Which one you first choose? በቅድሚያ የሚፈልጉት

Tuesday, November 4, 2014

በምእራብ አርማጭሆና በመተማ የአንድነት ፓርቲ አደራጆች ጭካኔ በተሞላበት መንገድ ታፍነው ተወሰዱ

በምእራብ አርማጭሆና በመተማ የአንድነት ፓርቲ አደራጆች ጭካኔ በተሞላበት መንገድ ታፍነው ተወሰዱ

ጥቅምት ፳፬(ሃያ አራትቀን ፳፻፯ / ኢሳት ዜና :-ከአዲስ አበባ የተላኩ የፌደራል ፖሊስ አባላትና ደህንነቶች፣ ወደ ፓርቲው መሪዎች ቤት ከንጋቱ አስራ አንድ ሰአት ላይ በመሄድ፣ መኖሪያ ቤቶቻቸውን ሰብረው በመግባትና አንዳንዶችንም ጭካኔ በተሞላበት ሁኔታ በመደብደብ አፍነው ወዳልታወቀ ቦታ ወስደዋቸዋል።

የመተማ ወረዳ ሰብሳቢ የሆኑት አቶ በላይነህ ሲሳይ፣ የምእራብ አርማጭሆ ወረዳ ሰብሳቢ አቶ አንጋው ተገኝ እንዲሁም የስራ አስፈጻሚ አባላት የሆኑት አባይ ዘውዱና እንግዳው ዋኘው ከተያዙት መካከል ይገኙበታል። የአቶ በላይነህ ቤት ከሌሊቱ 9 ሰአት የተከበበ ሲሆን፣ አቶ በላይ ሳይነጋ ቤቴን አልከፍትም በማለት፣ ከንጋቱ 11 ሰአት ላይ ቤቱን ሰብረው ገብተው ወስደውታል። ቤተሰቡ በፌደራል ወታደሮች ድርጊት በእጅጉ ተዳንገጠዋል።
ከንጋቱ 11 ሰአት ሲሆን በአብራጅራ የአንድነት ፓርቲ አመራር በሀነው በአቶ አንጋው ተገኝ ቤት የተገኙት የፌደራል ፖሊሶች፣ ቤቱን እንዲከፍት ሲጠይቁ፣ እስኪነጋ እንዲታገሱት ቢጠይቅም፣ ወታደሮቹ በሩን ሰብረው በመግባት ክፉኛ ደብድበው ወስደውታል። አቶ አንጋው ክፉኛ በመደብደቡ ወታደሮች አንስተው መኪና ላይ እንደጫኑት የአይን እማኞች ገልጸዋል።
ወጣት አባይ ዘውዱን ሊይዙ የሄዱት ፖሊሶች ከቤተሰቦቻቸው በደረሰባቸው ተቃውሞ ውዝግብ ፈጥረው የቆዩ ቢሆንም፣ በመጨረሻ ግን በሃይል መውሰዳቸውን ቤተሰቦች ተናግረዋል።
ለቤተሰቡ ብቸኛ የሆነውንና ከዚህ ቀደም ስራ በመከልከልና በእስራት ከፍተኛ እንግልት ሲደርስበት የነበረውን ወጣት አባይን ላለማስወሰድ ሲማጓቱ የነበሩ ሁለት እህቶቹ በሰደፍ በመመታታቸው በአሁኑ ጊዜ ጤና ጣቢያ ውስጥ መተኛታቸውን ቤተሰቦች ገልጸዋል። አንደኛዋ ጡቷ ስር በሰደፍ ስትመታ ሌላኛዋም ተመሳሳይ ጉዳት ደርሶባት ፈሳሽ ምግብ ወይም ግሉኮስ ተተክሎላት ህክምና እየተደረገላት ነው።  በአካባቢው ህዝብ ዘንድ ከፍተኛ ተቀባይነት ያላቸው ሶስቱ የፓርቲው አመራሮች በተያዙበት ወቅት ነዋሪው ተቃውሞ በማሰማት ውሳኔውን ለማስቀልበስ ጥረት ቢያደርግም ሳይሳካ ቀርቷል። ይሁን እንጅ ድርጊቱ የህዝብ ቁጣ መቀስቀሱን ነዋሪዎች ይናገራሉ።
አቶ አንጋው ተገኝ ከዚህ በፊት በከፍተኛ ሁኔታ  ተደብድቦ ታስሮ መፈታቱ ይታወቃል። አባይ ዘውዱም ኤርትራ ካሉ ተቃዋሚዎች ጋር ትገናኛለህ በሚል ከወር በፊት በመከላከያ አባላት ተይዞ በህዝብ ተቃውሞ እንዲፈታ መደረጉ ይታወቃል።  ሁለቱም መሪዎች ስለሚደርስባቸው እንግልት በቅርቡ ለኢሳት ቃለምልልስ መስጠታቸው ይታወቃል።
ገዢው ፓርቲ የሃይል አፈናውን  አጠናክሮ መቀጠሉን የሰሜን ጎንደር አንድነት ፓርቲ የአመራር አካል የሆኑት አቶ ሙላት ፍሰሃ ተናግረዋል በደቡብ ጎንደር ደግሞ የፎገራ ወረዳ የአንድነት ሰብሳቢ የሆኑት አቶ አለበል ዘለቀ ከሚሰሩበት የእርሻ ቦታቸው ላይ በፌዴራል በፖሊስ ተይዘው ወዳልታወቀ ቦታ ሲወሰዱ፣ በምዕ/ጎጃም ደጋ ዳሞት ወረዳ የወረዳው ሰብሳቢ አቶ ጥላሁን አበበና 3 የአንድነት አባላት ከቤታቸው በፌዴራል ፖሊስ ተይዘው ወዳልታወቀ ቦታ ተወስደዋል።
ከትናንት በስቲያ ደግሞ የምእራብ ጎጃም የመኢአድ ዋና ጸሃፊ አቶ ጌታቸው መኮንንና የፓርቲው ዋና ጸሃፊ የነበሩት አቶ ተስፋየ ታሪኩ  ተይዘው መታሰራቸው መዘገቡ ይታወቃል።  የወላይታ ዞን የአንድነት ፓርቲ ሰብሳቢ አቶ ማሞ ገሞ እና የዞኑ ድርጅት ጉዳይ ኃላፊ አቶ ወኖ በዳሳ ጥቅምት 22 ቀን 2007 ዓ.ም በወላይታ ሶዶ ከተማ በአንድ ሆቴል ውስጥ እያሉ በከተማው የፖሊስ አዛዥ መመሪያ በመንግስት ሀይሎች ከባድ ድብደባ እንደተፈፀመባቸው የፓርቲው የድርጅት ጉዳይ ለፍኖተ ነፃነት መናገራቸው መዘገቡ ይታወሳል።

ግንቦት7 በጣሊያን ከሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ጋር የተሳካ ስብሰባ ማካሄዱን ገለጸ

ግንቦት7 በጣሊያን ከሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ጋር የተሳካ ስብሰባ ማካሄዱን ገለጸ

ጥቅምት ፳፫(ሃያ ሦስትቀን ፳፻፯ / ኢሳት ዜና :-ድርጀቱ እሁድ እለት በሮም ባካሄደው ስበሰባ ላይ በርካታ ኢትዮጵያውያን ተገኝተው ድርጅቱን ወክለው ከተገኙት ከአቶ አበበ ቦጋለ ጋር ውይይት አድርገዋል።
የፖለቲካ ድርጅቶች በጣሊያን ስብሰባ ሲያደርጉ ባይታይም፣ ግንቦት7 ያካሄደው ስብሰባ ግን የተሳካ እንደነበር ያዘጋጅ ኮሚቴው ሰብሳቢ ሮዛ ተስፋየ ለኢሳት ተናግራለች።
በውይይቱ ላይ የተገኙት አብዛኞቹ ኢትዮጵያውያን ግንቦት7 ከኤርትራ ጋር ስላለው ግንኙነት ጥያቄዎችን ያነሱ እንደነበር አዘጋጆቹ ተናግረዋል።
በጣሊያን የተካሄደው ስብሰባ ድርጅቱ በመላው አለም እየዞረ ከሚያካሂደው ስብሰባ አንዱ አካል ነው።

ከፍተኛው ፍርድ ቤት በ16 የኦሮሞ ተወላጅ ተማሪዎች ላይ ውሳኔ አስተላለፈ

ከፍተኛው ፍርድ ቤት በ16 የኦሮሞ ተወላጅ ተማሪዎች ላይ ውሳኔ አስተላለፈ

ጥቅምት ፳፬(ሃያ አራትቀን ፳፻፯ / ኢሳት ዜና :-

 

የፌደራል ፍርድ ቤቱ ከአዲስ አበባ ማስተር ፕላን ጋር በተያያዘ ተይዘው በነበሩት ተማሪዎች ላይ ከ1 እስከ 5 በሚደርስ እስር እንዲቀጡ ውሳኔ አሳልፏል። በሌላ ዜና ደግሞ በአዳማ ቤታቸው የሚፈርስባቸው ሰዎች ባስነሱት ተቃውሞ ፖሊሶች ተጎዱ።
የአከባቢው ነዋሪዎች እንደገለጹት  ከከተማ አስተዳደሩ ቤት አፍራሽ ግብረ ሀይል  ህገወጥ የተባሉ ቤቶችን ለማፍረስ ወደ ስፍራው ቢንቀሳቀስም ወደ 1 ሺ የሚጠጋ ቁጥር ያላቸው ሰዎች ባስነሱት ተቃውሞ ፖሊሶች ጉዳት ደርሶባቸው ወደ መጡበት ተመልሰዋል። ጉዳት የደረሰባቸው ፖሊሶች በህክምና ላይ መሆናቸው ታውቋል።

የመኢአድ አባላት እየታደኑ በመታሰር ላይ ናቸው

የመኢአድ አባላት እየታደኑ በመታሰር ላይ ናቸው


ጥቅምት ፳፫(ሃያ ሦስትቀን ፳፻፯ / ኢሳት ዜና :-
መጪውን ምርጫ ተንተርሶ በሚመስል መልኩ በምስራቅና ምእራብ ጎጃም አመራሮችና አባላት መታሰራቸውን ድርጅቱ አስታወቀ
በተመሳሳይ ዜና ደግሞ የወላይታ ዞን የአንድነት ፓርቲ ሰብሳቢ አቶ ማሞ ገሞ እና የዞኑ ድርጅት ጉዳይ ኃላፊ አቶ ወኖ በዳሳ ጥቅምት 22 ቀን 2007 ዓ.ም በወላይታ ሶዶ ከተማ በአንድ ሆቴል ውስጥ እያሉ በከተማው የፖሊስ አዛዥ መመሪያ በመንግስት ሀይሎች “እኛ ሀገር እየመራን እናንተ ትቃወሙናላችሁ እናንተን እናጠፋቹሃለን” በማለት ከባድ ድብደባ እንደተፈፀመባቸው የፓርቲው የድርጅት ጉዳይ ለፍኖተ ነፃነት አስታውቀዋል፡፡ አመራሮቹ በድብደባው ከባድ ጉዳት እንደደረሰባቸውም ታውቋል፡፡
አቶ ወኖ በዳሳ ራሳቸውን ስተው በአምቡላንስ ወደ ሆስፒታል ቢወሰዱም እስካሁን እንዳላገገሙ እና የዞኑ የአንድነት ሰብሳቢ አቶ ማሞ ገሞ ህክምና አግኝተው ከወጡ በኋላም በከተማው ደህንነቶች ክትትልና ወከባ እየደረሰባቸው እንደሚገኝም ታውቋል፡፡
የወላይታ ዞን የአንድነት አመራሮች ላይ ድብደባ እንዲደርስ መመሪያ የሰጡት የከተማው የፖሊስ አዛዥ በአቶ ወኖ ላይ በደረሰው ከባድ ጉዳት ተደናግጠው በአምቡላንስ እንዲወሰዱ ካደረጉ በኋላ የዞኑ የአንድነት ሰብሳቢ አቶ ማሞ ገሞ “በአንድም ሚዲያ ስለሁኔታው እንዳይናገሩ” በሚል ክትትል እያስደረጉባቸው ያገኛል ሲል ፍኖተነጻነት ዘግቧል።

Monday, November 3, 2014

የወያኔ ግፍ በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ

26351fb59e29fb0a1375427042

ዘረኛዉ ወያኔና ባለሟሎቹ በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ በጋምቤላና በሸኮ መዠንገር አካባቢ የሚያካሄዱትን የማንአለብኝነት የመሬት ዝርፍያና ዜጎችን እርስ በርስ በማጋጨት ተጠቃሚ ለመሆን የሚያደርጉት አራዊታዊ ሩጫ የተነሳ ከፍተኛ ቁጥር ያለዉ ህዝብ ይህ ነዉ ተብሎ ሊነገር የማይችል እልቂት እየተፈጸመበት ነዉ። የመዠንገር ህዝብ የሞትና የህይወትን ያክል የማይወጣዉ ምርጫ ስለቀረበለት ተወልዶ ያደገበትን የአባቶቹንና የአያቶቹን አካባቢ ለቅቆ በመዉጣት እራሱን ለመከላከል ባደረገዉ እንቅስቃሴ የብዙ ንጹሃን ዜጎችና ቁጥራቸዉ ቀላል የማይባል ምስኪን ወታደሮችም ህይወት ማለፉ በይፋ እየተሰማ ነዉ። ይህንን ተከትሎ ግፈኞቹ የወያኔ መሪዎች በአካባቢዉ ብዙ ዘመን በቆዩ ብሄሰቦች መካክል ሆን ብለዉ ግጭት እንዲነሳ እያደረጉ በህዝብ መካክል ግጭትትና ዕልቂት የተነሳ በማስመሰል በአካባቢዉ ከፍተኛ ሰቆቃ በመፈፀም ላይ ይገኛሉ።
በዚህ በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ በተለያዩ አካባቢዎች እየደረሰ ላለዉ መጠነ ሰፊ ግጭትና ዕልቂት ተጠያቂዉ በአካባቢዉ ለዘመናት አብሮ በመደጋገፍ የኖረዉ ህዝብ ሳይሆን የዚህ አሰቃቂ ዕልቂት ባለቤትና ጠንሳሽ ህወሓትና ዘረኛ መሪዎቹ መሆናቸዉን ለአንድም ደቂቃ ሊዘነጋ አይገባም። ይህ ግጭት ሊነሳ የቻለዉ ህወሓት የአካባቢዉን ደሃ ገበሬ ከትዉልድ መሬቱ ላይ እያፈናቀለ መሬቱን ለከፍተኛ የጦር መኮንኖቹና የኔ ለሚላቸዉ ባለሟሎቹ በማከፋፈሉ መሆኑን ይህንን ግፍ የሚሰማ ኢትዮጵያዊ ሁሉ ልብ ሊለዉ ይገባል። ህወሃት የአማራን ተወላጆች አካባቢዉ የእናንተ አይደለምና ዉጡ እያለና እያፈናቀለ በሌላ በኩል ግን በየክልሉ የአካባቢዉን ነዋሪ እያፈናቀለ የራሱን ሰዎች የመሬት ባለቤት ማድረጉ አዲስ የጀመረዉ ክስተት ሳይሆን ቆየት ያለና ስር የሰደደ የወያኔ አሰራር ነዉ።
ይህ ዛሬ በጋምቤላና በአካባቢዋ እየደረሰ ያለዉ ግፍና መከራ ለአካባቢዉ ህዝብ ብቻ የሚተዉ ነጠላ ችግር ሳይሆን በአጠቃላይ ወያኔ በአገራችን ላይ ሆን ብሎ በማድረስ ላይ ያለዉ ችግርና መከራ አካል ነዉ። በጋምቤላ ዉስጥ የፈሰሰዉና እየፈሰሰ ያለዉ የሴቶች፤ የወጣቶች፤ የአረጋዉያንና የህጸናት ደም ለሁላችንም የነጻነት ጥሪ እያቀረበልን ነዉ። ይህ የነጻነት ጥሪ ሰምተን የምናልፈዉ ወይም ነገ እንደርሳለን በለን በቀጠሮ የምናልፈዉ ጥሪ አይደለም። ጥያቄዉ የአገርና የዜጎች ህልዉና ጥያቄ ነዉና ነገ ዛሬ ሳንል አሁኑኑ ይህንን የነጸነት ጥሪ ሰምተን ምላሽ ልንሰጠዉ ይገባል።
ይህ ወያኔ በደቡብ ደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ዉስጥ በንጹሃን ዜጎቻችን ህይወት ላይ እየፈጸመ ያለዉ ግፍ በአገራችን ህዝብ ላይ ሲደርስ የመጀመሪያዉ አይደለም፤ ካላቆምነዉ በቀር የመጨረሻዉ እንደማይሆንም አካሄዱ በግልጽ እያሳየን ነዉ። ወያኔ ጋምቤላ ዉስጥ ለምለም መሬት እየፈለገና ነዋሪዉን እያፈናቀለ መሬቱን ለባለሟሎቹ ማደሉን ሳይታቀብ በማንለብኝነት እንደቀጠለበት ነዉ። መሬቱን የተቀማዉ ደሃዉ የጋምቤላ ገበሬም ጫካ እየገባ ከወያኔ ጋር መተናነቁን ቀጥሏል። ትናንት በኦሮሚያ፤ በጉራፈርዳና በቤንሻንጉል አካባቢዎች በአማራ ተወላጆች ላይ የደረሰዉ ግፍና መከራ ዛሬ ደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ዉስጥ በተለያዩ ብሄረሰቦች ላይ እየደረሰ ነዉ።
ግንቦት 7 የፍትህ፤ የነጻነትና የዲሞክራሲ እንቅስቃሴ ይህ ለከቱን የለቀቀ የህወሓት ዕብሪት እንዲተነፍስና በወገኖቻችን ላይ የሚደርሰዉ ግፍና ሰቆቃ እንዲቆም እያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ ነግ በኔ እያለ የነጻነት ትግሉን እንደቀላቀል የትግል ጥሪ ያደርጋል። ወያኔ እያደረሰ ያለዉ እስራት፤ ድብደባ፤ ግድያና ስደት የሁላችንንም ቤት እያንኳኳ ነዉና ሁላችንም እንደ አንድ ሰዉ ቆመን ወያኔንና ወያኔ የፈጠረዉን ዘረኛ ስርዐት በትግላችን መደምሰስ አለብን። በጋምቤላና በተለያዩ የአገራችን አካባቢዎች የፈሰሰዉ የንጹሃን ወገኖቻችን ደም ደመከልብ ሆኖ የማይቀረዉ ለመብታችንና ለነጻነታችን ቆመን ወያኔን ካስወገድን ብቻ ነዉ።
በህብረት እንነሳ!!!!

Burkina Faso: A warning to other African leaders


Burkinfaso

NAIROBI – Violent clashes in Burkina Faso that led to the overthrow of the president are a stark warning to other African leaders pushing constitutional change to hang on to power, analysts say.

Chaos in Burkina Faso erupted this week as lawmakers prepared to vote to allow 63-year-old Blaise Compaore — who took power in a 1987 coup — to contest elections in November 2015.
While Compaore was forced out Friday, Burkina Faso is far from alone in having a president reluctant to relinquish office.

“It is a warning both to ageing regimes and for those trying to stay in power beyond constitutional limits,” said Thierry Vircoulon of the International Crisis Group (ICG).
“During the Arab Spring the question was whether Africa will have its own spring? Perhaps the attempts to change the constitutions will lead to it now.”
Countries including Benin, Burundi, Congo-Brazzaville, the Democratic Republic of Congo and Rwanda are all reportedly pondering change to allow their leaders a third term.
But the impact of events in Ouagadougou, and the storming of its parliament, may give several leaders across the continent “pause for thought”, said Paul Melly from Britain’s Chatham House.
“Burkina Faso has demonstrated that in today’s Africa popular acquiescence cannot be taken for granted,” Melly said.

– ‘Wake-up call for presidents’ –
Burkina Faso is far from the first country where heads of state seeking to extend their rule have been challenged.
In Niger, Mamadou Tandja was ousted by the army in 2010 after a third-term bid, while in contrast, Senegal’s President Abdoulaye Wade lost 2012 elections despite winning constitutional permission to run three times.
Some have carried it off. Cameroon’s Paul Biya, in power since 1982, successfully changed laws for another term in 2011, but the strongman had ensured the opposition was quashed.
Other nations were laws have been tinkered with to the benefit of their leaders include Algeria, Angola, Chad, Djibouti and Uganda.

But events in Ouagadougou may ring alarm bells for others.
“The evolving situation in Burkina Faso will hopefully serve as a wake-up call for presidents who are considering tailoring the constitution to suit their own interests, in west Africa and beyond,” said David Zounmenou, from the South African-based Institute for Security Studies (ISS).
And while the African Union sanctions those who make constitutional changes for the purpose of staying in power, such threats have had little impact, Zounmenou added.
Countries vary and not all leaders have been in power for as long as the 27 years Compaore lasted, Vircoulon said, noting that a crucial factor would be “the state of mind” of the people.
In tightly controlled Rwanda, allies of strongman President Paul Kagame have called for referendum to change the constitutional to allow him to run in 2017.
In contrast, the political climate in neighbouring Burundi is far more volatile for President Pierre Nkurunziza, who is expected to defy critics to run for a third term next year.
“Authoritarian traditions are still influential in some countries,” Melly said. “Few would bet against Kagame or Congo-Brazzaville’s Denis Sassou-Nguesso successfully pushing through a rule change to open their way to further terms of office.”
For others however the risks are greater.
Burundi’s Nkurunziza and DR Congo’s Joseph Kabila might “be “tempted to follow suit –- although for them it could be a higher risk exercise, governing countries with vocal civil society and state machines of limited establishment power,” Melly added.
And while Compaore’s fall may provide a lesson to some, many will still be tempted.
It is “up to the citizens to take responsibility to counter these political adventurers who undermine democracy and the promotion of lasting peace,” Zounmenou added, lamenting Africa’s reputation as a place of non-stop crises.

“It is time to change that, to make democratic structures outside individual politicians to allow socio-economic development,” he said.

ETHIOPIANS IN EASTERN UKRAINE NEED URGENT HELP

ETHIOPIANS IN EASTERN UKRAINE NEED URGENT HELP

Ethiopians living in Eastern Ukraine,Donetsk, for the last ten to more than 20 years are
in a dire situation and need urgent assistance. Ordinarily their plight was already
unbearable as they had to suffer unemployenent and crude racism.
The Ethiopians and their families do not have anyone to turn to as they are ebeaten and
mistreated be it by the "independentists" or by the Kiev forces. The refugees state : "we
and our children’s unable to walk on the streets even during day time, there is no
regular shopping, no school, no work and thus there is no means of life; our work
places are closed. We do not have other places to go and pass those hard times; no
relatives to shelter us.’’ The refugees and their families listed below are in need of
urgent help, of resettlement in other countries before they become innocent war victims.
SOCEPP is writing to European and North American leaders to come to the rescue of
the Ethiopians in Donetsk

INJUSTICE ANYWHERE IS INJUSTICE EVERYWHERE
SOCEPP, 30 RIGA COVE, WINNIPEG, MB
R2P 2Z7, CANADA
E MAIL: SOCEPP @AOL.COM or socepp@socepp.info
WEB SITE: www.socepp.info

NOVEMBER 3/2014
ETHIOPIANS IN EASTERN UKRAINE NEED URGENT HELP

Ethiopians living in Eastern Ukraine,Donetsk, for the last ten to more than 20 years are
in a dire situation and need urgent assistance. Ordinarily their plight was already
unbearable as they had to suffer unemployenent and crude racism.
The Ethiopians and their families do not have anyone to turn to as they are ebeaten and
mistreated be it by the "independentists" or by the Kiev forces. The refugees state : "we
and our children’s unable to walk on the streets even during day time, there is no
regular shopping, no school, no work and thus there is no means of life; our work
places are closed. We do not have other places to go and pass those hard times; no
relatives to shelter us.’’ The refugees and their families listed below are in need of
urgent help, of resettlement in other countries before they become innocent war victims.
SOCEPP is writing to European and North American leaders to come to the rescue of
the Ethiopians in Donetsk.
Name DOB Address
Alemu Wondu Tefera 27/08/1968 Donetsk
Alemu Yana Viktorovna 31/12/1985 Donetsk
Alemu Elizabeth Tefera 24/03/2007 DonetskINJUSTICE ANYWHERE IS INJUSTICE EVERYWHERE
SOCEPP, 30 RIGA COVE, WINNIPEG, MB
R2P 2Z7, CANADA
E MAIL: SOCEPP @AOL.COM or socepp@socepp.info
WEB SITE: www.socepp.info
Alemu Gabriel Tefera 30/01/2011 Donetsk
Haile Zereihun Abayneh 02/12/1989 Donetsk
Abayneh Alisa Zereihunovna 03/12/1989 Donetsk
Aredo Negga Mengistu 12/09/1965 Donetsk
Aredo Pavlina Anatolevna 31/05/1968 Donetsk
Aredo Diana Mengistovna 10/07/1994 Donetsk
Girma Tesfaye W/Gabriel 28/03/1969 Donetsk
Girma Natalia Leondovna 22/09/1993 Donetsk
Girma Daniel Tesfaye 18/03/1993 Donetsk
Girma Ted Tesfaye 28/09/2000 Donetsk
Halil Nazerath Ahmedin 1989 Donetsk
Halil Maksim Ahmedin 1995 Donetsk
Halil Ahmedin Hadra 1967 Donetsk
Volkovskaya Belachew Lina
Vyacheslavovna
12/08/1975 Donetsk
Belachew Maichael 17/01/2000 Donetsk
Belachew Dominika Tamiru 20/01/2007 Donetsk
Ratieva Olga Alexandrovina 07/04/1979 Donetsk
Orykhun Yeva 08/02/2003 Donetsk
Dagnew Orykhun 09/09/1969 Donetsk
Emma Dagnew 06/03/2014 Donetsk
Tefera Habtu Yimam 03/05/1966 DonetskINJUSTICE ANYWHERE IS INJUSTICE EVERYWHERE
SOCEPP, 30 RIGA COVE, WINNIPEG, MB
R2P 2Z7, CANADA
E MAIL: SOCEPP @AOL.COM or socepp@socepp.info
WEB SITE: www.socepp.info
Tefera Amina Zahirovna 25/08/1974 Donetsk
Tefra Khelen Habtu 25/01/1995 Donetsk
Tefera Sabina Habtu 24/03/2001 Donetsk
Tessema Girma 1970 Donetsk
Gaidai Eugenia Victorovna 1985 Donetsk
Gemedo Rabo Belda 10/03/1967 Donetsk
Karolina Ivanovna Vishnyakova 27/07/1969 Donetsk

ወያኔ/ህወሓት ያደራጃቸው ምሊሽያዎች በአፋር ነዋሪዎች ላይ ተኩስ ከፈቱ

ወያኔ/ህወሓት ያደራጃቸው ምሊሽያዎች በአፋር ነዋሪዎች ላይ ተኩስ ከፈቱ

  • 852
     
    Share
አኩ ኢብን አፋር ለዘ-ሐበሻ እንደዘገበው፦
ትናንት ማክሰኞ 18/02/2007 በአፋር ክልል በሰሜናዊ ዞን በኮናባ ወረዳ በትግራይ ታጥቂ ሚሊሻዎች በኮናባ ፈራስዳገ ቀበሌ ነዋሪዎች ላይ ጦርነት የከፈቱ ሲሆን ቦታውን በቶክስ እሩምታ ሲያምሱት ማርፈዳቸውን ከቦታው የሚወጡ መረጃዎች ጠቁመዋል። ይሁን እንጂ ለጊዜው ከአፋር ነዋሪዎች በኩል የቶክስ ምላሽ አላገኙም! ከቀኑ 8:00 ሰዓት ሲሆን የተጀመረው ይህ ቶክስን ተከትሎ ከኮናባ ወረዳ ብዙ ወጣቶች ተሰብሰበው በፍጥነት ወደ ቦታው የደረሱ ሲሆን በዛን ጊዜ የኔትዎርክ አገልግሎት ወዲያው ተቋርጧል። እስካሁን ከአፋር ነዋሪዎች በኩል የተተኮሰ አንድ ጥይት የለም።
afar
የቦታው ምንጮች አያይዘውም «ይህ ደግሞ የአፋር ወጣቶች ለሰላም ካላቸው ፍላጎት የተነሳ ነው። ነገር ግን አስገዳጅ ነገር ከተፈጠረ የሚደርስባቸውን ጥቃት ለመከላከል ከየቦታው ተሰብስበው ዝግጅት ላይ ናቸው።» ብለዋል። ከኮናባ አንድ ስሙን ሊናገር ያልፈለገ ወጣት እንደነገረኝ «ይሄ በህወሓት ሆን ተበሎ የሚደረግ ትንኮሳ በመሆኑ የአፋር ወጣቶች በበሰለ አስተሳሰብ ለሰላም ያላቸው ፈለጎት በትዕግስት አሳይተዋል።» ብሏል። አያይዞም «ኔትወርክ ራሱ የጠፋው ለሌሎች መረጃ እንዳይደርስና የአፋር ህዝብ እንዳይነሳ በመፍራት ነው» ሲል አክሏል። አሁንም ቦታው ውጥረት እንዳለ መረጃዎች ይጠቁማሉ።
በዚህ ጉዳይ ላይ የኮናባ ወረዳ የፀጥታ ቢሮ ኃላፊን አስተያየት ለማካተት ያደረኩት ተደጋጋሚ ሙከራ አልተሳካም።
-- Ze-Habesha Website 

በተለያዩ ክልሎች ሙስሊም ሴት ተማሪዎች ሂጃባችሁን አውልቁ በሚል ከትምህርታቸው እየተፈናቀሉ ነው

በተለያዩ ክልሎች ሙስሊም ሴት ተማሪዎች ሂጃባችሁን አውልቁ በሚል ከትምህርታቸው እየተፈናቀሉ ነው

በአሶሳ እና በሽሬ እንደስላሴ ከተማ የሚኖሩ 1ኛ እና 2ኛ ደረጃ ሙስሊም ተማሪዎች ሂጃባችሁን አውልቁ በሚል ከትምህርት ገበታቸው እየተፈናቀሉ እንደሚገኙ ተገለፀ::

አቡ ዳውድ ኡስማን
በቤኒሻንጉል ጉምዝ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት በአሶሳ ከተማ በሚገኙ የ1ኛ ደረጃ ት/ቤት የሚማሩ ሙስሊም ተማሪዎች ሂጃብ ለብሰው መማር እንዳይችሉ እየተደረጉ መሆናቸውን ምንጮች አስታወቁ፡፡
ፎቶ ከፋይል
በአሶሳ ከተማ በሚገኙ ት/ቤቶች ውስጥ ሙስሊም ሴት ተማሪዎች ሂጃብ ለብሰው በትምህርት ገበታቸው ላይ መገኘት እንደማይችሉ የት/ቤቱ አስተዳደሮች እየከለከሏቸው መሆኑ ታውቋል፡፡
በቤኒሻንጉል ጉምዝ በአሶሳ ከተማ በሚገኝ 1ኛ ደረጃ ት/ቤት 35 የሚሆኑ ሙስሊም ሴት ተማሪዎች ሂጃባችሁን ካላወለቃችሁ መማር አትችሉም በመባላቸው ከትምህርት ገበታቸው መፈናቀላቸውን ምንጮች አስታውቀዋል፡:
የትምህርት ቤቱን ርዕሰ መምህርን በጉዳዩ ላይ ለማነጋገር በአሶሳ ከተማ በስፋት በህዝብ ዘንድ የሚታወቀው ሰለፊያ ተብሎ የሚጠራው መስጂድ ኮሚቴዎች ሙከራ ያደረጉ ሲሆን ርዕሰ መምህሩ “እናንተ አሸባሪዎች እስካሁን አላቹ እንዴ” በማለት የተሳለቀባቸው ሲሆን ሴት ተማሪዎቹ ሂጃባቸውን እስካላወለቁ ድረስ በትምህርት ገበታቸው ላይ እንደማይቀጥሉ ምላሽ እንደሰጣቸው ታውቋል፡፡
በተመሳሳይም በትግራይ ክልል በሽሬ እንደስላላሴ ከተማ በሚገኙ 2ኛ ደረጃ ት/ቤቶች ውስጥ ሙስሊም ሴት ተማሪዎች ሂጃብ ለብሰው መማር እየተከለከሉ መሆናቸውን ምንጮች ዘግበዋል፡፡
በበሽሬ እንደስላሴ ከተማ የሚኖሩ በርካታ ቁጥር ያላቸው ሙስሊም ሴት ተማሪዎች ሂጃባችሁን አውልቃችሁ ተማሩ በመባላቸው ከትምህርት ገበታቸው ተፈናቅለው በቤት ውስጥ ተቀምጠው እንደሚገኙ ታውቋል፡፡
የትምህርት ቤት አስተዳደሮች የተማሪዎችን ወላጆች በመሰብሰብ በጉዳዩ ዙሪያ ያነጋገሩ ሲሆን ወላጆችን እና ተማሪዎችን ሲያስፈራሩ እንደነበር ተዘግቧል፡፡
በመላው ሃገሪቱ የሙስሊሞች ዋነኛ የእምነታቸው መገለጫ የሆነውን ሂጃብ እንዲያወልቁ ለማድረግ በመንግስት በኩል ከፍተኛ ስራ እየተሰራ ይገኛል፡፡ የፌደራል ጉዳዬች ሚኒስተር ዶ/ር ሽፈራው በኢስላም ላይ ባላቸው የግል ጥላቻ በመነሳት ከመሰሎቻቸው ጋር በመቀናጀት ሙስሊም ተማሪዎች ከትምህርት ገበታቸው ለማፈናቀል በክፍተኛ ደረጃ እየተንቀሳቀሱ እንደሚገኙ የሚታወቅ ሲሆን በመላው ሃገሪቱም በሴኩላሪዝም ሽፋን ሙስሊሞች ትምህርታቸውን አልያም ሃይማኖታቸውን እንዲመርጡ በማስገደድ ሙስሊሙን ከትምህርት ገበታ ለማራቅ ጥረት እየተደረገ ይገኛል፡፡
ሂጃብ የሙስሊም ሴት ህልውናዋ እንጂ ለድርድር የሚቀርብ የፖለቲካ አጀንዳ አይደለም።

Sunday, November 2, 2014

በልብ በሽታ የሚሰቃዩት አቶ በረከት ስሞኦን ለዳግም ህክምና ሳውዲ አረቢያ ሾልከው ገቡ

  • ኢትዮጵያን ሃገሬ ጅድ በዋዲ ለዘ-ሐበሻ እንደዘገበው
በልብ በሽታ የሚሰቃዩት አቶ በረከት ስሞን ህመሙ ጠንቶባቸው ከሁለት ወር በፊት በሼክ አላሙዲን የግል አውሮፕልና ተጭነው በድበቅ ለህክመና ሳውዲ አረቢያ መግባታቸው ይታወሳል። በወቅቱ ሳውዲ አረቢያ ጅዳ የሚገኝ አንድ «ቡግሻን» hospital እየተባለ የሚጠራ ሪፈራል ሆስፒታል የልብ ቧንቧ ማስፋት ህክምና ቢደረግላቸውም የባለስልጣኑ የጤነነት ሁኔታ የሚጠበቀውን ያህል ለወጥ ባለማሳየቱ ለዳገም ህክምና ቀጠሮ ተሰቷቸው ከሳምታት ቆይታ በሃላ ወደ ሀገር ቤት መመለሳቸውን መዘገባችን ይታወሳል ።
Bereket Simon weeping with his wife over Meles Zenawi's death
ይህ በዚህ እንዳለ ዛሬም የአቶ በረከት ጤንነት መልካም ሁኔታ ላይ እንዳልሆነ ምንጮች የሆስፒታሉን የምርመራ ውጤት አብነት ጠቅሰው ይናገራሉ ። አቶ በረከት በጤነታቸው መታወክ ፍጹም መረጋጋት እንደማይታይባቸው የሚገልጹት እንዚህ ውስጥ አዋቂዎች ቀደም ሲል ባለስልጣኑ ህክምና ላይ በነበሩበት ወቅት ወደ ሳውዲ አረቢያ በሚስጠር ለህክምና መግባታቸውን ተከትሎ በተለያዩ ድህረገጾች ዜናው በስፍት መናፈሱ በውስጣቸው በተፈጠረው አለመረጋጋት በልባቸው ምት አለመስተካከል በወቅቱ በቂ ህክማና መውሰድ እናዳልቻሉ ታውቋል። የአቶ በረከት የጤነንት ሁኒታ ዛሬም አስተማማኝ እንዳልሆነ የሚያውሱ እንዚህ የአይን እማኞች ከእለት ተዕለት የባለስልጣኑ የአካል መጠን በማይጠበቅ ሁኔታ መቀነስ እና የፊታቸው ገጽታ መለዋወጥ በውስጣቸው መልካም ነገር እንደማይታይ ያሳብቃል ብለዋል።
የአቶ በረከት ስሞኦን ህይወት ለመታደግ የአቅማቸውን ያህል ጠረት እያደረጉ የሚገኙ «ቡግሻን» hospital የሳውዲ አረቢያ ሆስፒታል ዶክተሮች ሰለበሽታው አደገኝነት ግንዘቤ በማስጨበጥ አቶ በረከት ከተለያዩ መጠጦች እና አይምሮ አደዛዥ እጾች መራቅ እንዳለባቸው እና የጤነንታቸው ሁኔታ አስተማማኝ ሁኔታ ከሲደርስ እረፍት መስውሰድ እንደሚገባቸው ሙያዊ ምክሮቻቸውን ለገሰዋቸዋል። ይህ በዚህ እንዳለ አቶ በረከት ለህክምና ወደ ሳውዲ አረቢያ ሲያቀኑ የህክምና ውጪያቸውን እየሸፈኑ ከሚገኙት ሼክ አላሙዲን ባሻገር ለኢ.ህ.አ.ዴ.ግ መንግስት ባለስልጣናት ሚስጠር መሆኑ አያሌ ወገኖችን በስፋት እያነጋገር ነው ። ከሁለት ወር በፊት አቶ በረከት እኩለ ለሊት ከቦሌ አይሮፕላን ማረፊያ ወደ ሳውዲ አረቢያ በሼክ አላሙዲን የግል አይሮፕልና በድብቅ ለህክማን መግባታቸው ለኢ.ህ.አ.ዴ.ግ ከፍተኛ ባለስልጣናት ወሬው የደረሰው እንደማንኛውም ኢትዮጵያዊ በዘ-ሃበሻ እና ጎልጉል ድህረገጾች በተለቅቁ መረጃዎች መሆኑን የሚናገሩ ምንጩች ለሁለተኛ ግዜ ዳግም ህክምና ወደ ሳውዲ አረቢያ ሲመለሱ በሼክ አልሙዲን በኩል በክበር «በፕሮቶኮል» ሊገቡ እንደሚቸል በወቅቱ ከጅዳ ቆንሳል ጽ/ቤት የወጡ መርጃዎች ቢያረጋግጡም የአቶ በረከት ስሞኦን እንደ ተለመደ በድብቅ ወደ ሳውዲ አረቢያ መግባት ባለስለስልጣኑ በውስጥም በውጨም ጥሩ ወዳጅ እንደሌላቸው የሚነገረውን ሃቅ ያጠናክረዋል ብለዋል ።
አቶ በረከት ትላንት በተደረገላቸው ምርመራ የቅርብ ክትትል እንደሚያሻቸው የሚገልጹ የሆስፒታል መረጃዎች ባለስልጣኑ የተሰጣቸውን ምክር እና የተለያዩ መደሃኒቶቻቸውን ይዘው ከሆስፒታሉ ውጭ ወደ ሚገኘው ምስጢራዊ ማረፊያቸው ማቃናታቸው ተገልጾል፡ ይህ በዚህ እንዳለ አሁን ዘግይቶ በደረሰን ዜና መስረት አቶ በረከት ስሞኦን ዛሬ ማምሻውን ለአስቸኳይ ጉዳይ ህክምናቸውን አቋርጠው ወደ ኢትዮጵያ እንደሚመለሱ ምስጢራዊ መረጃዎቻችን አክለው አረጋግጠዋል ።
-- Ze-Habesha Website

የወላይታ ዞን የአንድነት አመራሮች በመንግስት ሀይሎች ከባድ ድብደባ ተፈፀመባቸው


  • 62
     
    Share
(ፍኖተ ነፃነት ጋዜጣ) የወላይታ ዞን የአንድነት ፓርቲ ሰብሳቢ አቶ ማሞ ገሞ እና የዞኑ ድርጅት ጉዳይ ኃላፊ አቶ ወኖ በዳሳ ትላንት ጥቅምት 22 ቀን 2007 ዓ.ም ከቀኑ በ 8 ሰዓት ከስብሰባ ወጥተው በወላይታ ሶዶ ከተማ በአንድ ሆቴል ውስጥ እያሉ በከተማው የፖሊስ አዛዥ መመሪያ በመንግስት ሀይሎች “እኛ ሀገር እመራን እናንተ ትቃወሙናላችሁ እናንተን እናጠፋቹሀለን” በማለት ከባድ ድብደባ እንደተፈፀመባቸው የፓርቲው የድርጅት ጉዳይ ለፍኖተ ነፃነት አስታወቀ፡፡ አመራሮቹ በድብደባው ከባድ ጉዳት እንደደረሰባቸውም ታውቋል፡፡
UDJ
በድብደባው ከባድ ጉዳት የደረሰባቸው አቶ ወኖ በዳሳ ራሳቸውን ስተው በአምቡላንስ ወደ ሆስፒታል ቢወሰዱም እስካሁን እንዳላገገሙ እና የዞኑ የአንድነት ሰብሳቢ አቶ ማሞ ገሞ ህክምና አግኝተው ከወጡ በኋላም በከተማው ደህንነቶች ክትትልና ወከባ እየደረሰባቸው እንደሚገኝም ታውቋል፡፡
የወላይታ ዞን የአንድነት አመራሮች ላይ ድብደባ እንዲደርስ መመሪያ የሰጡት የከተማው የፖሊስ አዛዥ በአቶ ወኖ ላይ በደረሰው ከባድ ጉዳት ተደናግጠው በአምቡላንስ እንዲወሰዱ ካደረጉ በኋላ የዞኑ የአንድነት ሰብሳቢ አቶ ማሞ ገሞ “በአንድም ሚዲያ ስለሁኔታው እንዳይናገሩ” በሚል ክትትል እያስደረጉባቸው ያገኛል፡፡
-- Ze-Habesha Website

eight Ethiopian Air Force pilots have defected

A total of eight Ethiopian Air Force pilots have defected this month, according to a senior Eritrean official.
Ethiopian MiG-23
Ethiopian MiG-23

The official didn’t specify if the pilots defected to Eritrea, or if they managed to flee the country with their aircrafts, though it is highly likely they did in both cases.
The defections come as reports indicate the Ethiopian Air Force is in shambles, and that the TPLF oligarchs are “disgusted” by their poor performances.
Ethiopia is no stranger to high-profile air force defections. Last year, four Ethiopian helicopter pilots and a MiG-23 pilot defected to Eritrea.
The names of the helicopter pilots are Cap. Aklilu Mezene, Cap. Tilahun Tufa, Cap. Getu Worku and Cap. Biniam Gizaw, while the name of the MiG-23 pilot is Daniel Yeshewas.
Source: madote.com
-- -- ---
Ze-Habesha Website 

wanted officials