በ2007 ዓ.ም የተፈጸሙ 21 ዋና ዋና ክስተቶች
በ2007 ዓ.ም የተለያዩ ክንውኖች ተካሂደውበታል:: አሳዛኝ አሳፋሪና ብሔራዊ ውርደትን ያስከተለ ጭምር ነው። አዲስ ዓመት ብሄራዊ በኣል ስለሆነ እንደተለመደው 21 ጊዜ መድፍ ይተኮሳል። በኣመቱ ውስት ከተከናወኑት በርካታ ክንውኖች እናም 21ንዱን ዋና ዋና ጠቀስ አድርገን ለማለፍ ወደድን ::
ከሃብታሙ አሰፋና ታምሩ ገዳ
1. 28 ኢትዮጵያውያን በሊቢያ ታረዱ ፣ በጥይትን ተደፉ ። ይህን የኢትዮጵያውያን መታረድ ተቃውመው በሃገር ቤት ሰልፍ የወጡ ሰዎች በኢትዮጵያ መንግስት ታስረዋል:: በዓለም አቀፍ ደረጃ ኢትዮጵያውያን በያሉበት ሃገር አብረው አልቅሰዋል::
2. በደቡብ አፍሪካ ወገኖቻችን በግፍ ተገደሉ ። በእሳት ተቃጠሉ ።በሊቢያ ያሉ ወገኖች ወይታ በየመን የድረሱልን ጥሪና አገር ጥለው የወጡና ዛሬም መሔጃ አጥተው በጭንቅ ላይ ያሉ::
3.ይህን ግፍ ለመቃወም አደባባይ የወጡ በሺህ የሚቆጠሩ ኢትዮጵአውያን ታሰሩ ተደበደቡ የዛሬ ምሽት እንግዳችን አቶ ማሙሸት አማረ ሕጋዊው የመኢአድ ፕሬዝዳንት ።በዚህ ሳቢያ የታሰሩ የሰማያዊ ፣የመኢአድ አባላት በእስር ላይ ያሉ የተፈረደባቸው ጭምር አሉ በስም የማናውቃቸው አሉ
4.. በሜድትራልያን ባህር ከአንድ መንደር የተሰደዱ 11 ወጣቶች ሰመጡ ።
5.ትልቅ የፕሮፖጋንዳ ፍጆታ የሆነው ቀላል ባቡር ተመረቀ ተብሎ ምነው እንደ አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ተማሪዎች ተመርቆ ምነው ስራ አይጀምርም ተባለበት:: ባቡሩ እስካሁን ሥራም አልጀመረም::
6. ለሙስሊሙ ማህበረስብ መፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴ ላይ ፍርድ ተበየነባቸው:: የ18 ዓመት ወጣት 22 ዓመት ተፈረደበት ።
7. የመንግስት ተቃዋሚ የነበረው ወጣት ሳሙኤል አወቀ በድንጋይ ተቀጥቅጦ ተገደለ ። የአረና አመራር አባል እንዲሁ ሑመራ ላይ ቤታቸው ሊገቡ ሲሉ ተገደሉ::
8. የተጭበረበረውን ምርጫ ተከትሎ የመድረክ አባል የሆነው የኦሮሞ ሕዝብ ፌዴራሊስት ንቅናቄ(ኦፌዴን ) ምርቻ ታዛቢዎችና አባላት ጭምር ተገደሉ- በአርሲና ኮፈሌ:: እንዲሁም ታዋቂው ፖለቲከኛ አቶ በቀለ ገርባም የተፈቱት በዚሁ ዓመት ነበር:: ምርጫው ከመደረጉ አስቀድሞ መንግስት የፖለቲካውን ምህዳር በማጥበቡም ከ25 እላይ ጋዜጠኞች ወደ ጎረቤት ሃገራት ተሰደዋል::
9. ፍርድ ቤት ነፃ ያላቸው የህሊና እስረኞች ህውሃት አልፈታም አለ ። መንግስት አልፈታም ካላቸው ተቃዋሚዎች መካከልም ሃብታሙ አያሌውና አብርሃ ደስታ ይገኙበታል::
ዊንዲ ሼርማን የአሜሪካ ውጭ ጉዳይ የአፍሪካ ጉዳኢ ከሚመለከታቸው ባለስልታናት አንዷ የሆኑት ወይዘሮ አዲስ አበባ ላይ ግንቦት ሰባትን ወያኔ የሚያቀርብበትን ክስ ከማጽደቅ አልፈው የዓለም መሳቂአ የሆነው የመቶ በመቶ የተጭበረበረ ምርጫን አስቀድመው ዲሞክራሲአዊ ነው ማለታቸው ።ምርጫው 100% ተሰረቀ::
10..በምርጫው ቢያንስ አገዛዙን ለማንገዳገድ ሕዝባዊ መነቃነቅ ለመፍጠር ሰፊ ግምት ከተሰታቸው ቀበሌ ድረስ ወርዶ በማደራጀት ጎልቶ የወጣው አንድነት እና ጠንካራ አመራርና አባላት ጭምር ያሉት መኢአድ በሕገ ወጥ ውሳኔ ለአንድነት ተለጣፊ አንድነትና አመራር ለመኢአድ ተለጣፊ አመራር ተሰጠበት:: የአገር ቤቱ የሰላማዊ ትግል ቢአንስ በፖለቲካ ፓርቲዎች ስም የሚደረግ እንቅስቃሴ የት ድረስ እንደሚሄድ የታየበት ብዙዎች ከዚህ አገዛዝ ጋር በተቃዋሚነት በሕጋዊ መንገድ ተመዝግቦ የሚደረግ ትግል መጨረሻው ይሄ ነው ያሉበት::
11. ሰማያዊ ፓርቲና መድረክ ምርቻውን እንደ መታገያ ወስደናል ብለው ምርቻ ውስጥ የገቡበትና ከምርጫ በሁዋላ ራሳቸውም በሰጡት ቃለ ምልልስ ባለባቸው ጫና ሳቢያ ትግሉን የረሱት መስለው የምርጫውን ውጤት በመቃወም ጉልህ ተቃውሞ የአደባባይን መውጣት ጨምሮ አለማድረጋቸውና የዝምታ ፖለቲካው::
12..የፕ/ት ኦባማ ወደ ኢትዮጵያ መሄድን ተከትሎ የጋዜጠኛ ርዮት ዓለሙና ከጦማሪያኑና ከጋዜጠኞቹ በአጠቃላይ አምስቱ ተለይተው መፈታት:: የአንድ ጋዜጠኛን ጨምሮ የሌሎች መታሰር::
ርዕዮት ዓለሙ ከእህቷ እስከዳር ዓለሙ ጋር ከ እስር ከተፈታች በኋላ
13.የቀሩት ጦማሪያን ብይን መጓተት:: የጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ ፍርድ እና ይግባኝ ጠይቆም ፍርዱ እንዲጸና መደረጉ የዓመቱ አበይት ጉዳይ ነበር::
14. የአሜሪካን ፕሬዝደንት ኦባማ ኢትዮጵያን ጎበኙ ። የአፍሪካን መሪዎች ሰብስበው በስልጣን ለምን መቆየት ትወዳላችሁ ። ያውም ብዙ ገንዘብ እያላችሁ ሲሉ ጠየቁ ። ግንቦት ሰባት አሸባሪ አይደለም ሲሉ የህወሓት ኢህአዴግን አገዛዝ ክስ ውድቅ ማድረጋቸው የ2007 ትውስታ ነበር::
15.የአርበኞች ግንቦት ሰባት የደፈታ ውጊያ በይፋ መጀመሩን ማወጁና ውጊያውን ተከትሎ ብዙ ሳይቆይ የአርበኞች ግንቦት ሰባት ሊቀመንበር ፕ/ር ብርሃኑ ነጋ እና ሌሎች ከፍተና አመራሮች አቶ ነአምን ዘለቀና አቶ ኤፍሬም ማዴቦ ወደ ኤርትራ በረሃ ትግሉን ለመምራት መውረድና የፈጠረው ሰፊ መነቃቃት::
16.የት እንዳሉ ያልታወቀው እንግሊዝን የዘገየ ቁጣ ያስከተለው የነጻነት ታጋዩ አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ ካልታወቀ እስር ቤት ወደ ቃሊቲ መቃወር እና በአባታቸው መጎብኝት፣ ለልጆቻቸው ስልክ መደወላቸውና በስማቸው መጽሐፍ እየተጻፈ ለመሆኑ የአገዛዙ ውጭ ጉዳይ ሚ/ር ፍንጭ መስጠታቸው እና ተያያዥ ውሸታቸው
17.የሕወሓት መሪዎች የስልጣን ሽኩቻ:: በአዲስ አበባውና በመቀሌው ቡድን መካከል የነበረው ሽኩቻ በመቀሌው ቡድን አሸናፊነት መጠናቀቁ::
18 . የረሃብ አደጋው በሰውና በእንስሳ ላይ ጉዳት ማድረሱና የአገዛዙ የተለመደ የሀሰት መግለጫ::
19. ኢህአዴግዬ እኔ ከሌለሁ ትጠፋላችሁ ብሎ ለሚቀጥለው 5 ዓመት ራሱን መረጠ ።
20 .የቴዲ አፍሮ የአዲስ ኣመት ኮንሰርት መሰረዝ እና ስርኣቱ የተቀበላቸው አርቲስቶች ዝግጅት :: ቴዲ አፍሮን መንግስት በዚህ ዓመት ብቻ 4 የሃገር ቤትና የውጭ ኮንሰርቶቹን እንዲሰርዝ ቭዛ እና ጥበቃ በመከልከል አሰናክሏል::
21. እየተባባሰ የመጣው የሰብኣዊ መብት ጥሰትና የኑሮ ውድነት ብልሹ አሰራር ዛሬም ዜጎችን ብዙሃኑን አማርራል:: አገዛዙ የዲያስፖራ በዓል ሲል በውጭ የሚገኘውን ኢትዮጵያዊ ለመደለል ለመከፋፈል የሞከረበት::
በነገራችን ላይ የ13 ወር ጸጋ በሚባልባት አገር አስራሶ ስተኛዋ ወር ጳጉሜ ዘንድሮ ስድስት ቀን ነች ለመንግስት ሰራተኛው ደሞዝ የማይከፈልበት ወር ናት። ለዚህ ይመስላል ጋዜጠኛ ጌታቸው ሽፈራው ከአገር ቤት <<ሌላው ሌላውስ ይቅር! በኢትዮጵያ የመንግስት ሰራተኛው ጷግሜ ውስጥ ለሚሰራው እንዲከፈለው የሚያስችል ትግል እንኩዋን እያደረገ አይደለም! ኢትዮጵያ የ13 ወር ፀጋ የሚለውን ሲያስተጋባ በዚች ወር በተባለችው ወቅት ለሚሰራው 13 ብር እንኳን እንዲጨመርለት የሚጠይቅ የለም! በነገራችን ላይ አከራዮች ለዚች ወር ማስከፈል ጀምረዋል!>> ሲል በአገር ቤት ጳጉሜን ጠቀስ አድርጓታል::
- Source Zehabesha
No comments:
Post a Comment