Which one you first choose? በቅድሚያ የሚፈልጉት

Wednesday, June 20, 2018

አሜሪካና ሰሜን ኮርያ ታሪካዊ ስምምነት ተፈራራሙ


  የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ከሰሜን ኮርያው መሪ ኪም ጆንግ ኡን ጋር ታሪካዊ ስምምነት ተፈራራሙ።
ሁለቱ መሪዎች ዛሬ  ሲንጋፑር ወስጥ ባደረጉት ውይይት ለሁለቱ ሃገራት ሰላም እና ብልጽግና ለመስራት ቃል ገብተዋል።
በዚህም ሰሜን ኮርያ የኒውክለር ፕሮግራሟን ለመሰርዝ ቃል መግባቷም ተመልክቷል።
ኮርያ ሰሜን እና ደቡብ በሚል ከተከፈለችበት እንደ አውሮፓውያኑ አቆጣጠር ከ1945 ጀምሮ ለ 73 ዓመታት ከአሜሪካ ጋር በጠላትነት የቆየቸው ሰሜን ኮርያ ይህንን ታሪካዊ ስምምነት ማድረጓ ሃገሪቱን ወደ ዓለም አቀፉ መድረክ እንደሚመልሳትም ተመልክቷል።ሆኖም ከአለም ተነጥለው በፍጥጫ ውስጥ ለቆዩት ሰሜን ኮርያውያን  ይህ ርምጃ ደስታን በቻ ሳይሆን ቅሬታን ማስከተሉም ተዘግቧል።የሰሜን ኮርያው መሪ ኪም ጆንግ አን ወደ ታሪካዊው ስምምነት ለመምጣት ብዙ መሰናክሎችን ማለፋቸውን ተናግረዋል።በዚህም ስምምነት ዓለማችን መሰረታዊ ለውጥ ታያለች ሲሉም ቃል ገብተዋል።
ይህንኑ ስምምነት ታሪካዊ ሲሉ ያወደሱት የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ የትናንት  ግጭት የነገ ጦርነት አይሆንም፣የትናንቱም ጉዳይ የነገን ሁኔታ አይወስንም በማለት አዲስ ምዕራፍ ውስጥ መሆናቸውን ገልጸዋል።ሁለቱ መሪዎች በሲንጋፑር የደሴት ከተማ ሲንቶሳ ውስጥ ያደርጉት ሥምምነት የዓለም አቀፍ ሚዲያዎች አብይ ርዕስ ሆኖ ቀጥሏል።

No comments:

Post a Comment

wanted officials