የእንግሊዝ ቪዛ የተከለከሉት ፕሮፌስር መስፍን ወ/ማርያም አሜሪካ ገቡ
(ዘ-ሐበሻ) ወደ እንግሊዝ ሃገር የሚያስኬዳቸውን ቪዛ ተከልክለው ወደዚያው ሊያደርጉት የነበረው ጉዞ የተስተጓጎለባቸው የሰብአዊ መብት ተሟጋቹ ፕሮፌሰር መስፍን ዛሬ ዋሽንግተን ዲሲ መግባታቸውን በስፍራው የሚገኙ የዘ-ሐበሻ ዘጋቢዎች አስታወቁ::
በቅርቡ ‘አዳፍኔ’ የተሰኘ ‘አወዛጋቢ’ መጽሐፍ ለንባብ ያበቁት እኚሁ ፕሮፌሰር ዛሬ ዋሽንግተን ዱሉስ ኤርፖርት ሲደርሱ ወዳጆቻቸው ሞቅ ያለ አቀባበል እንዳደረጉላቸው የዘ-ሐበሻ ዘጋቢዎች አስታውቀዋል::
ፕሮፌሰር መስፍን በአሜሪካ ቆይታቸው አዲሱ መጽሓፋቸውን በዋሽንግተን ዲሲ በሸራተን ፔንታጎን ሲቲ እሁድ ሴፕቴምበር 13, 2015 ዓ.ም ከ2 ሰዓት ጀምሮ ያስመርቃሉ:: በዚህም ወቅት የሕዝብ ጋር ወቅታዊ ውይይት እንደሚያደርጉ አዘጋጆቹ ለዘ-ሐበሻ ከላኩት ፍላየር (በራሪ ወረቀት) መረዳት ተችሏል::
ፕሮፌሰር መስፍን እንግሊዝ ሃገር በተለያዩ ጊዜያት ቢመላለሱም ዘንድሮ ቪዛ መከልከላቸው ብዙዎችን አነጋግሩዋል። የእንግሊዝ መንግስት ቪዛ የከለከለበት ምክንያት በዚያው ሊቀሩ ይችላሉ በሚል ነው።

ፕሮፌሰር መስፍን በኢሳት ቢሮ
No comments:
Post a Comment