Which one you first choose? በቅድሚያ የሚፈልጉት

Friday, September 11, 2015

“እጄን ለምን ቆርጠው እንደወሰዱት ሁሌም ሳስበው ውስጤ በእጅጉ ያዝናል። ”

“እጄን ለምን ቆርጠው እንደወሰዱት ሁሌም ሳስበው ውስጤ በእጅጉ ያዝናል። ”
በዚህ ምስል ላይ የምትታየው የ 17 አመቷ ካቡላ ማሳንጃ የታንዛኒያ ዜጋ ሰትሆን ከወራት በፊት ከወላጅ እናቷ ጋር ቀኑን ሙሉ ደፋ ቀና ሲሉ ውለው አመሻሹ ላይ ጎናቸውን ከአልጋ ጋር ለማዋሃድ በዝግጅት ላይ ሳሉ የቤታቸው በር በሃይል ይበረገዳል። በሩን ሰብረው የገቡት ግለሰቦች በቅድሚያ “ያላችሁን ሁሉንም ገንዘብ አምጡ!” ሲሉ ቤተሰቡን ያሸብራሉ። የካቡላ እናትም በቤታቸው ውስጥ ምንም ገንዘብ እንደሌለ ነገር ግን ቤተሰቡ የሚገለገልባት አንዲት አሮጌ ባይስክል(bicycle) ሰላለች እርሷን እንዲወስዱ ፍቃደኝነታቸውን ይገልጻሉ። ይሁን እና ዘራፊዎቹ እንዲወስዷት የተሰጣቸውን ሳይክል ይተዉ እና ወጣቷ ካቡላን እንቅ በማድረግ ከወለል ላይ ያጋድሟታል። ብዙም ሳይቆዩ የቀኝ እጇን ቆርጠው ፣በላስቲክ ወስጥ በመክተት “ሌሎች ጓደኞቻችን መጥተው የተቀሩት የልጆት የሰውነት ክፍሎችን ይበልታሉ” በማለት ዝተው ከሰፈራው የሰወራሉ።
ካቡላ እንደ ሁላችን ሰብእዊ ፍጡር በትሆንም የቆዳ ቀለማችንን ኣንዲጸና የሚረዳው የመዳብ(ኮፐር) ንጥረ ነገር የሚይዘው ታይሮሲናስ (Tyrosinase enzyme )የተባለው ኢንዛየም በእርሷ ወስጥ ባለመኖሩ እና የአልቢኖ በሽተኛ ኮረዳ (Albino girl) በመሆኗ እና እርሷን መሰል ሰዎች የሰውነት ክፍሎቻቸውም በአገሬው ነዋሪዎች ዘንድ “ለሃብት ማግኛ መድሃኔት ነው ተብሎ በስፋት ሰለሚታመን” ካለፈው 2000 አኤአ ጀምሮ 76 አለቢኖዎች የአደገኛ ወንጀለኞች የአካላዊ እና የነፈስ መጥፋት ጥቃት ሰለባዎች ሆነዋል።የአልቢኖዎች እያንዳንዷ የሰውነት ክፍልም $600 ዶላር ስትሸጥ፡ አጠቃላይ ሰወነታቸው ከሆነ ደግሞ እስከ $75,000 ዶላር ኣንደሚያወጣ የተመድ የጥናት ባለሙያዎች ይናገራሉ።ከ15,000 ሰዎች አንዱ የ አልቢኖ ችግር ያለባት ታንዛኒያ የዜጎቿን መብት ለመታደግ አዲስ ሕግ በታውጣም ጥቃቱን ግን ሙሉ በሙሉ መቋቋም አለቻለችም።
አሳዛኙ ግፍ የደርሰባቸው ካቡላ እና 4 ሌሎች ኣድሜያቸው ከ 5 እስከ 15 አመት የደረሱ ታዳጊዎች ሰሞኑን ወደ አሜሪካ(ፒልስፊዲያ) ግዛት ተወሰደው ሰው ሰራሽ እጆች(ፕሮስቴቲክ )በተሳካ ሁኔታ ተገጥሞላቸው ማክሰኞ እለት ወደ አገራቸው (ታንዛኒያ)በሰላም መመለሳቸው ታወቋል። ለገንዘብ ሲሉ በአገሯ ዜጎች(ወንጀለኞች ) እጇን ያጣችው ፣ነገር ግን በማታውቃቸው አሜሪካኑ የህክምና ባለሙያዎች ሰው ሰራሽ እጅ ያገኘችው ካቡላ ማክሰኞ አለት ጆን ኤፍ ኬንዲ አውሮፕላን ጣቢያ ተገኝተው ሽኝት ሲያደርጉላት በእንባ ነበር የተለየቻቸው ። ታዲያ የአካል እና የሰነልቦና ጉዳተኛ የሆነችው ወጣቷ ካቡላም”ዛሬ ድረስ እጄን ለምን ቆርጠው እንደወሰዱት እና ከ እጄ ቁራጭ ምን ጥቅም ያገኙ ይሆን ?ብዮ ሳሰበው ልቤ በእጅጉ ያዝናል።”በማለት ቁጭቷን እና የወደፊቱንም ስጋቷን ለዜና ሰዎች ተናግራለች።
ነገርን ነገር ያነሳዋል እንዲሉ ሰሞኑን ኢትዮጵያ ውስጥም ቢሆን የተወሰነ ብሄር ተወላጆች “ በጭካኔ እንደተገደሉ፣ሰጋቸውም በሰዎች እንደተበላ እና አጥንታቸውም ለከበሮ መምቻ ውሏል “ መባሉን ሰምተናል ።ይሁን እንጂ አገዛዙም ሆነ የክልሉ ባለስልጣናት ግን የተባለውን ዜናን ለማሰተባበል ሆነ ለማመን አልሞከሩም። የትም ይሁን የት ይህ መሰሉ ጎጂ ባህል እና ኋላቀር እምነትን መዋጋት ጎሳ እና ፖሊቲካን ማእከል ማድረግ የሚያሻው አይመሰልም።

No comments:

Post a Comment

wanted officials