Which one you first choose? በቅድሚያ የሚፈልጉት

Monday, September 23, 2019

ውሃ ውስጥ ለፍቅረኛው የአግቢኝ ጥያቄ ያቀረበው ግለሰብ ሰጥሞ ሞተ



ስቲቨን ዌበርImage copyrightKENESHA ANTOINE
አንድ አሜሪካዊ ጎብኚ ታንዛኒያ ውስጥ ለፍቅር ጓደኛው የጋብቻ ጥያቄ ለማቅረብ ወደ ውሃ ውስጥ ገብቶ ሳይመለስ መቅረቱ ተሰምቷል።
ስቲቨን ዌበር የተባለው ግለሰብ እና ፍቅረኛው ኬኔሻ አንቱዋን በታንዛኒያ ፔምባ ደሴት ላይ በሚገኝ ማንታ በተባለ ሪዞርት ነበር ያረፉት። ስቲቨን ለፍቀረኛው ታገቢኛለሽ ወይ የሚለውን መልዕክቱን በወረቀት ላይ ጽፎ ነበር ወደ ውሃ ውስጥ የገባው።
ፍቅረኛው ኬኔሻ አንቱዋን በፌስቡክ ገጿ ላይ ባስተላለፈችው ምልዕክት ጥልቅ ወደሆነው ባህር አካባቢ የሄደው ስቲቨን መመለስ ሳይችል መቅረቱን አረጋግጣለች።
የማንታ ሪዞርት አስተዳደር ለቢቢሲ እንደገለጸው ስቲቨን ዌበር ውሃ ጠለቃ በሚደረግበት አካባቢ ገብቶ ህይወቱ ያለፈችው ባሳለፍነው ሐሙስ ከሰዓት ላይ ነበር።
''ባሳለፍነው ሐሙስ በሪዞርታችን በተፈጠረው ክስተት እጅግ ማዘናችንን መግለጽ እንፈልጋለን'' ብሏል ድርጅቱ በመግለጫ።
የሪዞርቱ ዋና ስራ አስኪያጅ የሆኑት ማቲው ሳውስ እንዳሉት መላው የማንታ ሪዞርት ሰራተኛ በተፈጠረው አደጋ ተደናግጠዋል።
አጭር የምስል መግለጫስቲቨን ዌበር እና ፍቅረኛው ኬኔሻ አንቱዋን
ስቲቨን ዌበር እና ፍቅረኛው ኬኔሻ አንቱዋን በሪዞርቱ የውሃ ጠለቃ በሚደረግበት የባህሩ ክፍል ለአራት ቀናት ለመቆየት ቀድመው ቦታ አስይዘው የነበረ ሲሆን ቦታው ከባህር ዳርቻ በግምት በ250 ሜትር ርቀት ላይ ይገኛል።

ለቀናት በአካባቢው ሲዝናኑ የቆዩት ጥንዶች በሶስተኛው ቀን ተያይዘው ጥልቀት ወዳለው የባህሩ ክፍል ያመራሉ። ስቲቨን ፍቅረኛው ሳታየው የታገቢኛለሽ ጥያቄውን ለማቅረብ ተዘጋጅቶ ነበር።
የውሃ ውስጥ መነጽሩን እንዳደረገም ስቲቨን ለፍቅረኛ የጋብቻ ጥያቄውን ማቅረብ ጀመረ።
በላስቲክ በተሸፈነ ወረቀትም እንዲህ ሲል ጽፎ ነበር፤ ''የምወድልሽን ነገሮች ሁሉ እንዳልነግርሽ ለረጅም ጊዜ ትንፋሼን መያዝ አልችልም፤ ነገር ግን ስላቺ የምወዳቸውን ነገሮች በሙሉ በእያንዳንዱ ቀን ይበልጥ እወድልሻለው።''
ቀጥሎም የጋብቻ ቀለበቱን ለፍቅረኛው አቅርቦ ነበር።
ስለ አሟሟቱ ዝርዝር መረጃ ባይሰጥም፤ ኬኔሻ አንቱዋን እንደገለጸችው ''ለጥያቄው ምላሼን እንኳን ሳይሰማ ህይወቱ በማለፉ በጣሙን አዝኛለሁ'' ብላለች።

No comments:

Post a Comment

wanted officials