Which one you first choose? በቅድሚያ የሚፈልጉት

Thursday, June 14, 2018

missing Children በአሜሪካ ከወላጆቻቸው የሚነጠሉ ህጻናት ቁጥር መጨመሩ ተገለጸ

በአሜሪካ ከወላጆቻቸው የሚነጠሉ ህጻናት ቁጥር መጨመሩ ተገለጸ

 የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ አስተዳደር የሚከተለውን የውጪ ፖሊሲ ተከትሎ ከወላጆቻቸው የሚነጠሉ ህጻናት ቁጥር አሳሳቢ ደረጃ ላይ መድረሱ ተገለጸ።
ፕሮ ፐብሊሺያ የተባለ የዜና ማሰራጫ ከቤተሰቦቻቸው ሲለያዩ ሕጻናቱ የሚያሰሙትን የሰቆቃ ድምጽ ቀርጾ ይፋ ማድረጉን ተከትሎ በፕሬዝዳንት ትራምፕ ላይ ተቃውሞ ማየሉ ተሰምቷል።
የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ህገወጥ በሚሏቸው ስደተኞች ላይ ያላቸው ፖሊሲ ርህራሄ የሌለው ነው በማለት በብዙዎች ዘንድ ተቃውሞ ሲገጥመው ቆይቷል።
አሁን ላይ ደግሞ በስደተኛ ማቆያዎች ውስጥ ከቤተሰቦቻቸው ተነጥለው እንዲቀሩ የተደረጉ በርካታ ህጻናት መኖራቸውን ነው ፕሮ ፐብሊሺያ የተባለ የዜና ማሰራጫ በቅርቡ ቀርጾ ባሰራጨው የሕጻናት የሰቆቃ ድምጽ መረዳት የተቻለው።
በመገናኛ ድረገጾች በከፍተኛ ፍጥነት የተሰራጨውና በብዙ ሰዎች ዘንድ መደመጥ የቻለው ይህ ድምጽ የ6 አመት ሕጻን ቤተሰቦቿን እየጠራች ስታለቅስ የሚያሳይ ነው።
በአካባቢዋ ያለው ድንበር ጠባቂ ፖሊስ ደግሞ በሕጻኗ ለቅሶ ሲያፌዝ አብሮ የተቀረጸው ድምጽ ደግሞ ከፍተኛ ቁጣ እንዲቀሰቀስ ምክንያት ሆኗል ብለዋል።
የድንበር ተቆጣጣሪ ሰራተኞች በበኩላቸው ህጻናቱን ከቤተሰባቸው መነጠል ፍላጎታችን ባይሆንም ህጉን ተከትለን ግን ስራችንን እየሰራን ነው ማለታቸው ተገልጿል።
በበርካቶች ዘንድ ፕሬዝዳንቱ ትችት እየተሰነዘረባቸው ቢሆንም የትራምፕ አስተዳደር ግን ህገወጥ ናቸው ባላቸው ስደተኞች ላይ እየወሰደ ያለው ርምጃ ተጠናክሮ መቀጠሉ ነው የተገለጸው።
የትራምፕ አስተዳደር ይህንንም የሚያደርጉት በሜክሲኮ እና በአሜሪካ መካከል እገነባለሁ ላሉት ግንብ ዲሞክራቶች ላይ ጫና ለማድረግና በጀት እንዲፈቅዱላቸው ለማድረግ መሆኑን አልጀዚራ በዘገባው አስፍሯል።
በእስካሁኑ ሂደትም 2000 የሚደርሱ ሕጻናት ከወላጆቻቸው መነጠላቸውን ዘገባው አመልክቷል።

No comments:

Post a Comment

wanted officials