አዲስ አበባን ማዳን ኢትዮጵያን ማዳን ነው !!
ኢ/ር ጌታነህ ባልቻ አባላለሁ:: በአዲስ አበባ ከተማ ምርጫ ወረዳ 1እና 9 የህዝብ ተወካዮች ም/ቤት ዕጩ ተወዳዳሪ ነኝ።
አዲስ
አበባን ማዳን ኢትዬጵያን ማዳን ነው ! ብለን የጀመርነው ጉዞ ብዙ ርቀትን ተጉዘንበታል ። አዲስ አበባን ከተረኞች
ጉያ ፈልቅቀንም አናወጣለን!! አዲስ አበበም በእውነተኛ ልጆችዎ እንድትመራና ለዘመናት የደረሰባትን
የኢኮኖሚ፣የማህበራዊ፣ የፖለቲካዊ እና ህጋዊ ስብራት እንድትታከም፤ የህዝቡም ጥያቄዎች በአግባቡ እንዲመለስ ለማድረግ
የመጨረሻ ምዕራፍ የደረስንበት ግዜ ላይ እንገኛለን።
ስለዚህ ባለፈው ሁለት አመት ጉዟችን አብራችሁን
የነበራችሁ በመንገዳችን የደገፋችሁን፣የመከራችሁን፣አዲስ አበባን በሰላማዊ መንገድ ብቻ ለማዳን የተጋችሁ የከተማችን
ነዎሪዎች በሙሉ የትግላችን ማሳረጊያ የሆነውን ምርጫ ለማከናወን የመራጮች መመዝገቢያ ጥቂ ቀናት ብቻ ቀርቶታል።
በመሆኑም
አዲስ አበባን ለማዳን የምርጫ ካርድ መያዝ ወሳኝ ጉዳይ በመሆኑ እንድታወጡ፤ በምርጫው እለትም ባልደራስ
ያቀረባቸውን የከተማው ነዎሪ ህዝብ እውነተኛ እጩ ተወካዬች በመምረጥ ሀገራዊ ግዴታዎን ይወጡ ዘንድ በአክብሮት
መልዕክቴን አስተላልፋለሁ።
ድል ለእውነተኛ ዲሞክራሲ
Which one you first choose? በቅድሚያ የሚፈልጉት
Tuesday, April 13, 2021
ኢ/ር ጌታነህ ባልቻ አባላለሁ:: በአዲስ አበባ ከተማ ምርጫ ወረዳ 1እና 9 የህዝብ ተወካዮች ም/ቤት ዕጩ ተወዳዳሪ ነኝ። አዲስ አበባን ማዳን ኢትዮጵያን ማዳን ነው
Subscribe to:
Post Comments (Atom)
No comments:
Post a Comment