Which one you first choose? በቅድሚያ የሚፈልጉት

Monday, September 28, 2015

በሰበታ አይነውር ተማሪዎች በፓሊስ ተደበደቡ


 sebeta 1
ማየት የተሳናቸው ተማሪዎች መስከረም 11 ቀን 2008 ዓም ከመብት ጋር የተያያዙ ጥያቄዎች በባንሳታቸው በፓሊሶች ክፉና የተደበደቡ ሲሆን የተማሪዎችን ተወካዮች ጨምሮ 17 ማየት የተሳናቸው ተማሪዎች ተይዘው ታስረዋል።
ስማቸው እንዳይገለጽ የፈለጉ ተማሪዎች ሌኢሳት እንደገለጹት ተማሪዎች የማደሪያ ክፍል በአንድ ግቢ ውስጥ ለሚገኘው ኮሌጅ በመስጠቱ ተማሪዎች እንዲመለስላቸው ሲጠይቁ ይፌደራል ፓሊስ በፍጥነት ገብቶ አይነስውራን ተማሪዎች ደብድባል ።
ተማሪዎቹ የመኝታ ክፍሉ እንዲመልስላቸው በተደጋጋሚ ሲጠይቁ ቢቆዩም መለስ በማጣታቸው የትምህርት ማቆም አድማ አድርገዋል።  ፓሊሶች ተማሪዎቹ ከመኝታ ክፍላቸው እንዲወጡ ትእዛዝ  ቢሰጡም ተማሪዎቹ ግን ፈቃደኛ አልሆኑም። ፓሊሶች ወደ ክፍል እየገቡ ራሳቸውን መከላከል በማይችሉ ተማሪዎች ከባድ ድብደባ የፈፀሙ ሲሆን ብዙዎቹ እጆቻቸውና እግሮቻቸው በድብደባ ብዛት ተጎድቷል ። አንድ ተማሪ እሩጠን ለማምለጥ በማንችልበት ሁኔታ ፓሊስ ጭካኔ የተሞላበት እርምጃ ወስዶብናል ብሎአል ። 17  የታሰሩት  አይነስውራን ተማሪዎች እስካሁን አልተፈቱም ትምህርት አልተጀመረም።
የፌደራል ፓሊስ እስካሁን የሰጠው ይፋዊ መግለጫ የለም።
Source/ESAT

No comments:

Post a Comment

wanted officials