራት ይኖርባቸዋል። ስለሆነም ድርጊቱ የተፈጸመ ስለሆነ ሞረሽ-ወገኔ ትላንትም ሆነ ዛሬ ያለው አቋም አንድ ነው፦ በመተከል ዞን መልካን እና አይጋሊ-ሞዛምቢክ ቀበሌዎች ጉምዞች ዐማሮችን ገድለው ሥጋቸውን በልተውታል። ደረቁ ሃቅ ይህ ነው!
6          «የሚከሰሱት አሕዛብ ናቸው፣ ሃይማኖት የላቸውም፣ ለዚህም ነው ሰው የሚበሉ አውሬዎች ናቸው ብሎ ልፈፋም አማራ ነን ባዮች ምንኛ ኋላቀር የሀገርና ሰላምና የአንድነት መሠረት አውዳሚ እንደሆኑ ያሳያል።» ይህ አባባል አንድ ነገር ያስታውሰናል፦ አበው «ከሣሽ ተከሣሽ የሚለውን ቢያውቅ ኖሮ፣ ክስ አይመሠርትም ነበር፣» ይላሉ። ሞረሽ ወገኔ የዐማራ ድርጅት «ጉምዞች አሕዛብ ናቸው፣ ኃይማኖት የላቸውም፣ ስለዚህም ሰው የሚበሉ አውሬዎች ናቸው» አላም። ከመግለጫችን ውስጥ ይህን የሚያስረዳ አንዳችም አረፍተነገር የለም። «በመልካን እና አይጋሊ-ሞዛምቢክ ቀበሌዎች ጉምዞች ዐማሮችን አርደው በሏቸው፤ ጉበትና ኩላሊታቸውን በሚጥሚጣ አጣፍጠው በሉት፤» ብለናል። ይህ ደግሞ የተፈጸመውን ድርጊት አመልካች ዕውነት፣ የማያወላውል ደረቅ ሃቅ ነው።
የፍኖተ-ሞክራሲ ዝግጅት ክፍል፣ እኛ ጉምዞችን በጅምላ ፈርጀን ያላልነውን «አሉ» ብሎ ሲወነጅለን አንድ ታሪካዊ ክስተት እንድናስታውስ አደረጉን። ቀድሞ የኢሕአፓ አባል፣ ከዚያም የኢሕዴን/ብአዴን መሥራች እና ሊቀመንበር የነበረው እና አሁን ደግሞ የፕሮቴስታንት ዕምነት ሰባኪ የሆነው ጌታቸው ማሞ (ታምራት ላይኔ) በ፲፱፻፹፬ ዓ.ም. ጅጅጋ ወርዶ ነበር። ታምራት ላይኔ የተናገረው ንግግር፦ «እነዚህን ሽርጣም ሶማሌ የሚሏችሁን ዐማሮች አሁን በሏቸው» ሲላቸው፣ ብልሆቹ የሶማሌ አዛውንት «ወላሂ አሁን ገና አንተ ሰደብከን፣ እነርሱ በየጓዳቸው ያሙን እንደሆን እንጂ፣ እንዲህ ብለው በአደባባይ ሲሰድቡን አልሰማንም፤» በማለት ነበር ቅንድቡን ያሉት። በትይዩ ሲታይ የጉምዝ ነገድ ተወላጆችን በጅምላ «አሕዛብ፣ ኃይማኖት የሌላቸው፣ ሰው የሚበሉ አውሬዎች» ብሎ የዘለፋቸው የ«ፍኖተ-ሞክራሲ» ሬድዮ ጣቢያ ነው። በዚህ ረገድ ሊታወቅ የሚገባው ጉዳይ ሞረሽ-ወገኔ የማንኛውንም ነገድ ወይም ጎሣ አባሎችን በጅምላ አይወነጅልም፣ የድርጅቱ መርሆም አይደለም።
አልፎም ሞረሽ-ወገኔን በኢትዮጵያ አንድነት «አውዳሚነት» መወንጀል የ«ፍኖተ-ሞክራሲ» ሬዮ ባለቤቶችን ትክክለኛ ማንነት በትልቁ ያሣብቅባቸዋል። ለመሆኑ ወያኔ በሕገ-አራዊቱ አንቀፅ ፴፱(ሰላሣ ዘጠኝ) ያፀደቀውን «የብሔር-ብሔረሰቦች መብት እስከመገንጠል» የሚለውን አገር-አፍራሽ አጀንዳ አውቀው እና ፈቅደው ለመጀመሪያ ጊዜ የድርጅታቸው መርህ አድርገው የተነሱ እነማን ነበሩ? ከዚያም አልፎ ይህን አጀንዳ ተግባራዊ ለማድረግ በመቶ ሺህዎች የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያንን አደራጅቶ፣ ሠራዊት አሰልጥኖ ጫካ ገበቶ በኢትዮጵያውያን ልጆች ንጹህ ደም የታጠበውማን ሆነና ነው?  ስለዚህ «አንድነታችን ተናጋ፤ የአገሪቱ አንድነት መሠረት የሆነው ዐማራ የትግሬ-ወያኔ እና አጋሮቹ የዘር ማጥፋት እና የዘር ማጽዳት ወንጀል ፈጸሙበት፤ ከዚህም አልፈው ጉምዞችን አደራጅተው አስፈጁት፣ ሥጋውንም አስበሉት» እያለ የሚጮኸውን ሞረሽ-ወገኔን በአገር አፍራሽነት መክሰስ ምን ይሉታል? ለነገሩ «መበደል መበደል ወታደር በድሏል፣ መካሱን ግን ባላገር (ገበሬ) ይካስ፤» ዓይነት አባባል እንደሆነ ሁሉም ኢትዮጵያዊ በጥልቀት ያውቀዋል።
7          « የጉምዝ ቤንሻንጉልን ሕዝብ በጸያፍ ውንጀላ የከሰሱ ሁሉ ሕዝብን ይቅርታ መጠየቅ አለባቸው፤»  ልብ በሉ ወገኖች፣ የ«ፍኖተ-ሞክራሲ» ሬዮ ዝግጅት ክፍል በአሠቃቂ እና አረመኔያዊ ሁኔታ ለተገደሉት እና ሥጋቸውን ለተበሉት፣ እንዲሁም ኃብት ንብረታቸውን ተቀምተው ለተፈናቀሉት ዐማሮች አላዘነም። ይባስ ብሎ ጥብቅና የቆመው ለወያኔ እጀታ ሆነው ዐማራውን ለገደሉት እና ሥጋውን ለበሉት የጉምዝ ሰዎች ሆነ። አልፎ ተርፎም «እንዴት ጉምዞች እንዲህ ይባላሉ?» ብሎ እኛን ሞረሽ-ወገኔን ይቅርታ እንድንጠይቅ ያስጠነቅቃል። ይቅርታ የሚጠይቅ እኮ ጥፋት ያጠፋ፣ የዋሸ፣ የሰረቀ፣ የገደለ እንጂ እውነቱን የተናገረ አይደለም። ስለዚህ ሞረሽ-ወገኔ የዐማራ ድርጅት ባወጣው መግለጫ አጥፊዎቹን የጉምዝ ነገድ ተወላጆች ይቅርታ አይጠይቅም፤ ይፋረዳቸዋል እንጂ!
8          «ኢትዮጵያን ሲጎዳ የቆየውን ትምክህት በማናፈሳቸውም በሕዝብ መከፋፈል ልክ እንደ ወያኔ ሊከሰሱ ይገባቸዋል።» ይላል ጉዱ አያልቅበት «ፍኖተ-ሞክራሲ» የሬዮ ጣቢያ! ልብ በሉ ዐማራውን ትምክህተኛ እያለ በየሜዳው የሚያርደው እና የሚያሣርደው የትግሬ-ወያኔ አገዛዝ ነው። ይህ በላኤ-ሰብ የአገዛዝ ሥርዓት በኢትዮጵያ ውስጥ ከቤተክህነት እስከ ቤተመንግሥት፣ ከጽዳት ሠራተኛ እስከ ሚኒስቴር፣ ከተራ ወታደር እስከ ሙሉ ጄኔራል ያሉትን የሥልጣን ሥፍራዎች እና የኃላፊነት ደረጃዎች በሙሉ በትግራይ ተወላጆች አስይዟል። የሥላቁ ብዛት የትግሬ-ወያኔ ዘወትር ዐማራውን «ትምክህተኛ» ይለዋል። አዎ! ዐማራው በባህሉ፣ በቋንቋው፣ በኢትዮጵያዊነቱ፣ በስፋት አመለካከቱ፣ በእንግዳ ተቀባይነቱ፣ በአብሮነት ስሜቱ፣ በኃይማኖተኝነቱ፣ በይሉኝታው፣ ወዘተርፈ አብዝቶ ይመካል። መመካት በራስ የመተማመን፣ ራስን የመሆን ምልክት ነው። ይህ የሌለው የትግሬ-ወያኔ አይነቱ ንፉግ እና ጠባብ፣ ከፋፋይ እና አገርሻጭ፣ የእፉኝት ልጅ ባንዳ በምኑ ይመካል? እናም የ«ፍኖተ-ሞክራሲ» ሬዮ የዝግጅት ክፍል ምኑ ያስነውራል ብሎ ይሆን «ኢትዮጵያን ሲጎዳ የቆየውን ትምክህት በማናፈሳቸው» እያለ ሞረሽ-ወገኔን የሚከስሰው? መቼም «በምኒልክ ጊዜ የደነቆረ በምኒልክ አምላክ እያለ ይኖራል» እንደሚሉት በግራው ርዕዮተዓለም የመደብ ጠላት ለመፍጠር ሲጠቀሙበት የኖሩትን የዝባዝንኬ ቃል በመጠቀም የሞረሽ-ወገኔን አባሎች እና ደጋፊዎች ለማሸማቀቅ ከጅለዋል። የኢትዮጵያን ሕዝብ በመከፋፈል የሚጠየቅ ካለ በመጀመሪያ ተጠያቂዎቹ «ፍኖተ-ሞክራሲን» በባለቤትነት የሚያስተዳድረው አካል መሪዎች ናቸው። ከትግሬ-ወያኔ በፊት «የብሔር፣ ብሔረሰቦች መብት እስከመገንጠል» የሚለውን መርሆ በማራመድ የኢትዮጵያን ሕዝብ በነገድ እና በጎሣ ተከፋፍሎ እንዲባላ ትልሙን ተልመዋል፤ ኤርትራ እንድትገነጠልም ታግለዋል። የትግሬ-ወያኔም ያደረገው ይኸንኑ ነው። ስለዚህ የእነርሱ ችግር «እኔ ሳላደርገው ተቀደምኩ» ቁጭት እንጂ፣ በአፈጻጸም ደረጃ ከታዬ ከትግሬ-ወያኔ በባሰ በአገር ላይ ጦስ ያመጡ እንደነበረ ጥርጥር የለውም። ደግነቱ «እባብን የልቡን አይቶ እግር ነሣው» እንዲሉ ሆነና ምኒልክ ቤተመንግሥት ለመግባት የሕልም ሩጫ እንደሮጡ አረጁ።
ከዚህ በላይ በዝርዝር ለማሣዬት እንደተሞከረው፣ የ«ፍኖተ-ሞክራሲ» ሬዮ ዝግጅት ክፍል በሞረሽ ወገኔ የዐማራ ድርጅት ላይ የሠነዘረው ክስ መሠረተ-ቢስ የአሉባልታ ወሬ ነው። ለወደፊቱም የ«ፍኖተ-ዲሞክራሲ» ሬድዮም ሆነ ሌሎች በ«ኢትዮጵያዊነት» ስም የሚንቀሣቀሱ የብዙሃን መገናኛ ተቋሞች በዐማራው ተወላጆች ላይ ጥቁር ነጥብ የሚጥል እንዲህ ዓይነት የአሉባልታ ወሬ ከማሠራጨት ይልቅ በሃቅ ላይ የተመሠረተ እና ከጭፍን ወገናዊነት የራቀ ሚዛናዊ ዘገባ እንዲያቀርቡ አደራ እንላለን።
ዐማራን ከፈፅሞ ጥፋት እንታደጋለን!
ፈለገ-አሥራት የትውልዳችን ቃልኪዳን ነው!
ኢትዮጵያ በታማኝ እና ቆራጥ ልጆቿ መስዋዕትነት ለዘለዓለም ፀንታ ትኖራለች!

No comments:

Post a Comment

wanted officials