Which one you first choose? በቅድሚያ የሚፈልጉት

Sunday, September 22, 2019

ከ34 ዓመት በፊት በአውሮፕላን ጠለፋ የተጠረጠረው በቁጥጥር ስር ዋለ

https://zethiopians.blogspot.com/2019/09/blog-post_68.htm

የተጠለፈው አውሮፕላን

Image copyrightALAIN NOGUES/GETTY
እ.አ.አ. 1985 በአሜሪካ አየር መንገድ ንብረት በሆነ አውሮፕላን ላይ በተፈጸመው ጠለፋ እጁ አለበት የተባለው የ65 ዓመት ሊባኖሳዊ ግሪክ ውስጥ በቁጥጥር ስር መዋሉን ፖሊስ አስታወቀ።
ስሙ ያልተጠቀሰው ተጠርጣሪ ባሳለፍነው ሐሙስ ነበር ሚይኮኖስ በተባለ ደሴት በቁጥጥር ሥር የዋለው። ተጠርጣሪው በጉዞ ላይ በነበረበት ወቅት ፓስፖርቱ ሲታይ ጀርመን ውስጥ ተፈላጊ እንደሆነ ተደርሶበታል።

'ቲደብልዩኤ' የበረራ ቁጥር 487 የነበረው አውሮፕላን መሳሪያ ታጥቀው በነበሩ ሂዝቦላህ የተባለው ኢስላማዊ ቡድን አባላት በቁጥጥር ስር ሆኖ ነበር። ምንም እንኳን ሂዝቦላህ ድርጊቱን አለመፈጸሙን ቢክድም።
ተጠርጣሪው እ.አ.አ. በ1987 ፈጽሞታል በተባለው የጠለፋና ሰዎችን በማገት ወንጀል ነበር በጀርመን ባለስልጣናት ይፈለግ የነበረው። በአሁኑ ሰዓት ተጠርጣሪው ከፍተኛ ጥበቃ በሚደረግለት የግሪክ ማረሚያ ቤት ውስጥ ይገኛል።
ወንጀሉን ፈጽሟል ከተባለ ከሁለት ዓመታት በኋላ ጀርምን ውስጥ በቁጥጥር ስር ውሎ የነበረ ሲሆን ቤሩት ውስጥ ታግተው የነበሩ ሁለት ጀርመናውያንን ለማስቀቅ ወደ ሊባኖስ በነጻ ተለቆ ነበር።
እ.አ.አ. በ1985 የትራንስ ወርልድ አየር መንገድ ንብረት የሆነው አውሮፕላን ከካይሮ ተነስቶ በአቴንስ፣ ሮም፣ ቦስተን እና ሎስ አንጀለስ አድርጎ ወደ ሳንዲዬጎ በመብረር ላይ ሳለ ነበር ከአቴንስ ሲነሳ ጠላፊዎቹ አስገድደው ቤሩት እንዲያርፍ ያደረጉት።
153 የአውሮፕላኑ ተሳፋሪዎችና ሰራተኞች ለ17 ቀናት በቆየው አጋች ታጋች ድራማ በአውሮፕላኑ ውስጥ ቆይተዋል። ጠላፊዎቹም በእስራኤል ተይዘው የሚገኙ በመቶዎች የሚቆጠሩ የሊባኖች ዜጎች ይፈቱልን በማለት ታጋቾቹን በማሰርና በመደብደብ በኋላ እንደሚገድሏቸው ሲያስፈራሩ ነበር።
በእስራኤል የሚገኙት ታሳሪዎች ሳይለቀቁ ሲቀር በአውሮፕላኑ ውስጥ ተሳፋሪ የነበረ አንድ የ23 ዓመት አሜሪካዊ የውሃ ጠላቂ ወታደር ተተኩሶበት የተገደለ ሲሆን ሬሳውም ወደ ውጪ ተወርውሮ ነበር።
በመጨረሻ ግን ጠላፊዎቹ ታጋቾቹን ለቀዋል።
እንደ ኤፍቢአይ ከሆነ አውሮፕላኑን በመጥለፍ ወንጀል ውስጥ ቢያንስ አራት ሰዎች ቀጥተኛ ተሳትፎ ነበራቸው።
እአአ 1986 ላይ የተለቀቀው እና 'ዘ ዴልታ ፎርስ' (The Delta Force) የሚል ስያሜ የተሰጠው ፊልም ይህን የአውሮፕላን ጠለፋ ላይ መሰረት ተድርጎ የተሰራ ነው።

No comments:

Post a Comment

wanted officials