Which one you first choose? በቅድሚያ የሚፈልጉት

Wednesday, September 16, 2015

የተወሰኑት የኮሚቴ አባላት ስለተፈቱብቻትግሉእንደማይቆም ድምፃችንይሰማአስታወቀ

የተወሰኑት የኮሚቴ አባላት ስለተፈቱብቻትግሉእንደማይቆም ድምፃችንይሰማአስታወቀ
መስከረም ፭ (አምስት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የሙስሊም የመፍትሔ አፈላላጊ ኮሚቴ አባላት ከሆኑት መካካል ኡስታዝ ያሲን ኑሩ፣ ሳቢር ይርጉ፣ አቡበከር ዓለሙ እና ገጣሚው ሙኒር ሁሴን ከእስር መለቀቃቸውን አስመልክቶ ድምፃችን ይሰማ ባወጣው መግለጫ፣ ሁሉም እስረኞች ካለምንም ቅድመ ሁኔታዎች እስካልተፈቱ ድረስ ትግላቸው እንደሚቀጥሉ በአጽንኦት ገልጿል።
ድምፃችን ይሰማ ፣ ” ተፈቺዎቹም ይሁኑ ታሳሪዎቹ ጀግኖቻችን ሃይማኖታችን በተደፈረበት፣ መንግስታዊ አምባገነንነት በሰፈነበት በዚህ ቁርጥ ጊዜ ታላቅ ህዝባዊ አደራ ተሸክመው የሰው ልጅ ችሎ ያልፈዋል ተብሎ በማይታሰበው የስቃይ እቶን ላይ እራሳቸውን መስዋዕት ያደረጉልንን ወንድሞቻችንን ሳናወዳድር ሁሉንም በክብር ሰገነት ላይ ለማስቀመጥ አናቅማማም። ” ብሎአል።
“የወንድሞቻችን መፈታት የትግላችን ተጨማሪ ጥያቄ እንጂ ዋነኛ ጥያቄያችን አለመሆኑን ሁሌም ማስታወስ ይገባል” የሚለው ድምጻችን ይሰማ፣ “የትግላችን ማጠንጠኛ መንግስት የጀመረው ሃይማኖትን መሰረት ያደረገ ብሄራዊ ጭቆና ነው፡፡ የትግላችን ግብም ይህንን ጭቆና ማራገፍ እና መብታችንን በዘላቂነት ማስከበር መቻል ነው” ብሎአል።


No comments:

Post a Comment

wanted officials