Which one you first choose? በቅድሚያ የሚፈልጉት

Tuesday, April 13, 2021

ፈረንሳይ_ለጋሲዮን የምርጫ ክልል 12/13 ተወዳዳሪዎች ባልደራስ፣ ኢዜማ ብልጽግ ና

 

የ ኢዜማ ተወዳዳሪ ታዋቂው ታሳሪ ንቁ መሪ አንዷለም አራጌ ፤ ምርጫ ወረዳ 12/13 !
💚💛❤💕
ምርጫ ወረዳ 12/13 ፡ በፈረንሳይ፣ ቤላ፣ ሚኒሊክ፣ ቀበና፣ ስድስት ኪሎ... ከወረዳው የኢዜማ እጩ አይበገሬው አንዲ ጋር በመሆን የተሳካ የጎዳና ላይና የቤት ለቤት የማስተዋወቅ ፤ እንዲመዘገቡና ኢዜማን እንዲመርጡ ቅስቀሳ አድርገዋል!
ንቁ ዜጎች መዝነው ይመርጣሉ ኢትዮጵያ ታሸንፋለች! 
 
ወረዳ 13 ለህዝብ ተወካዮች !
~ ሙአዘ ጥበባት ዲያቆን ዳንኤል ክብረት ( በግል)
~ አቶ አንዱዓለም አራጌ ( ኢዜማ)
~ ባልደራስ ( መሶበ ወርቅ ቅጣው )
~ ብልጽግና ( እጩ ተወዳዳሪ ይፋ አልሆነም)
የካ ክፍለ ከተማ ወረዳ 13 የምርጫ ክልል ከፍተኛ ፉክክር እንደሚኖር ከወዲሁ የሚጠበቅ ነው ።
#ማስታወሻ ፦ " የተፋጠነ የፍትሕ ሥርዓት ይሰጠን ፤ ለምርጫ የሚጠብቀን ህዝብ አለ ፤ ህዝብ በምርጫ ካርድ ይዳኘን " በማለት ለባለፉት 8 ወራት በተደጋጋሚ በፍ/ቤት አቤቱታ እያቀረበ የሚገኘው ፤ የባልደራስ ፓርቲ ፕሬዝዳንት እስክንድር ነጋ ውልደት እና እድገቱ በምርጫ ወረዳ 12/13 አካባቢ መሆኑ የሚታወቅ ነው።
May be an image of 4 people and text

 May be an image of 2 people and text

 ፈረንሳይ_ለጋሲዮን የምርጫ ክልል 12/13

የአምባገነኖች ሥርዓት በእውነተኛ ዲሞክራሲያዊ ሥርዓት ለመተካት ምርጫው ቁልፍ መሣሪያ ነው !!

መሶበወርቅ ቅጣው እባላለሁ። የባልደራስ ለእውነተኛ ዲሞክራሲ ፓርቲ በአዲስ አበባ ከተማ የምርጫ ክልል 12/13 የፌደራሉ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እጩ ነኝ።

በኢትዮጵያ ቋንቋዎችና ሥነ ጽሑፍ - የመጀመሪያ ዲግሪ እና በኢትዮጵያ ሥነ ጽሑፍና ፎክሎር - የማስተርስ ዲግሪ አለኝ። በአሁን ወቅት ደግሞ የፎክሎር የፒ. ኤች. ዲ. ተማሪ ነኝ።

በዜጎች ላይ ማንነታቸውን እና ሀይማኖታቸውን መነሻ በማድረግ እየደረሰባቸው ያለውን የዘር ማጥፋትና ኢሰብአዊ ጭፍጨፋ ፓርቲያችን ባልደራስ አጥብቆ ይቃወማል።

በመዲናችን አዲስ አበባ ዘርን መሠረት በማድረግ እየደረሱ ያሉ በርካታ ችግሮችን አሰወግዶ ሰላም፣ እኩልነት እና ዲሞክራሲያዊ አሠራር እንዲሰፍን ባልደራስ ጠንክሮ እየሠራ ይገኛል።

በሀገርና በሕዝብ ላይ እየደረሰ ያለውን አስከፊ የአምባገነኖች ሥርዓት በእውነተኛ ዲሞክራሲያዊ ሥርዓት ለመተካት ምርጫው ቁልፍ መሣሪያ ነው።
የተወደዳችሁና የተከበራችሁ ወገኖቻችን!!! ህልውናችንን ለማስከበር ወሳኝ የሆነውን የምርጫ ካርድ ጊዜው ሳያልፍ እንድታወጡ በትህትና እጠይቃለሁ።

May be an image of 1 person
ድል ለእወነተኛ ለዲሞክራሲ

No comments:

Post a Comment

wanted officials