Which one you first choose? በቅድሚያ የሚፈልጉት

Tuesday, September 29, 2015

ሰንደቅ አላማው ላይ የተለጠፈውን የሰይጣን ምልክት ኮከብ አለመቀበል ምክንያታዊ ነው!





ባለ ኮከቡን ሰንደቅ አላማ አለመቀበል ምክንያታዊ ነው!

(ጌታቸው ሺፈራው)

በዚህ የህዝብ ምርጫ በሚከበርበት ዓለም ሰንደቅ አላማ ያህል ነገር አንድ ገዥ ቡድን ‹‹ከአሁን በኋላ ሰንደቅ አላማው ይኼ ነው›› ብሎ አንዳች ምልክት ሊለጥፍበት አይገባም ነበር፡፡ በአሁኑ ወቅት ያለው ሰንደቅ አላማ የመጣው ግን በዚህ መንገድ ነው፡፡


ለዚህ ሰንደቅ አላማ በቅርቡ አዋጅ ወጥቶለታል፡፡ ስርዓቱም ግን አያከብረውም፡፡ ይህን አዋጅ እንዲያከብረው የሚፈለው ሌላው በተለይ ከስርዓቱ በተቃራኒ ያለው ህዝብ ነው፡፡ ይህን ስርዓቱ የሚጥሰው፣ ህዝብ ግን አክብረው ተብሎ የመጣበትን አዋጅ ያፀደቀው የ99.6 በመቶው ፓርላማ ነው፡፡ ህዝብ ለዚህ ፓርላማ ምን አይነት አመለካከት እንዳለው ደግሞ ግልፅ ነው፡፡ ህዝብ ይወክለኛል ብሎ የማያምነው ፓርላማ ነው፡፡ ለህዝብ ጥያቄ ሳይሆን የገዥውን ፓርቲ ትዕዛዝ በተዋረድ የሚያስፈፅም፣ እጅ እንኳን ሲያወጣ፣ ሲደግፍና ድምፀ ታዕቅቦ ነኝ ሲል በትዕዛዝ ነው፡፡ ይህን ፓርላማ የህዝብ ወኪል ነው ማለት ቀልድ ነው፡፡

ፓርላማው ይወክለኛል የሚል አካል እንኳን ቢኖር ፓርላማ አወጣው፣ ገዥው ፓርቲ አፀደቀው፣ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ተናገረው የሰላማዊ ትግል አንዱ መርህ ተገቢነት የለውም ብሎ ላመነው የአምባገነን ህግ አለመገዛት ነው፡፡ መቃወም የሚቻለው ደግሞ ተግባሩን በመቃወም ነው፡፡ ለምሳሌ ያህል ሰንደቁ ላይ የተለጠፈውን ኮከብ ምልክት ባለመቀበል፣ ወይንም ንፁሁን ሰንደቅ አላማ መጠቀም!

በሌላ በኩል በቅርብ አመታት ሰንደቅ አላማው ላይ የተለጠፈውን ምልክት ከሰይጣን አምላኪዎች ጋር አገናኝተው አይወክለንም የሚሉት ኢትዮጵያውያን እየተበራከቱ ነው፡፡ የእነዚህ ግለሰቦች ትንታኔ ለእውነታ የቀረበም ነው፡፡ ይህ የአብዛኛዎቹም ኢትዮጵያውያን እምነት የሚቃረን እና የተጠላ (የ666 ምልክት የሚባለው) ሰንደቁ ላይ ተቀምጦ ኢትዮጵያውያን ለሰንደቁ ክብር ይሰጣሉ ማለት ዘበት ነው፡፡ በመሆኑም ኮከቡ የባዕድ አምልኮ ምልክት ነውና ይነሳልን ብለው የሚቃወሙት ምክንያታዊ ናቸው፡፡ እንደ ትንታኔያቸው መቃወም ግዴታቸውም ነው፡፡

በተለይ በቅርቡ ስርዓቱ የሰንደቅ አላማ በዓልን ያከብራል፡፡ ሰንደቁ ላይ የተለጠፈውን ምልክት አንቀበልም የሚሉ አካላትም በየራሳቸው መንገድ ምልክቱን አንቀበልም ብለው ለመዝመት ጊዜ አሁን ይመስለኛል፡፡ በየራሳቸው መንገድ!

የአምባገንንን ህግ መቃወም አፀፋ እንደሚያስከትል እሙን ነው፡፡ ይህን አፀፋ ለመቀነስ ትልቁ አማራጭ በጋራ፣ በዘመቻ፣ በአንድነት የአምባገነንን ህግ መቃወም ነው፡፡ ለምሳሌ ያህል የመስቀል በዓል እለት አንድ ወጣት ኮከቡ የተለጠፈበትን ሰንደቅ አላማ በራሱ መንገድ ተቃውሟል፡፡ ይህ ወጣት ያመነበትንና ምክንያታዊ ነው ያለውን ግን አድርጓል፡፡ ወጣቱ ከስርዓቱ ቅጣት ሊገጥመው ይችላል፡፡ በተግባር የተቃወመው ብቻውን በመሆኑ ቅጣቱም ሊበረታበትም ይችላል፡፡ በጋራና በተጠናከረ መንገድ ከሆነ ግን ስርዓቱ እርምጃም ለመውሰድ ይቸገራል፡፡ እርምጃ እንኳን ቢወስድ ሌላ ብሶት ይፈጥራል፣ ለተጠናከረ ትግልም መንገድ ይከፍታል፡፡ በተቀናጀ መንገድ የሚደረገው ተቃውሞም ህዝብ በስፋት የእንቅስቃሴው አካል እንዲሆንና መረጃውም እንዲደርሰው ማድረግ ይቻላል!

No comments:

Post a Comment

wanted officials