Which one you first choose? በቅድሚያ የሚፈልጉት

Tuesday, June 26, 2018

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አፋር ክልል አዳራሹ በካድሬ ብቻ ተሞልቶ ስለጠበቃቸው አኩርፈው የተዘጋጀውንም ምሳ ሳይበሉ መመለሳቸው ተሰማ። በአፋር ብዙ ምሁራንና ወጣቶች ታሰሩ። ባንክና ሆቴሎች የመሳሰሉትም ተዘግተዋል


ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ በአፋር ክልል ሰመራ ከተማ ከክልሉ ነዋሪዎች ጋር ሕዝባዊ ውይይት አደርገዋል። የጠቅላይ ሚኒስትሩን መምጣት ተከትሎ የክልሉ ገዢ ፓርቲ የሆነው የአፋር ሕዝብ ዴሞክራሲያ ፓርቲ (አ.ብ.ዴ.ፓ.) የፓርቲውን አባላትና ደጋፊዎችን ከተለያዩ ከተሞች በማምጣት አስተዳደራዊ ቅሬታዎች እንዳይሰሙ አድርጓል።
በክልሉ የተንሰራፋውን ሌብነት፣ የዘመድ አዝማድ አሰራር፣ ኋላቀርነትና የህወሃትን ጣልቃ ገብነት ያጋልጣሉ የተባሉ ግለሰቦች ላይም አካላዊ ጉዳቶች ተፈጽሞባቸዋል። ቁጥራቸው ከሰማኒያ በላይ የሚሆኑ ወጣቶችና የሰመራ ዩኒቨርሲቲ ምሁራንም ካለ ፍትሕ ታስረዋል። ወጣቶችን በመደገፍ የምትታወቀውና የከተማው ፖሊስ ሰራዊት አባል የሆነችው ሳዲያ አህመድ በድብደባ ጉዳት ከደረሰባቸው ውስጥ አንድዋ መሆኗን የአፋር ሰብዓዊ መብት ታጋይ ወጣት አካድር ኢብራሂም ገልጸዋል።
የአፋር ክልል፣በኢትዮጵያ ኋላቀር ክልል ተብለው ከማእከላዊ መንግስት ተጨማሪ በጀት ከሚመደብላቸው ክልሎች አንዱ ቢሆንም፣ የክልሉ ነዋሪዎች አሁንም የልማቱ ተጠቃሚዎች መሆን አልቻሉም።
ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ዛሬ ለተገኙት ተሰብሳቢዎች ባሰሙት ንግግር “የዴሞክራሲ ስርዓት ግንባታ ሂደት ላይ የሚፈጠሩ ዘርፈ-ብዙ ችግሮችን ለመፍታት በአንድነት ከጎናችን ሆናችሁ ጥንካሬ እንደምትጨሩረልን አንጠራጠርም። ምክንያቱም አንድም ቀን ለኢትዮጵያ ፍቅርን ለባንዲራ ፍቅርን አሳንሳችሁ አታውቁምና!” በማለት የአፋር ህዝብ ለኢትዮጵያዊነት ምስረታ ላበረከቱት አስተዋጾ አመስግነዋል። ወደፊትም የተለመደው አጋርነታቸውን እንዲቀጥሉ ጥሪ አቅርበዋል።
ክቡር ጠሚዶኮ ዐቢይ አህመድ የጀመሩትን የመደመር መርሃ ግብራቸውን ለማስቀጠል ዘበዛሬው ዕለት ወደ አፋር ክልል አቅንተዋል። በዚያም የክልሉ ባለሥልጣናት ለጠቅላዩ አቀባበል አድርገዋል። ነገር ግን ለጠቅላያችን የተደረገው አቀባባል በሌሎች ክልሎች ከተደረገው አቀባበል ጋር እንኳን ሊቀራረብ ጭራሽ አይጠቀስም ይላሉ የመረጃ ምንጮቼ።
በአፋር ተቃውሞ ከተጀመረ ሳምንታት ተቆጥረዋል። አፋሮቹ እንደሚሉት ከሆነ የህውሓት እስትንፏሷ ያለው ወልቃይት ሳይሆን አፋር ነው ነው የሚሉት። በአፋር ጨውና ጥጥን ጨምሮ የተፈጥሮ ሃብቱንና ኢኮኖሚውን ጭምር የተቆጠጠሩት ህውሓቶች በመሆናቸው ሀገሬው የበዪ ተመልካች ሆነዋል ነው የሚሉት። እናም ዛሬ የከተማው ህዝብ ወደ አዳራሹ በመሄድ ብሶቱን ለመናገር ገና ከጠዋቱ ነበር ጉዞ የጀመረው።
ዶር ዐቢይ ከመምጣቱ ቀደም ባሉት ሳምንታት አፋሮችን የሚያስቆጣ ተግባር በክልሉ መሪ ፓርቲ አብዴፓ/ኢህአዴግ መፈጸሙ ለዛሬው ህዝባዊ ቁጣ እንደዳረጋቸውም ይነገራል። በአፋሮች ዘንድ እንደ እንደ ጀግና የሚቆጠር ረሺድ የሚባል የአፋር ተወላጅ ነበር። ይህ ሰው እጅግ የተማረ ስለሆነ ለሆዱ ሳይሆን ለህሊናው መኖር የጀመረ ሰው እንደሆነ ይነገርለታል። የህውሓቶቹ በክልሉ ውስጥ የሚፈጽሙት ህገወጥ ተግባራት በሙሉ ነገረሥራቸው ሁሉ አይጥመውም፣ ባገኘው አጋጣሚ ሁሉ ሳይፈራ ይቃወማቸዋል፣ ቢቸግራቸው ገንዘብ ሲያገኝ ይተንይሆናል በማለት የወረዳ ፋይናንስ ኃላፊ አድርገው ይሾሙታል። እሱ ግን አሻፈረኝ በማለት ሰመራ ዩንቨርስቲ የሰው ሃብት ተቀጥሮ በመሥራት ተቃውሞውን ቀጠለበት። በዚህ ሁኔታ እያለ ነው እንግዲህ የዐቢይን ወደ ሥልጣን መምጣት ተከትሎ ባለፈው ሳምንት አካባቢ ተጠልፎ የተሰወረው።
ይህ በእንዲህ እንዳለ ታድያ አዲሱን መንግሥት ተከትሎ የአፋር ህዝብ ልል እንደሌሎቹ ከተሞች ህዝብ ለዶር ዐቢይ የድጋፍ ሰልፍ ለማድረግ አደባባይ ቢወጣ የክልሉ አቃጣሪ ፓርቲ በመሳሪያ ኃይል ሰልፈኛውን እንደበተነ ይነገራል።
አፋሮቹ ተስፋ ሳይቆርጡ እንደገና ሰኔ 16 ጠሚዶኮ ዐቢይን ለመደገፍና አስጠቅቶናል፣ አስዘርፎናል፣ ድኃም እንድንሆን አስደርጎናል የሚሉትን የህውሓት ተለጣፊውን አብዴፓን እንቃወማለን በማለት ሰልፍ ወጡ። የክልሉ መንግሥትና ፓርቲውም አቶ ረሺድን እኛ አላሰርነውም የት እንዳለም አናውቅም በማለት ለህዝቡ ምላሽ ሰጡ። ጉዳዩም ከዶር ዐቢይ ጆሮ ደርሰ። እናም ለዚህ ነበር የአፋር ህዝብ ወደ አዳራሽ እንዳይገባም፣ ጥያቄም እንዳያቀርብ የተከለከለው።
ጠዋት ላይ አሁን የአፋር ወጣቶች ዐቢይን ማግኘት እንፈልጋለን። ለእሱ የምንነግራቸው ምስጢሮች አሉን በማለት ነበር ወደ አዳራሹ የተመሙት። ነገር ግን እዚያ ሲደርሱ አብዴፓ ሆዬ ህዝቡን ትቶ የቀበሌ ሠራተኞችን፣ የፓርቲው አባላትና የወጣት ፎረም አደረጃጀቶችን፣ እንዲሁም የህውሓት ካድሬዎችን በኮድ እየመረጠ ህዝቡን አላስገባ አለ። በዚህ መሃል ህዝቡ የክልሉ ፓርቲ የፈለገውን እያስገባ እኛን አላስገባ ብሎናል በማለት ጭቅጭቅና ግርግር ይፈጠራል። እነገባለን አትገቡም ጭቅጭቁ ሲበረታ ጊዜ ፖሊስ ጥይት በተኮስ የኃይል እርምጃ በመውሰዱ ብዙዎችን አበሳጭቷል፡፡ በኃይል እርምጃውም ወታደሮቹ በብዙ የአፋር ወጣቶች ላይ የአካል ጉዳት እንደደረሰባቸው ነው የሚደርሱኝ መረጃዎች የሚያሳዩት።
ዶክተር ዐቢይም በአዳራሹ ውስጥ ባዩት ነገር ደስተኛ አልሆኑም። እንዲያውም እንዲህ ማለታቸው ነው የተሰማው። " እናንተ የአፋር አመራሮች ሁለት ሞት ትሞታላችሁ፡፡ አንድም ሐብቱና ንብረቱ በዘረፋችሁበት አፋር ህዝብ ዘንድ ትሞታላች፡፡ ሁለተኛው ደግሞ በአምላክ ዘንድ ሞታችሁ ትጠየቁበታላችሁ፡፡ በማለት አብዴፓን አስደንግጠዋል ተብሏል።
በዚህ የዶክተር ዐቢይ ንግግር የተደፋፈረና በአዳራሹ በተአምር የተገኘ ጀግና የሆነ የአፋር ወጣት እራሱ የአብዴፓ ካድሬዎችን ሳያስቡት ያስጨበጨባቸውን ንግግር ማድረጉ ተነግሯል። ወጣቱ እንዲህ ነበር ያለው " የአፍዴራ ጨው ለ27 ዓመታት እየተጠቀመ ያለው የአብዴፓ አመራሮችና ነፍሰ አባታቸው የህወሓት መሪዎች ናቸው " ። እናም እኛ አፋሮች የኢኮነሚም የፖለቲካም ነፃነትና ፍትህ እንፈልጋለን በማለት እቅጯን ተናግሮ ለአፋሮች መተንፈሱ ነው የተነገረው።
ዶክተር ዐቢይ ዛሬ በአፋር አመራሮች ደስተኛ እንዳልሆኑ ነው የተነገረው። በዚህም የተነሳ አብዴፓ ያዘጋጀውን ምሳ እንኳን ሳይበሉ በመጡበት አውሮፕላን ተሳፍረው በወደ አዱ ገነት ተመልሰዋል ተብሏል።
ሽማግሌው የአፈር ሱልጣን አሊ ሚራህ ወጣቶቹ ከህውሀት ጥገኝነት እንላቀቅ የሚሉና ራሳቸውን ልክ እንደ ቄሮ፣ ፋኖ፣ ዘርማ #ዱኮሄና እያሉ የሚጠሩ እንደሆነና ዱኮሄናዎችም ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ጉልበት እያወጡ የመጡ ናቸው ተብሏል።
አሁን አስቸጋሪ ሁኔታ ተፈጥሯል እያለኝ ነበር። ጓደኛዬና የመረጃ ምንጬ ወታደሮቹ ዐቢይን ወደ አዳራሽ ካስገቡ በኋላ ከውጭ ያገኙትን ሰው ሁሉ እያፈሱ እንደሆነና የቢሮ ሠራተኞችም አፈሳውን ፈርተው ከቢሮ ሳይወጡ በቢሮ ውስጥ ለመቀመጥ መገደዳቸውን ነግሮኛል።
የመረጃ ምንጬ እንደሚለው ከሆነ ህዝቡ በጣም አዝኗል። ጠቅላይ ሚንስትሩ በየሄዱበት ክልል እስረኞች እያስፈቱ አድናቆት ሰጥናቸው ሳናበቃ እነሆ ዛሬ ወደ አፋር ሲመጡ በእሳቸው ፊት ምሁራን ወጣቶች ታሰሩ ። ከ 32 በላይ ወጣቶች ተደበደቡ፣ ታሠሩም። ይሄ ሁሉ በደል የደረሰውና የታሰሩት ምሁራን የህዝብን ጥያቄ ለጠቅላይ ሚንስትሩና ለኢትዮጵያ ህዝብ ጆሮ ያደርሳሉ ተብሎ በመፈራቱ ነው ይላሉ።
ይሄ ግን መፍትሄ ይሆናል ወይ? ብለውም ይጠይቁና በጭራሽ መፍትሄ አይሆንም። መንግሥት ዛሬ በህዝቡ ላይ በወሰደው እርምጃ ህዝቡ እንዲያውም አንድነቱን እንዳጠነከረበት ይናገራሉ።
Image may contain: one or more people and people sitting
አፋሮቹ በእስር ቤት ታጉረዋል። ዶር ዐቢይም ቢያዩት መልካም ነበር። ነበር ባይቀር መደመር አለ አፋር።
Image may contain: 2 people, people smiling, people standing and text
የአፋሮቹ እነደ ቄሮ፣ ፋኖ እና ዘርማ ራሳቸውን ዱኮሂና ብለው ተከስተዋል። ብራቦ ዱኮሂናዎች ። በርቱ ።
Image may contain: one or more people

No comments:

Post a Comment

wanted officials