Which one you first choose? በቅድሚያ የሚፈልጉት

Friday, September 18, 2015

ሞላን የተቃዋሚ ፓርቲ አመራሮች "አበጀህ የእኛ ሎጋ "አሉት፣ሞላን መርቁልኝ ይቀጥላል -= ዳዊት ሰሎሞን


ሞላን የተቃዋሚ ፓርቲ አመራሮች "አበጀህ የእኛ ሎጋ "አሉት፣ሞላን መርቁልኝ ይቀጥላል
___________________________
ሞላ አስገዶም አገር ቤት መግባቱን ተከትሎ "ጀግና፣አገር ወዳድ፣ጀነራል ወዘተ "ሲሉት የከረሙት የኢህአዴግ ሚዲያዎች ወደ ታማኝ ተቃዋሚዎች ጎራ በማለት ሞላስ ለናንተ ምንድን ነው በማለት እንደ ሞላ ተቃዋሚዎችን ሲሰልሉና በአንድም ይሁን በሌላ መንገድ ሰላማዊ ትግሉ ፈቅ እንዳይል እንቅፋት ሆነው የቆዩትን በመነጠል ጠይቀዋል።
እዚህ ዝርዝር ውስጥ እንደማገኛቸው ስጠብቃቸው ከነበሩ አንዱ ትዕግስቱ አወሉ ከፍ ባለ ድምጽ የሞላን መመለስ ለሰላማዊ ትግል እንደተከፈለ መስዋዕትነት እንደሚቆጥሩት ተናግሯል።
የመድረኩና የኢዴፓው ተወካይም ለሰላማዊ ትግል ድል መሆኑን አብስረዋል።
አሁን የሚቀሩት አንዳንድ የአዲስአባ ነዋሪዎች፣ጥቃቅንና አነስተኞች፣ልማታዊ አርቲስቶች፣የነጋዴዎች ፎረም፣የሴቶች ማህበራት፣ሊጎች ወዘተ,..ናቸው ።ኢህአዴግማ ሞላን ሳያስመርቅ በቀላሉ ገና አይፋታንም።
----------------

----------------
እኔን የገረመኝ ግንበአገሪቱ ያሉት ፓርቲዎች እነዚህ ብቻ ናቸው እንዴ? እንዴ አየለ ጫሚሶ የሉም?ልክ ነው ብዙዎቹ ምርጫ ሲቃረብ ከየጉራንጉሩ ኮት ለብሰው ብቅ የሚሉ በመሆናቸው መገኛቸው ላይታወቅ ይችላል።ግን ትዕግስቱን ያገኙ ፋናዎች ቢሮ ከፍተው የሚታገሉትን ሰማያዊዎችን እንዴት ማግኘት አቃታቸው?
ነገሩ ግልጽ ነው ፋናዎች ማን የሚፈልጉትን መልስ እንደሚሰጣቸው ስለሚያውቁ ካዛንቺስ ሩቅ ሆኖባቸዋል።የሆነስ ሆነና ሞላ በሰላማዊ ትግል ለመታገል መጣሁ አላለም ጥያቄዬ ተመልሷል እንጂ።
ኢህአዴግ አመት ሙሉ ከሞላ ሲደራደር ሰላማዊ ታጋዮችን ደግሞ ሽብርተኛ ገለመሌ እያለ ሲያስርና ሲያሳድድ ነበር።የሰላም በሮችን በመዝጋቱም የአመጽ
በሮች ተከፍተዋል።ሞላን በጥቅም ደልሎ መመለስ ጊዜያዊ ፌሽታ ይፈጥር ይሆናል እንጂ ዘላቂ መፍትሄ አይሆንም።
ኢህአዴግ እነብርሃኑ ነጋን ከሰበቁት ጦር የምር መመለስ ከፈለገም መፍትሄው በእጁ ነው።አልያ ሌሎች ብዙዎች ሞላ ተውኩት ባለው መንገድ አራት ኪሎ ለመምጣት መነሳታቸው አይቀሬ ይሆናል።

No comments:

Post a Comment

wanted officials