Which one you first choose? በቅድሚያ የሚፈልጉት

Sunday, September 13, 2015

የመንግስት ልሳን ፋና ራድዮ ሞላ አስገዶም ከሱዳን ኢትዮጵያ ገባ አለ * በፎቶ የታዩት 25 አይሞሉም

ከአቤ ቶኪቻው

mola asgedom

 ሞላ አስገዶም የተባሉት የትህዴን ሸማቂ ቡድን መሬ፤ ዛሬ ኢትዮጵያ መግባታቸውን ራዲዮ ፋና ዘግቧል። ራዲዮ ፋና እንዳለን ሰውዬው ወደ ሀገር ቤት የገቡት ሰባት መቶ የሚደርሱ ወታደሮቻቸውን ይዘው ነው። እርግጥ እኛ የደረሰን የፎቶ እና የሰው ማስረጃ የሚያሳየን የፋና ምንጮች ቁጥር እንደማይችሉ ነው። ሰውዬውን የተከተሏቸው ወይም ከመንገዱ ተርፈው ሱዳን ድንበር የደረሱት ታጣቂዎች ሰላሳ ከደረሱ ብዙ ናቸው። ትላንት እና ከትላንት በስተያ የወጡ የመንግስት የስጋ ዘመድ የሆኑ ድረ ገጾች አቶ ሞላ አስገዶምን ‘ድሮውንም ስለላ ላይ ነበሩ… ከኢትዮጵያ ደህንነት እና መረጃ ክፍል ጋር ሲሰሩ ነበር…’ ብለውናል። ሰውዬው እውነትም ሰላይ ከነበሩ… እስከዛሬ የሰለሉት ነገር ቢኖር የገዛ ደህሚታቸውን ብቻ ነበር… አሁን አራት ጠመንጃ ያነገቱ ቡድኖች ሲጣመሩ እና ምክትል ሊቀመንበር ሲደረጉ ጥለው መውጣታቸው ዋና የስለላ አዝመራውን ትተውት እንደወጡ ሰነፍ ሰላይ ነው የሚቆጠሩት፤ (እና ቅጣት ይጠብቃቸዋል… ብለን እናላግጣለን!) ራዲዮ ፋና እንዳለን ደግሞ ሰውዬው ‘ሀገሪቱን ለማተራመስ የሽብር ስራን ሲሰሩ የሰነበቱ’ ከሆነ… የመንግስትን አቀባበል አይተን የምናነሳው ጥያቄ ይኖረናል፤ አቶ ሌንጮ ለታ በሰላማዊ መንገድ አዲሳባ ሲገቡ ”ተመለሱ…” ብሎ የመለሳቸው መንግስት ዛሬ እነ ሞላ አስገዶምን ከነመሳሪያቸው እንኳን ደህና መጣችሁ ብሎ ከተቀበላቸው ያኔ በደንብ የምንጠያየቀው ይኖረናል::


 የፋና ዜና ዘገባ እንደወረደ:- አዲስ አበባ፣ መስከረም 2፣ 2008 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ራሱን የትግራይ ህዝብ ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ /ደህሚት/ በማለት የሚጠራው እና በኤርትራ ውስጥ ሲንቀሳቀስ የነበረው የጦር ክፋይ ትናንት ወደ ሀገሩ ገባ። ጦሩ የንቅናቄው መሪ በሆነው ሞላ አስገዶም እየተመራ ወደ ሀገር ውስጥ የገባው። ቁጥራቸው ከ700 በላይ እንደሚሆኑ የተገመተው የደህሚት ጦር ከነ ሙሉ ትጥቁ ከሱዳን ወደ ኢትዮጵያ በሁመራ እና በመተማ አድርጎ ሰላማዊ በሆነ መንገድ መምጣቱን የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ምንጮች ተናግረዋል። ጦሩ ወደ ኢትዮጵያ ሲገባ በመንገድ ላይ ትንኮሳ ሊፈጥሩበት ጥረት ያደረጉ የሻዕቢያ ሀይሎችን እየደመሰሰ ነው ወደ እናት ሀገሩ የገባው። ጦሩ በሻዕቢያ እና ግንቦት 7 አስተባባሪነት በኢትዮጵያ ላይ የተለያዩ አደጋዎችን ለማድረስ ሲንቀሳቀስ መቆየቱ ይታወሳል። ከዚህ ጋር በተያያዘ መንግስት መግለጫ ይሰጣል ተብሎ ይጠበቃል

No comments:

Post a Comment

wanted officials