Which one you first choose? በቅድሚያ የሚፈልጉት

Showing posts with label ህወሃት. Show all posts
Showing posts with label ህወሃት. Show all posts

Tuesday, January 16, 2018

ኦብነግ የህወሃት ወታደሮችን መግደሉንና ማቁሰሉን አስታወቀ



የኦጋዴን ብሔራዊ ነጻነት ግንባር /ኦብነግ/ከኢትዮጵያ መንግስት ወታደሮች ጋር ባደረገው ውጊያ በርካታ ወታደሮችን መግደሉንና ማቁሰሉን አስታወቀ።
የኦጋዴን የዜና ወኪል የኦብነግን አባል ጠቅሶ እንደዘገበው ውጊያው የተካሄድው ታህሳስ 30/2010 ነው።
በሁለቱ ወገኖች መካከል በተደረገው ውጊያ በመንግስት በኩል ማርጋገጫ ባይገኝም የመንግስት ወታደሮች መገደላቸውና መቁሰላቸው ተመልክቷል።
በጃሌሎ መንደር ተደረገ በተባለው በዚህ ውጊያ ከወታደሮቹ መገደልና መቁሰል በተጨማሪ የጦር መሳሪያዎች፣ጥይቶችና የመገናኛ መሳሪያዎች መማረካቸው ተገልጿል።
በሁለቱ ወገኖች መካከል ተደረገ ስለተባለው ውጊያ ከገለልተኛ ወገን የተባለ ነገር የለም ።
ኦብነግ በተደጋጋሚ በኦጋዴን አካባቢ በህወህት ሰራዊት ላይ ጥቃት እየሰነዘረ እንደሚገኝ ይታወቃል።
ድርጀቱ ከዚህ ቀደም በነዳጅ ፍለጋ ላይ ተሰማርቶ በነበረው የቻይና ኩባንያ ላይ ጥቃት በመሰንዘር 74 የኩባንያው ሰራተኞችን መግደሉ ይታወሳል።
ይህንንም ተከትሎ የህወሃት አገዛዝ በሶማሌ ክልል መጠነ ሰፊ ወታደራዊ ዘመቻ ለመክፈት በሚል አካባቢውን ለአለማቀፍ መገናኛ ብዙሀንና የእርዳታ ድርጅቶች ዝግ በማድረግ የጅምላ ግድያና የሰብአዊ መብት ጥሰት መፈጸሙን የተለያዩ አለም አቀፍ የሰብአዊ መብት ተቋማት ሪፖርት ማድረጋቸው የሚታወስ ነው።

Thursday, December 7, 2017

የአፋር አብዮታዊ ዲሞክራሲያዊ አንድነት ግንባር አርዱፍ የህወሃትን ሰራዊት መቶ መለሰ


(ኢሳት ዜና–ሕዳር 29/2010)
የሕዝባዊ ወያኔ ሃርነት ትግራይ ሰራዊት የአርዱፍን ይዞታ ሰብሮ ለመግባት ያደረገው ሙከራ መክሸፉንና ተመቶ መመለሱን የአፋር አብዮታዊ ዲሞክራሲያዊ አንድነት ግንባር አርዱፍ አስታወቀ።
መብታችን እስኪከበር በሕወሃትና በመልዕክተኛው የአፋር ልዩ ፖሊስ ሃይል ላይ የጀመርነው ውጊያ ይቀጥላል ሲልም አስታውቋል።
የውጭ ሀገር ዜጎችና ጎብኚዎች አካባቢውን ለቀው እንዲወጡ አርዱፍ አስጠንቅቋል።
የብሔር ብሄረሰቦች በአል ሰላማዊ ሆኖ እንዲከበር በሚል በአርዱፍ ላይ የተከፈተው ዘመቻ ከአርዱፍ ተዋጊዎች አልፎ በሰላማዊ ዜጎች ላይም የተነጣጠረ እንደሆነ ግንባሩ አስታውቋል።
በዚህም ሰላማዊ የአፋር ተወላጆች ሰቆቅና እስራት እየተፈጸመባቸው እንደሆነም በመግለጫው ተመልክቷል።
ከነሀሴ ወዲህ 580 ሰዎች በሕገ ወጥ መንገድ ተይዘው በተለያዩ ስፍራዎች መታሰራቸውንም አርዱፍ አስታውቋል።
የሕዝባዊ ወያኔ ሃርነት ትግራይ ሰራዊት ከአፋር ክልል ልዩ ሃይል ፖሊስ ጋር በመሆን፣በህዳር ወር ሶስተኛ ሳምንት በሞጎሮስ ተራራማ ስፍራ ላይ የተጀመረው ውጊያ እንደ አውሮፓውያኑ እስከ ታህሳስ 3/2017 መቀጠሉን በመግለጫው ዘርዝሯል።
የሕወሃት ሰራዊት የአርዱፍን ይዞታ ሰብሮ ለመግባት ያደረገ ሙከራ ባለፈው እሁድ ሙሉ በሙሉ መክሸፉንና ተመተው መመለሳቸውን ይፋ አድርጓል።
በዚህም 17 ወታደሮች ሲገደሉ በደርዘኖች የሚቆጠሩ ቆስለዋል ሲል በመግለጫው አስታውቋል።
የአፋር አብዮታዊ ዲሞክራሲያዊ አንድነት ግንባር አርዱፍ መብቱ እስኪከበር ውጊያውን አጠናክሮ እንደሚቀጥልም ሕዳር 28/2010 ባወጣው መግለጫ አስታውቋል።
በአፋር ክልል የሚገኙ የውጭ ሀገር ኩባንያዎች እንዲሁም ጎብኝዎች ለደህንነታቸው ሲሉ አካባቢውን ለቀው እንዲወጡ ጥሪ አቅርቧል።
አዳዲስ ጎብኚዎችም ወደ አካባቢው እንዳይጓዙ አስጠንቅቋል።
የአፋር አብዮታዊ ዲሞክራሲያዊ አንድነት ግንባር አርዱፍ በአፋር ክልል ለ7 ጊዜያት ያህል ጎብኝዎችን እያገተ በድርድር ሲፈታ ቆይቷል።
በዚህም አለም አቀፍ እውቅና ያገኘ ሲሆን ባለፈው እሁድ በአፋር ክልል ከተገደሉት ጀርመናዊ ጎብኚ ጋር በተያያዘም የስርአቱ ደጋፊ መገናኛ ብዙሃን አርዱፍን ተጠያቂ ማድረጋቸው ይታወሳል።

wanted officials