Which one you first choose? በቅድሚያ የሚፈልጉት

Showing posts with label ESAT. Show all posts
Showing posts with label ESAT. Show all posts

Thursday, May 5, 2016

በሼህ መሃመድ አላሙዲን የገንዘብ ድጋፍ የሚንቀሳቀሰው AESA One በኢሳት ጋዜጠኛ ተወልደ በየነ ላይ የከፈተው ክስ ውድቅ ሆነ

ኢሳት (ሚያዚያ 27 ፥ 2016) 

በሼህ መሃመድ አላሙዲን የገንዘብ ድጋፍ በሰሜን አሜሪካ የሚንቀሳቀሰው AESA One (ኤሳ ዋን) የተባለው ተቋም በኢሳት ጋዜጠኛ ላይ የከፈተው ክስ ውድቅ ሆነ። በኢሳት የመዝናኛ ክፍል ጋዜጠኛ በሆነው በጋዜጠኛ ተወልደ በየነ ላይ በአሜሪካ ቨርጂኒያ ግዛት የተመሰረተው ክስ ውድቅ የተደረገው፣ ራሱ ከሳሽ አካል ማስረጃ ማቅረብ ባለመቻሉና ክሱን በማቋረጡ መሆኑንም መረዳት ተችሏል። ይህ አመታዊ የስፖርት ውድድሮችን ለማካሄድ ባለፉት 4 አመታት በአንዳንድ የአሜሪካ ግዛቶች ሲንቀሳቀስ የቆየው ይህ ቡድን፣ ኪነጥበባዊ ዝግጅቶችንም ለማካሄድ በየአመቱ ከሃገር ቤት የሙዚቃ ባለሙያዎችን ሲጋብዝ ቆይቷል። በዚህ የሙዚቃ ዝግጅት ላይ የኪነጥበብ ባለሙያዎች እንዳይገኙ በማስፈራራት በተቋሙ ላይ ኪሳራ አድርሷል በሚል በጋዜጠኛ ተወልደ በየነ ላይ የተመሰረተው ክስ ውድቅ መሆኑ የታወቀው በዛሬው ዕለት በዋለው ችሎት መሆኑን መረዳት ተችሏል። ይህ በቢሊዮነሩ ትውልደ ኢትዮጵያዊ ሼህ መሃመድ አላሙዲን የገንዘብ ድጋፍ የሚንቀሳቀሰው ተቋም፣ ከ30 ዓመታት በላይ በሰሜን አሜሪካ የሚንቀሳቀሰውን የስፖርት ፌዴሬሽን ለመሰንጠቅ ሞክሮ፣ በፍ/ቤት ስሙን እንዳይጠቀም ዕገዳ ከተጣለበት በኋላ ኤሳ ዋን በሚል አዲስ ስያሜ አራት አመታት አስቆጥሯል። ከሩብ ክፍለ ዘመን በላይ ያስቆጠረውን የኢትዮጵያ የስፖርት ፌዴሬሽን በሰሜን አሜሪካ ለሁለት ለመክፈል የተደረገው ሙኬራ መክሸፉን ተከትሎ ተቋሙ በኤሳ ዋን የጀመረው አመታዊ ውድድር የኢትዮጵያውያንን ትኩረት ባለመሳቡ፣ ይልቁንም ዋናውን የስፖርት ፌዴሬሽን ለማዳከም የተደረገ እንቅስቃሴ ነው በሚል ስነ-ስርዓቱ በተመልካች ድርቅ ሲመታ መቆየቱን መረዳት ተችሏል፥ ተቃውሞዎችም ሲቀርብበት ቆይቷል። የኬነጥበብ ባለሙያዎቹ በዝግጅቱ እንዳይሳተፉ የሚያግባባውም እንዲሁም የሚያስፈራራው ጋዜጠኛ ተወልደ በየነ ነው በሚል ክሱ መመስረቱንም መረዳት ተችሏል። ሆኖም ረቡዕ ዕለት ይኸው ክስ ውድቅ መደረጉም ተረጋግጧል። የቀድሞ የኮሚኒኬሽን ጉዳዮች ሚኒስተኢር አቶ ሬድዋን ሁሴን በአሜሪካ የገጠማቸው ተቃውሞ በማስመልከት በአክቲቪስት መኮንን ጌታቸው ላይ የመሰረቱት ክስ በተመሳሳይ ውድቅ መደረጉ ይታወሳል። በሰሜን አሜሪካ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያንን በዋናነት ያቀፈውና ከተለያዩ የአለም ክፍሎች የመጡ ኢትዮጵያውያን የሚታደሙበት ዓመታዊ የኢትዮጵያ የስፖርት ፌዴሬሽን በሰሜን አሜሪካ ዝግጅት በመጪው ሰኔ ወር መጨረሻ በካናዳ ቶሮንቶ እንደሚካሄድም ለማወቅ ተችሏል። ኢትዮጵያውያን በቋንቋና በፖለቲካ አመለካከት ሳይለያዩ የሚታደሙበት ይህ ዝግጅት መከበር ከጀመረ ከ30 ዓመታት በላይ አስቆጥሯል። እኤአ ከፊታችን ጁላይ 3 እስከ 9 በካናዳ ቶሮንቶ ለ33ኛ ጊዜ ይከበራል።

Wednesday, January 13, 2016

በጥይት የተመታው ሙሽራ በሞት አፋፍ ላይ ነው። የሚረዳው ሆስፒታል አጥቷል




በሠርጉ ዕለት ዋዜማ ጭንቅላቱን በጥይት የተመታው መምህር ፍጹም አባተ በመቱ ሆስፒታል ቆይቶ ለቀዶ ጥገና ሕክምና ወደ ጥቁር አንበሳ ሆስፒታል ተልኮ የሚረዳው አጥቷል። ጥቁር አንበሳ በበኩሉ ምንም እርዳታ ሳያደርግ ወደ አለርት ሆስፒታል ቢልከውም አልርት ሆስፒታል በተመሳሳይ መልሶ ወደ ጥቁር አንበሳ ልኮታል። ተገቢ ሕክምና የተነፈገው ፍጹም ደሙ በየዕለቱ እየቀነሰ ከመምጣቱ የተነሳ በሞት አፋፍ ላይ ነው።
ኢሳት
"በሬው ታርዶ፣ ምግብ ተዘጋጅቶ፣ ዘመድ ጎረቤቱ እየጨፈረ ነበር። ሌሊት 7 ሰዓት አካባቢ ከርሱ ጋር በስልክ አውርተን፣ 'አሁን ስለደከመኝ ልተኛ ነው' ብሎኝ ተሰነባበትን ከዚያ..."
በመንግስት ወታደሮች በሠርጉ ዋዜማ በጥይት የተመታው መምህር ፍጹም አባተ እጮኛ ወይዘሪት ፍሬሕይወት በለጠ ናት። ስለአሰቃቂው ሁኔታ ትናገራለች። አባቱም አሉ።
ኋላ ላይ ይጠብቁን
ኢሳት የሕዝብ ድምጽ!.

Tuesday, November 24, 2015

በባህርዳር የተደረገውን የባጃጆች አድማ ተከትሎ ሹፈሮች እየታሰሩና የገንዘብ ቅጣት እንዲከፍሉ እየተደረገ ነው

 

bajaj
ጥቅምት ፳፫ (ሃያ ሦስት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ዘጋቢያችን ነዋሪዎችን በማነጋገር እንደገለጸው፣ በአድማው የተሳተፉትን ሹፌሮችን ወደ እስር ቤት የወሰዱ ሲሆን፣ ከፖሊስ የሚደርስባቸውን ጫና በመፍራት ስራ እንጀምራለን ያሉት ደግሞ 500 ብር ቅጣት ካልከፈሉ እንደማይጀምሩ ተነግሯቸዋል። ከፖሊስ የሚደርሰውን ወከባ በመፍራት ብዙ ሹፈሮች አሁንም ራሳቸውን ደብቀዋል።
አንድ የባጃጅ ባለሃብት መንግስት ለምን አድማ አደረጋችሁ በሚል እየተበቀለ ነው ብለዋል።
bajaj

wanted officials