Which one you first choose? በቅድሚያ የሚፈልጉት

Saturday, June 2, 2018

የጠቅላይ ሚኒስቴር ዶ/ር አብይ አህመድ ከ01-04 ኦገስት 2018 በሽቱትጋርት ከተማ ላይ በሚደረገው በአውሮፓ የስፖርትና የባህል ዝግጅት ላይ በእንግድነት ተገኝቼ ንግግር ላድርግ ጥያቄን ይመለከታል


ግልጽ ደብዳቤ (ከሽቱትጋርትና አካባቢው ኢትዮጵያውያን የጋራ ግብረ ሃይል


የኢትዮጵያውያኖች ትግል የህግ የበላይነት የተከበረባት ዲሞክራሲያዊት ኢትዮጵያን ለመመስረት ነው::
 ሽቱትጋርት, 28.05.2018
የዚህ ግልጽ ደብዳቤ ኣላማው: በቅርቡ በተለያዩ ሚዲያዎች የተሰራጩትን የጠቅላይ ሚኒስቴር ዶ/ር አብይ አህመድ 01-04 ኦገስት 2018   በሽቱትጋርት ከተማ ላይ በሚደረገው በአውሮፓ የስፖርትና የባህል ዝግጅት ላይ በእንግድነት ተገኝቼ ንግግር ላድርግ ጥያቄን ይመለከታል
በመሰረቱ ጠቅላይ ሚኒስቴር ዶ/ር አብይ አህመድ ያቀረቡት ጥያቄ አንድነቱ የዲሞክራሲያዊ መብቱና ዜግነቱ ተጠብቆለት የሚኖር ማንኛውም ህዝብ የሚደግፈውና ደስ የሚያሰኝ ጥያቄ ነው፥፥ ባለመታደል ሆኖ ኢትዮጵያ አገራችን ያለችበት ሁኔታ ከዚህ አይነቱ መሰረታዊ የነጻነትና የህግ የበላይነት መከበሮች በጣም የራቅ በፍጹምም በሚቃረን መንገድ ላይ ነው:: ይህ ግፍና ጭቆና ገደላ ያንገፈገፈው የኢትዮጵያ ህዝብ ባለፉት 27 አመታት ህይወቱን በመሰዋት ፣ በመታሰር ፣ በመገረፍ በከፈለው ተጋድሎ አገራችን ዛሬ የደረሰንበት ወሳኝ ምእራፍ ላይ እንድትገኝ ሆናለች::
በዚህ ምዕራፍ ውስጥ እየተገኝን በቅርቡ  ጠቅላይ ሚኒስቴር ዶ/ር አብይ አህመድ ኢትዮጵያን እያወደሱ የተናገሯቸው ንግግሮች ይበርቱበት የሚያስብልና ህዝባችንን ተስፋ ብርሃን እንዲያይ ያደረገ ቢሆንም በአንጻሩ ከመንግስት በኩል በተግባር ደረጃ የታዩት የህሊና እስረኞችን መፍታት  ፣ የህግ የበላይነትን ማስከበር እንዲሁም ከየቦታው በጎሳ ፖለቲካ አማካኝነት የሚፈናቀሉትንና የሚንገላቱትን ወገኖች የዜግነት መብታቸውን የማስከበሩን ስራዎች ስንመለከት በመድረክ ላይ ከሚቀርቡ  የተስፋ ቃላቶች በስተቀር የተግባር ለውጦች ባዶ ሆነው እናገኛቸዋለን:: ይህንን አይነቱ አካሔድ ደግሞ ለአለፉት 60 አመታት የኢትዮጵያ ህዝብ በተፈራረቁበት መንግስታቶች ያየውና አልቀበልም ብሎ ህይወቱን ለነጻነቱ ለመብቱ እንዲከፍል ያስገደደው ነው::
እኛ በሽቱትጋርትና አካባቢው የምንገኝ ኢትዮጵይውያን ግብረሃይሎች ጠቅላይ ሚኒስቴር ዶ/ር አብይ አህመድ ለአውሮፓው ስፖርት ዝግጅት ከመምጣታቸው በፊት ከዚህ በታች የሚገኙትን መሰረታዊ የኢትዮጵያን ህዝብ ጥያቄዎች እንዲያሟሉ እንጠይቃለን:
  •  የፍትህና የመብት ጥያቄን ሆን ተብሎ ለማፈን የወጣው የአስቸኳይጌዜ አዋጁ ከህዝባችን ላይ ይነሳ
  •  የሽብርተኛ ህግ ከህዝባችን ላይ ይነሳ
  •  ሁሉም የፖለቲካና የህሊና እስረኞች ያለምንም ቅድመ ሁኔታ ይፈቱ
  •  ከሞያሌ፣ ከቤንሻንጉልና ከሌሎች ቦታዎች የተፈናቀሉ ወገኖቻችን ወደተፈናቀሉበት ቦታ ይመለሱ
  •  ነፃፕሬስ እና ለዲሞክራሲ ግንባታ የሚረዱ ተቋሞች ነፃ ይሆኑ
  •  የወልቃይት ህዝብ ጥያቄ መልስ ያግኝ
  •  የወያኔን እስርና ግድያን በመሸሽ በአውሮፕና በአፍሪካ በስደተኝነት ጥያቄ ላይ ያሉ ወገኖቻችን ከላይ የተጠቀሱት ጥያቄዎቻችን በተግባር ደረጃ ሳይመለሱ ባህርና በረሃን አቋርጠው የመጡበትን የተባበሩት መንግስታት የስደተኛነት መብታቸውን እንዳያበላሹ እንጠይቃን
እነዚህን ከላይ የተዘረዘሩትን የህዝባችንን መሰረታዊ ጥያቄዎች ሳይመልሱ በሽቱትጋርት የሚደረገው ስብሰባ ላይ ቢመጡ በተቃውሞ እጅበን እንደምንቀበሎት በግልፅ ለማስቀመጥ እንወዳለን።
የህዝባችንን መሰረታዊ ጥያቄዎች ይከበሩ በተግባርም መልስ ያግኙ
ከሽቱትጋርትና አካባቢው ኢትዮጵያውያን የጋራ ግብረ ሃይል!!

Source: abbaymedia

No comments:

Post a Comment

wanted officials