Which one you first choose? በቅድሚያ የሚፈልጉት

Friday, September 11, 2015

የህዝብ አመጽ ዙሪያውን እየተቀጣጠለ ነው! ኮማንደር እንዳርጋቸው አለሙና ሌሎችን ባለስልጣናት ስብሰባ ላይ ነበሩ

የህዝብ አመጽ ዙሪያውን እየተቀጣጠለ ነው! ኮማንደር እንዳርጋቸው አለሙና ሌሎችን ባለስልጣናት ስብሰባ ላይ ነበሩ
==================================
በአማራ ክልል ሰሜን ጎንደር ዞን በሚገኙ ሶስት ወረዳዎች የሚኖሩ አስተዳዳሪዎችና የህዝብ ተወካዮች መሬትን በተመለከተ ስብሰባ ማካሄዳቸው ታወቀ።
በሰሜን ጎንደር ዞን ወረዳዎች መተማ ሳንጃና ጭልጋ የሚገኙ አስተዳዳሪዎች የሚሊሻ ኮማንደሮችና ከ40 በላይ የሚሆኑ የህዝብ ተወካዮች በተገኙበት ነሓሴ 24 / 2007 ዓ/ም ስብሰባ ማካሄዳቸውን የገለፀው ሪፖርቱ የስብሰባው ዋና አጀንዳም ከኢህኣዴግ የምናገኘው ለውጥ የለም፤ መሬታችን ራሳችንን ማስተዳደር አለብን? መሬታችን አሳልፈን አንሰጥም? የሚሉና ሌሎችን እንደነበሩ ታውቋል።
በስብሰባው ከተሳተፉ የስርዓቱ ወገኖች ከሆኑ ስሞችን ለመጥቀስ ያህል የሳንጃ ወረዳ ኮማንደር እንዳርጋቸው አለሙና ሌሎችን የሚገኙባቸው እንደተሳተፉ ሲገልፅ በዚህ ሁኔታ የሰጉ አንዳአንድ የስርኣቱ ካድሬዎች ደግሞ “በዚህ ስብሰባ ፀረ-መንግስት ተቃውሞ የሚያነሱ ያሉ የአርበኞች ተላላኪዎች ሰርጎ ስለ ገቡ ነው” ሲሉ እንደተሰሙና በዛን ቀን ደግሞ በመቐለ ከተማ የኢህአዴግ ጉባኤ እየተካሄደ እንደነበር የተገኘው መረጃ ጨምሮ አስታውቋል።
====================================
በህወሃት ስርዓት ከፍተኛው ተጠቂ ገበሬው ነው! ትመስክር አዲያቦ!
==================================
በሸራሮና ታሕታይ አድያቦ የሚገኙ ገበሬዎች አመት ሙሉ ደክመው የዘሩትን ማሽላና ሰሊጥ የስርአቱ ተላላኪዎች በከብት እንዳስበሉትና እንዳስረገጡት ተገለፀ።
ከአከባቢው የተገኘ መረጃ እንዳስታወቀው በትግራይ ሰሜናዊ ምዕራብ ዞን ሸራሮ ወረዳና ትሕታይ አድያቦ በሚገኝ የእርሻ መሬት የተዘራ ሰሊጥና ማሽላ በአስተዳዳሪዎቹ በተላኩት የስርአቱ ፖሊሶች ይሄ መሬት “ለከብት መኖ የተዘጋጀ እያለ ከመንግስት ፍቃድ ውጪ ለምን ትዘራላችሁ” በሚል ትክክል ያልሆነ ምክንያት ነሓሴ 18/2007 ዓ/ም እንስሳትን በማስገባት ሰብሎችን እንዳበሉትና እንዳበላሹት ለማወቅ ተችሏል።
ሰብሎቻቸው የተበላሸባቸው ገበሬዎች ደግሞ ላጋጠማቸው ሰቆቃ ለሚመለከታቸው የአከባቢው ሃፊዎች አብየቱታቸውን ቢያቀርቡም ሰሚ ጀሮ ስላጡ “ይህ ስርአት ለልማት ሳይሆን ለጥፋት የቆመ ስርአት ነው” በማለት በስርአቱ ላይ ያላቸውን ጥላቻ በመግልፅ ላይ መሆናቸው መረጃው በመጨረሻ ገልጿል።
====================================
የ አባይ ወልዱ ሚስት ወ/ሮ ትርፉ ኪዳነማርያም በሙስና ተከሰው ከስልጣን ልቀቁ ቢባሉም እስካሁን ስልጣናቸውን መንካት አልተቻለም
===============================
የትግራይ ክልል ሲቪል ሰርቪስ ሃላፊና የክልሉ ዳኞች ሰብሳቢ የሆኑት ወ/ሮ ትርፉ ኪዳነማሪያም በሙስና ስለተገመገሙ ከሃላፊነታቸው መውረድ አለባቸው ሲሉ የህወሓት ጉባኤተኞች የወሰኑትን ውሳኔ እስከ አሁን ድረስ እንዳልተተገበረ ተገለፀ።
እንደ ምንጮቻችን መረጃ መሰረት የአባይ ወልዱ ሚስት የሆኑት ወ/ሮ ትርፉ ኪዳነማሪያም ላለፉት አመታት የትግራይ ክልል የሲቪል ሰርቪስ ሃላፊ ሆነው በሰሩበት ጊዜ በመስሪያ ቤቱ አዳዲስ ለውጦች ባለማምጣታቸው የተነሳና ጊዜው ያለፈው አስራር በየጽህፈት ቤቱ በነበረበት መሰረት እንዲቀጥል በማድረጋቸው እንደተነቀፉና ሌሎች በፍትህ ቢሮ በተደረገ ግምገማ በከባድ ሙስና የሀገርና የህዝብ ሃብት በማጠፋፋት ስለተገመገሙ በህወሓት ጉባኤተኞች ከሃላፊነታቸው እንዲወርዱ ወስኖ እያለ ባለሉበት የስልጣን እርከን በመቀጠል ላይ እንዳሉ ታወቀ።
አግባብነት የሌለውን የትግራይ ክልል የአስተዳደር አሰራር የታዘቡት አገር ወዳድ የመንግስት መስሪያ ቤት ሃላፊዎችና ምሁራን ወ/ሮ ትርፉ ቀድሞም የሲቪል ሰርቪስ ሃላፊ ሆኖው የተመደቡበት ምክንያት በአቅም በልጠው ሳይሆን የአባይ ወልዱ ሚስት በመሆናቸው ነው። አሁንም በፈፀሙት ጥፋት ከሃላፊነታቸው ተወግደው ጉዳያቸው በህግ ፊት መጣራት እየተገባው በሃላፊነታቸው መቀጠላቸው የስርአቱን አመጣጥ የሚያመለክት እንደሆነ እየገለፁ እንዳሉ ለማወቅ ተችሏል

No comments:

Post a Comment

wanted officials