የባህር ዳር ጨርቃጨርቅ ፋብሪካ ሰራተኞች የስራ ማቆም አድማ ማድረጋቸው ተገለፀ
የባህርዳር ጨርቃጨርቅ ፋብሪካ ሰራተኞች የስራ ማቆም አድማ ማድረጋቸውን ሰራተኞቹ ለነገረ ኢትዮጵያ ገልፀዋል፡፡ በየዓመቱ ሰኔ 20 በጀት ከተሰራ በኋላ ከትርፉ ድጎማ እንዲያገኙ ከፋብሪካው ጋር ስምምነት እንዳላቸው የገለፁት የፋብሪካው ሰራተኞች ፋብሪካው ትርፋማ ቢሆንም ድጎማቸው ስላልተሰጣቸው በዛሬው (ነሃሴ 25/2007 ዓ.ም) ዕለት የስራ ማቆም አድማ እንዳደረጉ ለነገረ ኢትዮጵያ ገልጸዋል፡፡ አንድ የፋብሪካው ሰራተኛ ለነገረ ኢትዮጵያ እንደገለፁት በዘንድሮው ዓመት ፋብሪካው ከፍተኛ ትርፍ ቢያገኝም ድጎማውን ላለመስጠት ከስረናል ማለታቸውን ገልጸዋል፡፡ ‹‹በዚህ ዓመት ከፍተኛ ሽያጭ ነው ያለው፡፡ ወደ ውጭ የተላከውን እናውቀዋለን፡፡ ምርቱንም እናውቀዋለን፡፡ ይህን እያወቅን ነው ከስረናል የሚሉን›› ሲል ለነገረ ኢትዮጵያ ገልጾአል፡፡
ፋብሪካው መክሰሩን በመግለፅ ድጎማውን አልከፍልም እንዳለ የገለፁት ሰራተኞቹ፣ ፋብሪካው ከስሬያለሁ ካለም ኦዲት እንዲደረግ ቢጠይቁም ፈቃደኛ አለመሆኑን ገልጸዋል፡፡ በዚህም ምክንያት ‹‹ተዘርፈናል!›› እስከማለት የደረሱ ሰራተኞች መኖራቸውን ገልጸዋል፡፡ የባህርዳር ጨርቃጨርቅ ፋብሪካ ማኔጅመንት ለሳምንት ያህል ሰራተኛውን ለማሳመን ቢጥሩም ሰራተኛው ‹‹ካልተከፈለን፣ ወይንም ኦዲት ተደርጎ ካላወቅን›› በማለታቸው ስኬታማ መሆን እንዳልቻሉ ተገልጾአል፡፡ ችግሩም ተባብሶም በዛሬው ዕለት ሰራተኛው የስራ ማቆም አድማ እንዳደረገ የፋብሪካው ሰራተኞች ለነገረ ኢትዮጵያ ገልጸዋል፡፡ ‹‹በዛሬው ዕለት ስራ የለም፡፡ ስራ አቁመናል፡፡ የገቡ ሰራተኞች ቢኖሩም ቁጭ ከማለት ውጭ ስራ እየሰሩ አይደለም፡፡ አብዛኛው ሰራተኛ ዝም ብሎ ቁጭ ብሏል›› ሲሉ የፋብሪካው ሰራተኛ ለነገረ ኢትዮጵያ ገልጸዋል፡፡

No comments:
Post a Comment