Which one you first choose? በቅድሚያ የሚፈልጉት

Showing posts with label #HR128. Show all posts
Showing posts with label #HR128. Show all posts

Sunday, January 28, 2018

ኤች አር 128 በመባል የሚታወቀውና በአሜሪካ ምክር ቤት የወጣው ረቂቅ ሕገ ውሳኔ በምክር ቤቱ ለድምጽ አሰጣጥ እንደሚቀርብ ታወቀ።

(ኢሳት ዲሲ–ጥር 22/2010) 
ኤች አር 128 በመባል የሚታወቀውና በአሜሪካ ምክር ቤት የወጣው ረቂቅ ሕገ ውሳኔ በምክር ቤቱ ለድምጽ አሰጣጥ እንደሚቀርብ ታወቀ። ሕገ ውሳኔው ለድምጽ አሰጣጥ የሚቀርበው በኢትዮጵያ ያለው አገዛዝ የተባበሩት መንግስታት የሰብአዊ መብት መርማሪዎች በሀገሪቱ እየተፈጸመ ያለውን የሰብአዊ መብት ጥሰት እንዲያጣሩ እስከሚቀጥለው ወር ድረስ የማይፈቅድ ከሆነ ነው። የኢትዮጵያ አሜሪካውያን ሲቪክ ካውንስል ከሌሎች የማህበረሰቡ ተወካዮችና ድርጅቶች ጋር በመሆን ትላንት ከአሜሪካ ምክር ቤት አባላትና ከተባበሩት መንግስታት ድርጅት የሰብአዊ መብት ኮሚሽን ተወካይ ጋ ኤች አር 128 ሕገ ውሳኔ ስለሚጸድቅበት መንገድ ተወያይተዋል። ውይይቱ በአሜሪካ የተወካዮች ምክር ቤት የአብላጫ ወንበር ያለው የሪፐብሊካን ፓርቲ መሪ ኬቨን ማካርቲ ከኢትዮጵያውያኑ ተወካዮች ጋር ተገናኝተው ለመነጋገር በጠየቁት መሰረት የተካሄደ መሆኑን ለመረዳት ተችሏል። በቀጣዩ ወር ማለትም እስከ የካቲት 8 ድረስ በኢትዮጵያ ያለው አገዛዝ የተባበሩት መንግስታት አጣሪ ቡድን በሃገሪቱ ገብቶ የተፈጸሙ የሰብአዊ መብት ጥሰቶችን እንዲያጣራ ፍቃድ እንዲሰጥ ቀነ ገደብ ለማስቀመጥ ስምምነት ላይ መደረሱን የውይይቱ ተሳታፊዎች ከጋዜጠኞች ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ ተናግረዋል። አገዛዙ ለዚህ የማይተባበር ከሆነ ግን ኤች አር 128 በመባል የሚታወቀውና በኢትዮጵያ የሰብአዊ መብት እንዲከበርና የመብት ጥሰት የፈጸሙትን በሕግ ተጠያቂ የሚያደርገው ሕግ በአሜሪካ ምክር ቤት እንዲጸድቅ እንደሚደረግ ለማወቅ ተችሏል። የሕገ ውሳኔው ዋና አዘጋጅ የሆኑት የምክር ቤቱና የውጪ ጉዳይ ኮሚቴ አባል ክሪስ ስሚዝ የተባበሩት መንግስታት መርማሪዎች ሙሉ ለሙሉ በፈለጉበት ቦታ ተንቀሳቅሰው የተፈጸሙትን የሰብአዊ መብት ጥሰቶች እንዲያጣሩ አገዛዙ የማይፈቅድ ከሆነ ሕጉ በአስቸኳይ ይጸድቃል ብለዋል። ይህም ብቻ ሳይሆን ክሪስ ስሚዝ እንዳሉት በመብት ጥሰቱ ተሳታፊ የሆኑ ግለሰቦችን በአለም አቀፉ ማግንትስኪ የሰብአዊ መብት ሕግ መሰረት በሕግ እንዲጠየቁ እንደሚደረግ አስታውቀዋል። ሌላው የምክር ቤት አባል ማይክ ኮፍማን እንዳሉት ደግሞ አሜሪካ ለረጅም ጊዜ ከአገዛዙ ጋር ይላትን የጸጥታ ትብብር ሰበብ በማድረግ እየተፈጸሙ ያሉ የሰብአዊ መብት ጥሰቶችን ችላ ስትል መቆየቷ አግባብ እንዳልነበር ተናግረዋል። አገዛዙ ሕዝቡን እያሸበረ አሜሪካ ትብብሯን መቀጠሏ አግባብ አይደልም ሲሉ ተደምጠዋል። በኢትዮጵያ አሜሪካውያን ሲቪክ ካውንስል ተወካይ ዲያቆን ዮሴፍ ተፈሪ በበኩላቸው በውይይቱ ወቅት በምክር ቤቱ የአብላጫ ወንበር ያለው የሪፐብሊካን ፓርቲ መሪ ኬቨን ማካርቲ እንደተገኙና እሳቸውም በኢትዮጵያ ያለውን የመብት ረገጣ በቅርብ እንደሚከታተሉት ገልጸውላቸዋል። ኬቨን ማካርቲ ሕጉን የማስቆም ፍላጎት እንደሌላቸው ይሁን እንጂ አገዛዙ አንድ እድል እንዲሰጠው እንደሚፈልጉ ተናግረዋል ብለዋል። በዚህም መሰረት የተባበሩት መንግስታት ድርጅት መርማሪዎች ፍቃድ የማያገኙ ከሆነ ሕጉን ተግባራዊ ለማድረግ ስምምነት ላይ ተደርሷል ብለዋል። በውይይቱ ላይ የተገኙት የተባበሩት መንግስታት የሰብአዊ መብት ኮሚሽን ተወካይም አገዛዙ ለጥያቄው አዎንታዊ መልስ የሚሰጥ ከሆነ የኮሚሽኑ ባለሙያዎች ወዲያውኑ የማጣራት ስራቸውን እንደሚጀምሩ ተናግረዋል።

Friday, October 20, 2017

በአሜሪካ በዲሞክራሲና ነጻነት ላይ የሚሰራ ድርጅት ባልደረባ በኢትዮጵያ ያለውን የሰብአዊ መብት ጥሰት አሰቡ

Bildergebnis für HR 128

በኢትዮጵያ ያለው አገዛዝ በጸረ ሽብርተኝነት አጋርነት ከአሜሪካ ጋር መተባበሩን እንደመደበቂያነት ተጠቅሞ እየፈጸመ ካለው የሰብአዊ መብት ጥሰት እንዲቆጠብ በአሜሪካ በዲሞክራሲና ነጻነት ላይ የሚሰራ ድርጅት ባልደረባ አስታወቁ።
በአሜሪካ ኮንግረስ ተረቆ የሚገኘውን ኤች አር 128 በሚባል የሚታወቀውን ህገ ውሳኔ አሜሪካ በአስቸኳይ ማጽደቅ አለባት ሲሉም ተናግረዋል።
በአሜሪካ በዲሞክራሲና ነጻነት ላይ በሚሰራው ፍሪደም ሀውስ በተባለው ድርጅት ውስጥ የአፍሪካ ፕሮግራም ኦፊሰር የሆኑት ዮሴፍ ባድዋዛ በድርጅቱ የመረጃ መረብ በለቀቁት ጽሑፍ በኢትዮጵያ ያለው አገዛዝ የጸረ ሽብር አጋር ስለሆነ ብቻ በተቃዋሚዎቹ ላይ እየፈጸመ ያለውን ግድያና እስር አሜሪካ በዝምታ ማለፍ የለባትም።
ኤች አር 128 የተባለውን ሕገ ውሳኔ በአፋጠኝ በማሳለፍ አገዛዙ እየፈጸመ ላለው የሰብአዊ መብት ጥሰት ተጠያቂ እንዲሆን ማድረግ ያስፈልጋል ብለዋል።
በኢትዮጵያ ያለው አገዛዝ በገዛ ዜጎቹ ላይ ወንጀል የሚፈጽም እንዲሁም በአገዛዙና በሕዝቡ መካከል ጤናማ ግንኙነት በሌለበት ሁኔታ ኢትዮጵያ የአሜሪካ የጸጥታ አጋር መሆን አትችልም ብለዋል።
ኤች አር 128 ሕግ የሚወጣ ከሆነ ኢትዮጵያ ከአሜሪካ ጋር ያላትን የጸረ ሽብር ትብብር ታቋርጣለች በማለት በቅርቡ በአገዛዙ እየተሰጠ ያለውን የውሸት ማስፈራሪያ አሜሪካ ቸል በማለት ጠንካራና የማያወላውል አቋሟን ማሳየት አለባት።
ይህም በኢትዮጵያም ሆነ በአፍሪካ ቀንድ ሰላምና መረጋጋትን ለመጠበቅና እያንዣበበ ያለውን ቀውስ ለመከላከል ወሳኝ አስተዋጽኦ ይኖረዋል ሲሉ ዮሴፍ ባድዋዛ ጽፈዋል።
ሕጉን በማጽደቅ አሜሪካ ኢትዮጵያ ላለው አገዛዝ ጠንከር ያለ መልዕክት ልታስተላልፍ ትችላለች ሲሉም አስፍረዋል።
የአሜሪካ የህግ መወሰኛ ምክር ቤት አባላት የጸረ ሽብር ትብብር አቆማለሁ የሚለውን የኢትዮጵያ መንግስትን የውሸት ማስፈራሪያ ወደ ጎን በመተው ሕጉን በአስቸኳይ ማጽደቅ አለባቸው ብለዋል።
በአሜሪካ ኮንግረስ የኮሎራዶ ተወካይ ማይክ ኮፍማን በቅርቡ በዋሽንግተን ዲሲ የኢትዮጵያውን አምባሳደር ባናገሩበት ወቅት ሕጉ የሚጸድቅ ከሆነ ሀገሪቱ የጸረ ሽብር ትብብሯን ታቋርጣለች እንዳሏቸው በኮሎራዶ ለሚገኙ የኢትዮጵያ ማህበረሰብ አባላት መናገራቸውን ጽሑፉ አስታውሷል።
ጸሐፊው ሲያጠቃልሉም በኢትዮጵያ ያለው አገዛዝ መቼም ቢሆን እንዲህ አይነቱን ማስፈራሪያ እስከመጨረሻው ገፍቶበት አያውቅም። በጸረ ሽብሩ ላይ ላለመተባበር ቢወስን ማን እንደሚጎዳ ጠንቅቆ ያውቃል ብለዋል።

wanted officials