ለመሆኑ የዘመን አቆጣጠራችንን ስሌት የምናውቀው እንዴት እንደሆነ ያውቃሉ?
የዛሬ መቶ አመት እንቁጣጣሽ ምን ዕለት እንደሚውልና ዘመኑ ምን እንደሆነ ማወቅ የምንችለው እንዴት ነው?
በተጨማሪም የኛ ዘመን ኣቆኦጣጠር ከሌላው የሚለይበትን ንጽጽር ዘአብርሃም ብሎግ ከምንጩ ያገኘውን እንዲህ አቅርቦታል።
በቅድሚያ የዘመን ኣቆጣጠር ቀማሪ በሆነችው ቤተክርስቲያን መሰረት ማቴዎስ፤ማርቆስ፤ሉቃስ እና ዮሐንስ ዘመኑን በየአራት አመቱ በወንበራቸው እየተቀያየሩ እንደሚጠሩበት እናስታውስ።። ሰለሆነም
አዲሱ ዓመት በየትኛው ወንጌላዊ እንደሚሰየም ለማወቅ
በመጀመርያ ከክርስቶስ ልደት በፊት 5500 ዘመንና ከክርስቶስ ልደት በኋላ ለማስላት የምንፈልገው ዓመተ ምህረትን እንደምራለን።ከዛም ድምሩን ለ4 እናካፍላለን።ወይም ሁለተኛው ቀላሉ መንገድ የምንፈልገውን ዓመተ ምህረትን ብቻ ለ4 ኣካፍለን 1 ከቀረ ዘመነ ማቴዎስ፤ 2 ከቀረ ዘመነ ማርቆስ፤ 3 ከተረፈ ዘመነ ሉቃስ፤ 0 ከሆነ ዘመነ ዮሐንስ ይባላል።
አስረጅ 2008 ዘመነ ማን እንደሚባል
5500+2008=7508 ይሆናል እሱን ደግሞ ለ4 እናካፍለዋለን 7508 ፥4=1877 ይደረሳል ቀሪ 0 ይሆናል።
ወይም በሁለተኛው ቀላሉ መንገድ የምንፈልገውን ዓመተ ምህረት ብቻ ለ4 ኣካፍለን 2008 ፥4=502 ቀሪ 0 ይሆናል።
ስለዚህ ከአራቱ ወንጌላውያን የዚህ አመት ወንበር 2008 ዘመነ ዮሐንስ ነው።
የ ዓመቱ መስከረም አንድ ምን ዕለት እንደሚውል ለማወቅ
ቅድመልደተ ክርስቶስ ያለውን 5500 እና የምንፈልገውን ዓመተ ምህረት ድምር እና ከዛም ድምሩን ለአራት አካፍለን የምናገኘውን ድርሻ እንደምራቸዋለን። የድምሩን ውጤት ለሰባት ስናካፍል 1 ከተረፈ ማክሰኞ፤ 2 ከተረፈ ረቡዕ፤ 3 ከተረፈ ሐሙስ፤ 4 ከተረፈ ዓርብ፤ 5 ከተረፈ ቅዳሜ፤ 6 ከተረፈ እሁድ ፤ 0 ከሆነ ሰኞ ዕለት መስከረም አንድ ቀን ይሆናል ።
አስረጅ የ2008 ዓ\ም መስከረም አንድ ምን ዕለት እንደሚውል
ይህንን ለማወቅ ደግሞ 5500+2008=7508
ይህንን ለማወቅ ደግሞ 5500+2008=7508
ከዛም 7508፥4=1877 ዕለቱን ለማወቅ 7508+1877=9385 ይህን ደግሞ ለ7 እናካፍለዋለን 9385፥7=1340 ደርሶ 5 ይተርፋል ።
ካለፉት አመታት የአውደ አመቱ መባቻ መቼ እንደዋሉ ወይም የመጪዎቹን አመታት ወንበሮች ለምሳሌ 2009 ዓም ዘመኑ ማቴዎስ ዕለቱ እሁድ እንደሚሆን አስልታችሁ ድረሱበት። በዚህ አይነት የመቶ አመት ካለንደር መስራት ቻላቹ ማለት አይደል። ቀጥሉ 3008 ዓም/ ሚሊኒየም መቼ ይገባል?ዕለቱስ
ዘአብርሃም ብሎግ ከምንጩ ያገኘውን እንዳጋራችሁ እናንተም ለመላው ኢትዮጵያውያን የሃገራችን የዘመን አቆጣጠር እንዴት እንደሚሰላ ያጋሩ።እኛ ኩሩ ባህል ና የዘመን አቆጣጠር ያለን ነን ስለዚህ ሞክሩት!
የኢትዮጵያ ዘመን አቆኦጣጠር ከሌላው የሚለይበት ንጽጽር
መልካም አዲስ አመት!
No comments:
Post a Comment