Which one you first choose? በቅድሚያ የሚፈልጉት

Sunday, September 22, 2019

የኦርቶዶክስ ተዋህዶ እምነት ተከታዮች በተለያዩ ከተሞች ሰልፍ እያካሄዱ ነው



በደብረ ማርቆስ ከተማ እየተካሄደ የሚገኘው የተቃውሞ ሰልፍImage copyrightAMMA
አጭር የምስል መግለጫበደብረ ማርቆስ ከተማ እየተካሄደ የሚገኘው የተቃውሞ ሰልፍ
የኦርቶዶክስ ተዋህዶ እምነት ተከታዮች በተለያዩ የአማራ ክልል ከተሞች ሰልፍ እያካሄዱ ነው።
የተቃውሞ ሰልፍ እየተካሄደ ከሚገኝባቸው ስፍራዎች መካከል፤ የአማራ ክልል መዲና በሆነችው ባህርዳር፣ የሰሜን ወሎ ዞን ዋና ከተማ ወልዲያ እና ምሥራቅ ጎጃም ደብረ ማርቆስ ይጠቀሳሉ።

የሰልፉ ተሳታፊዎች በቤተክርስቲያኗ፣ በኃይማኖት አባቶች እና በምዕመኖቿ ላይ እየደረሰ ያለው ጥቃት ይቁም የሚል መልዕክት ይዘው ወጥተዋል።
በሰላማዊ ሰልፉ ላይ እየተሰሙ ካሉ ድምጾች መካከል፤ ''በቤተ-ክርስቲያኗ እና በምዕመኖቿ ላይ የሚፈጸሙት ጥቃቶች ይቁሙ፣ ጥፋተኞች ለሕግ ይቅረቡ'' የሚሉ ይገኙበታል።
በወልዲያ ከተማ እየተካሄደ የሚገኘው የተቃውሞ ሰልፍImage copyrightAMMA
አጭር የምስል መግለጫበወልዲያ ከተማ እየተካሄደ የሚገኘው የተቃውሞ ሰልፍ
በደብረ ማርቆስ ከተማ እየተካሄደ ያለውን ሰልፍ ከሚያስተባበሩት መካከል አንዱ የሆኑት አቶ በሪሁ ተስፋዬ "እጅግ በርካታ ሰዎች እየተሳተፉ የሚገኙበት ሰልፍ ሰላማዊ በሆነ መልኩ እየተከናወነ ነው" ብለዋል።
በሰላማዊ ሰልፉ ላይ እየተሰሙ ካሉ መፈክሮች መካከል ''የቅዱስ ሲኖዶስ ድምጽ ይሰማ'' እና ''የቤተክርሰቲያን እና የኦሮቶዶክሶዊያን መገደል ይቁም'' የሚሉት ጎልተው እንደሚሰሙ አቶ በሪሁ ተናግረዋል።

የዛሬ ሳምንት ዕሁድ በተመሳሳይ መልኩ በተለያዩ የአማራ ክልል ከተሞች የተቃውሞ ሰልፎች ተካሂደው ነበር።
በደሴ፣ ደብረ ታቦር እና ጎንደር ከተማ በተካሄዱት እና በሰላም በተጠናቀቁት ሰላማዊ ሰልፎችም ''በተለያዩ የሃገሪቱ ክፍሎች ቤተ-ክርስቲያን ያቀጠሉ እና ምዕመናንን የገደሉ ለፍርድ ይቅረቡ፣ መንግሥት ቤተ-ክርስቲያንን ሊያከብር ይገባል'' የሚሉ ተመሳሳይ የተቃውሞ ድምጾች ነበር የተሰሙት።

No comments:

Post a Comment

wanted officials