Which one you first choose? በቅድሚያ የሚፈልጉት

Thursday, March 5, 2020

ወሲብ በፊንጢጣ በኩል (anal sex) በመፈፀም የሚከሰት የመቀመጫ ካንሰር አሳሳቢ እየሆነ ነው

ያልተለመደ ወሲብ በተለይም በፊንጢጣ በኩል (anal sex) በመፈፀምና ከአንድ በላይ ወሲብ አጋር በመያዝ በሴቶች ላይ ከሚከሰቱ ካንሰሮች ውስጥ የሚፈረጀው የፊንጢጣ ካንሰር ነው፡፡ እንዶኒውስዊክ መፅሔት ሰፊ ዘገባ ከሆነ ይህን ካንሰር ለየት የሚያደርገው ችግሩ ከአንዳንድ ሴቶች ቅጥ ያጣ የወሲብ ባህሪ ጋር የሚያያዝ መሆኑና በዚህም ማህበረሰባዊነት በሌለው ባህሪ ሳቢያ የሚከሰተውን ካንሰር ለሌሎች ለመናገር አሳፋሪ (taboo) መሆኑ ነው፡፡
ለሰዎች በተለይም ለሐኪም የማይነግርበት አንዱ ምክንያት ሰዎች ችግሩን ከተለያዩ አሉታዊ ነገሮች ጋር ስለሚያያይዙትና መያዛቸው ስለሚያሳፍራቸው ይዘውት ይቆያሉ፡፡ ችግሩም ይባባሳል፤ ሌላውም ሰው ያስተላልፉታል ይላል መፅሔቱ፡፡
ብዙ ሰዎች የፊንጢጣ ካንሰር እንዳለባቸው ይነገራል፤ ነገር ግን ለሕይወታቸው የሚጠቅም ህክምና ለማድረግ በጣም ይቸገራሉ፡፡ ብዙ ጊዜ የቅርብ ቤተሰቦቻቸው እንዲሁም የሚቀርቧቸው ጓደኞቻቸው ያለባቸውን ችግር ቢያውቁትም በሽታው ያለባቸው ሰዎች ለቤተሰቦቻቸውም ሆነ ለሐኪም ይህን በሽታ አውጥተው መናገር አይፈልጉም፡፡
በሽታው ያለባቸው ሰዎች ‹‹በግልፅ የቂጥ (የፊንጢጣ) ካንሰር አለብኝ›› ብሎ መናገር በጣም ያሳፍራቸዋል፡፡ ብዙ ጊዜም ስሙን ሸፋፍነውት ማለፍን ይመርጣሉ፡፡ በሽታው መኖሩና አለመኖሩ የሚታወቀው በተደጋጋሚ በሚደረግ የኮሎኖስኮፒ ምርመራ ሲሆን በዚህ ምርመራ የመቀመጫ ካንሰር ለበት ሰው በቀጣይ በሚደረግለተ ምርመራ ካንሰሩ በደም ስር ውስጥ ተዛምቶ ይሁን አይሁን ለማረጋገጥ ተጨማሪ ምርመራዎችን ሊያደርግ ይችላል፡፡
ህክምናው በአሜሪካ ሀገር ውስጥ በዓመት ለ8,000 ሰዎች ይደረጋል፡፡ የመቀመጫ ካንሰር ብዙ ያልተለመደ በሽታ ቢሆንም ግን የበሽታው ቁጥር ላለፉት ሦስት ዓመታት በሶስት እጥፍ ጨምሯል፡፡ በየዓመቱ በዚህ በሽታ የተጠቁ ሰዎች ቁጥር በ2 በመቶ እየጨመረ ይገኛል፡፡ የቂጥ ካንሰር /anal cancer/ ህክምናውን ለመጀመር ብዙ ሰዎች ለውሳኔ ይቸገራሉ፤ ምክንያቱም ይህ ካንሰር የሚያጠቃውን የሰውነት ክፍል ለመግለፅ ስለሚያፍሩ ብዙ ሰዎች ዝምታን ይመርጣሉ፡፡
ይህ በሽታ ብዙ ጊዜ የሚከሰተው ከአንድ በላይ የሆነ የወሲብ ጓደኛ በመኖር ወይም ከተሌዩ ሰዎች ጋር ወሲብ በመፈፀም ነው፡፡ እንዲሁም ባልተለመደ መንገድ ወሲብ መፈፀም ማለትም በፊንጢጣ በኩል የሚደረግ ወሲብ ለዚህ በሽታ መንስኤ ተደርገው ከሚጠቀሱት ምክንያቶች ውስጥ ግንባር ቀደሙ ነው፡፡
ከዚህ በላይ ይህን በሽታ እንዲባባስ የሚያደርገው ሰዎች በበሽታው ከተያዙ በኋላ የሚደርስባቸው ትልቅ የስነ ልቦና ጉዳት ነው፡፡ ‹‹ሰው ምን ይለኛል›› በሚል እሳቤ በሽታው ወደ መጨረሻ ደረጃ እንዲደርስ ከማድረጉም በላይ በቀላሉ ወደሌሎች ሰዎች ሊተላለፍ ይችላል፡፡
ዶ/ር ካርይ ኢንግ የካንሰር ህክምና ባለሙያ ሲሆኑ በአሜሪካን ሀገር በቴክሳስ ዩኒቨርሲቲ በሜድ አንደርሰን ሴንተር ውስጥ የካንሰር በሽታ ህክምና ለመስጠት እስፔሻላይዝ ያደረጉ ሲሆን እሳቸው እንደሚሉት ከሆነ በዚህ በሽታ ላይ ትልቅ መገለል እንዲሁም ከሌሎች በሽታዎች ተለይቶ የሚታይበት መንገድ አለ ይላሉ፡፡ ምክንያቱም ሰዎች ለዚህ የካንሰር በሽታ የሚሰጡት ግምት እና ትኩረት እንደሌሎቹ የካንሰር በሽታዎች ሳይሆን ከዛ በላይ የሚጓዝ መሆኑን ይገልፃሉ፡፡ ይህ የሆነው ደግሞ በበሽታው የተያዙ ሰዎች ችግሩን አውጥተው ለመግለፅ ድፍረት ስለሌላቸውና ማህበረሰቡ የሚቀበላቸው ስለማይመስላቸው ነው፡፡
እንደሳቸው ገለፃ ሌሎች የካንሰር በሽታዎችን ማህበረሰቡ ለመግለፅና ለመናገር ምንም አይቸገርም፡፡ ለምሳሌ የጡት ካንሰርን ሴቶች ያለፍርሃትና ያለማፈር ጮክ ብለው ጣራን በሚሰነጥቅ ድምፅ ሊናገሩት ይችላሉ፡፡ ምክንያቱም በማህበረሰቡ ውስጥ ተቀባይነት ስላገኘ በበሽታው የተያዙ ሴቶች ስለበሽታው ያለፍርሃት ከሰዎች ጋር ያወራሉ፡፡
በ1914 (እ.ኤ.አ) ለመጀመሪያ ጊዜ ቤቲ ፎርድ የተላለፈ የጡት ካንሰር እንዳለባትና በዚህ በሽታ የተነሳ ጡቶቿ እንደተቆረጡ ተናገረች፡፡ ከዚህ ጊዜ ጀምሮ ሰዎች በነጻነት ስለጡት ካንሰር መናገር ችለዋል፡፡ ይቺ ቤቲ ፎርድ የተባለችው የመጀመሪያዋ የጡት ካንሰር አብዮተኛ ተደርጋ ተወስዳለች፡፡ ይቺ ሴት ደፍራ ስለበሽታው በሚዲያ በመናገሯ በሌሎች የካንሰር ህሙማን ያለባቸውን በሽታ በግልፅ ያለፍርሃት እንዲናገሩ በር ከፍታለች፡፡
ይህ የቂጥ ካንሰር በሽታ ብዙ ጊዜ ሴቶችን የሚያጠቃ ቢሆንም በተሌ ሆሞሴክሽዋል ወንዶችም በበሽታው ይጠቃሉ፡፡ ብዙ ጊዜ በፊንጢጣ በኩል ደም ሊፈስና ቁስል ሊታይ ይችላል፡፡ በርካታ በዚህ በሽታ የተጠቁ ሴቶች እንደሚሉት ከሆነ ‹‹በጡት ካንሰር ብንያዝ ኖሮ በማህበረሰቡ ዘንድ ተቀባይነት እናገኝ ነበር፡፡ ነገር ግን በቂጥ ካንሰር ለተጠቁ ሰዎች ማህበረሰቡ ያለው ምላሽ ወይም አስተያየት ጤናማ ያልሆነ ወይም አስነዋሪ ህይወት እንዳለን ነው የሚቆጥረው›› ይላሉ፡፡ በዚህ የተነሳ በማህበረሰቡ ከሚሰጠው ዝቅተኛና ትንሽ ግምት ተነሳ ስለጉዳዩ ለመግለፅ ያፍራሉ፡፡
ለዚህ በሽታ መንስኤ 90 በመቶ የሚሆነው የሚከሰተው በወሲብ በሚተላለፈው ፓፒሎማ ቫይረስ (papilloma virus) ወይም በአጭሩ HPV በሚባል ሲሆን ይህ ቫይረስ በተመሳሳይ ለማህጸን በር ካንሰር እንዲሁም በወንዶችና በሴቶች ብልት ላይ ለሚፈጠሩ በሽታዎች መንስኤ ነው፡፡ ይህ HPV ቫይረስ ከሰው ወደ ሰው በቆዳ ንክኪ የሚተላለፍም ነው፡፡ በተለይ ያለ መከላከያ በአፍና በፊንጢጣ በኩል የሚደረግ የግብረሥጋ ግንኙነት ሊከሰት ሁሉ ይችላል፡፡
በአሁኑ ወቅት 79 ሚሊዮን የሚሆኑ ሰዎች በዚህ ቫይረስ ይጠቃሉ፡፡ ይህ ማለት ደግሞ ሰዎች በህይወታቸው ውስጥ በሚፈጠር አንዱ አጋጣሚ በዚህ ቫይረስ የመጠቃት ዕድላቸው ከፍተኛ ነው፡፡ ከ79 ሚሊዮን ከሚሆኑ በዚህ ቫይረስ ከተጠቁ ሰዎች ውስጥ በአሁኑ ሰዓት 27 ሺ የሚሆኑት በየዓመቱ የካንሰር ምርመራ ይደረግላቸዋል፡፡ ከእነዚህ ውስጥ 5 ሺ የሚሆኑት ደግሞ በፊንጢጣ ካንሰር ተይዘው ህክምና የሚረግላቸው ናቸው፡፡
በካሊፎርኒያ ዩኒቨርሲቲ በፊንጢጣ ካንሰር ህክምና መስራችና ተቆታጣሪ የሆኑት ዶ/ር ጆኤልፕላቪስኖ እንደሚሉት ከሆነ የ HPV ቫይረስ በሚሰጠው ክትባት በመቀነስ ላይ ይገኛል፡፡ እናም ክትባቱን መውሰድ ትልቅ መፍትሄ መሆኑን ይናገራሉ፡፡
ክትባቱ በተጀመረባቸው 10 ዓመታት ውስጥ የዚህ ቫይረስ ስርጭት መከላከል ተችሏል፡፡ ምክንያቱም ክትባቱ ለሴቶችም ሆነ ለወንዶች ህፃናትን በ11 እና 12 ዓመታቸው (ለግብረ ሥገ ግንኙነት ዕድሜ ከመድረሳቸው በፊት) ስለሚሰጣቸው ወደፊት ከሚገጥማቸው በቫይረሱ ከሚመጣ የካንሰር በሽታ መታደግ ተችሏል፡፡ ነገር ግን ብዙ ጊዜ ወላጆች ክትባቱን ለልጆቻቸው ለማስወገድ ፍቃደኛ አይደሉም፡፡
የዚህ ምክንያቱ አንዱም ስለዚህ በሽታ በቂ እውቀት ስለሌላቸው ነው፡፡ ሌላው የህፃናት ዶክተሮች ለወላጆች ልጆቻቸውን እንዲያስከትቡ ሙያዊ ምክር ስለማይሰጧቸው ነው፡፡ በዚህም የተነሳ እስካሁን በአሜሪካን ሀገር 40 በመቶ ሴት ህፃናትና 20 በመቶ ወንድ ህፃናት ብቻ ናቸው የቅድመ ክትባት አገልግሎቱን ያገኙት፡፡
ይህ ሁኔታ ደግሞ ችግሩ እንዲባባስ ያደርገዋል፡፡ ከዚህም በላይ በበሽታው የተያዙ ሰዎች በራሳቸው ላይ በሚያጋጥማቸው የስነ ልቦና ጉዳት የተነሳ ህክምናውን ለማድረግም ሆነ በሽታው ምን አይነት ደረጃ ላይ እንደደረሰ ለማወቅ ይቸገራሉ፡፡ በዚህ የተነሳ የማይነገር በሽታ አድርገው ውስጣቸውን ያሳምኑታል፡፡ ውስጣቸውን በማሳመናቸው የተነሳ ስለራሳቸው የበታችነት ስሜት እና ተስፋ መቁረጥ እንዲሁም ለራሳቸውና ለሌሎች ሰዎች ግድ ማጣት ይገጥማቸዋል፡፡ በዚህ የተነሳ በሽታውን ወደሌሎች ሰዎች በቀላሉ ሊያስተላልፉት ይችላሉ፡፡
ይህ የማይነገር የተባለውን በሽታ በመናገር እና ቅድመ ክትባት በማድረግ እራስንና ወገንን ከሞት እና ከስቃይ መታደግ ይቻላል፡፡ ለዚህም ከግለሰብ ጀምሮ እስከ ማህበረሰብ ድረስ ጠንካራ ስነ ልቦናዊ ጥንካሬ ያስፈልጋል፡፡ የህክምና ባለሙያዎችም ለወላጆች ልጆቻቸውን የፀረ ፓፒሎማ ክትባት እንዲያስከትቡ ሊመክሯቸው ይገባል በማለት ኒውስ ዊክ ዘገባውን ቋጭቷል፡፡

Wednesday, March 4, 2020

ኢትዮጵያ ውስጥ የላቀ ጣዕም ያለውን የቡና ዓይነት የሚለይ ውድድር ተካሄደ




በዘንድሮው ውድድር ከ1ሺ በላይ የቡና ናሙናዎች ቀርበዋል
ከሰሞኑ ከመላው ኢትዮጵያ የተላኩ የቡና ናሙናዎች አዲስ አበባ ላይ መዓዛቸው ሲለካ፣ ጣዕማቸው ሲወዳደር ሰንብቷል።ይህ Cup of excellence የተሰኘ የላቀ ጣዕም ያላቸውን የቡና ዐይነቶች የማወዳደር መርሃ-ግብር ልዩ ጣዕም ያላቸውን ቡናዎች የማስተዋወቅ፣ የተሻለ ገበያ ዕድል እንዲያገኙ ማገዝ ዓላማው እንደሆነ አስተባባሪው ተቋም ይፋ አድርጓል።
ሀብታሙ ስዩም ውድድሩን የማስተባበር ኃላፊነት ከተሰጣት ቅድስት ሙሉጌታ ጋር ያደረገውን ምጥን ቆይታ ያዳምጡ።
*ቃለ-ምልልሱ ከተደረገ በኋላ በውድድሩ ያሸነፉ የቡና ናሙናዎች ዝርዝር ይፋ ተደርጓል።በዚህም መሰረት:-መቀመጫውን በኦሮሚያ ክልል ጉጂ ዞን፣ ቡቃ ሳይሳ ቀበሌ ያደረገው -ቡቃ ሳይሳ የቡና አምራች ድርጅት ያቀረበው የቡና ናሙና የአንደኛ ደረጃን አግኝቷል።የምዕራብ ጉጂ ስቄ ቦኮሳ ቀበሌው ታምራት ኢደና የቀረቡት የቡና ናሙና የሁለተኛ ደረጃን እንዲሁም የምዕራብ ጉጂ ሃሮዋቹ ቀበሌው ገሬ ዋሌ ያቀረቡት ቡና ሶስተኛ ደረጃን ማግኘታቸውን አወዳዳሪው አካል በማህበራዊ ገጹ ይፋ አድርጓል።
አሸናፊው ቡና በበይነ መረብ ላይ በሚደረግ የጨረታ ስነስርዓት ዓለም አቀፍ ገበያተኞች እንዲፎካከሩበት እንደሚደረግ ይጠበቃል።https://amharic.voanews.com/pp/5315087/ppt0.html

በህዳሴ ግድብ ድርድር ኢትዮጵያ ጫና እየደረሰባት ነው ያሉ ትውልደ-ኢትዮጵያዊያን ሰልፍ ወጡ

የካቲት 28, 2020


በዮናይትድ ስቴትስ ውጭ ጉዳይ መስሪያቤት ፊት ለፊት ትውልደ ኢትዮጵያዊያን ሰለማዊ ሰልፍ አድርገዋል።ሰላማዊ ሰልፍ አድራጊዎቹ ዮናይትድ ስቴትስ የህዳሴ ግደብ ድርድርን በተመለከተ ለግብጽ ያደላ አቋም ይዛለች ፣ኢትዮጵያ ላይም ጫና እያሳደረች ነው ሲሉ ወቅሰዋል።
የኢትዮጵያ መንግስት የሀገሪቱን ጥቅም አሳልፎ የሚሰጥ ድርድር እንዳይፈርም፣ የእስከአሁኑን ድርድር ይዘት በግልጽ እንዲያሳውቅም ጠይቀዋል።
ሰልፉን የተከታተለው ሀብታሙ ስዩም ቀጣዩን ዘገባ አሰናድቷል።  https://amharic.voanews.com
No media source currently available

በቻይና አዲስ የኮሮናቫይረስ ተያዦች ቁጥር ቀንሷል


አዲስ የኮሮናቫይረስ ተያዦች ቁጥር ከምንጊዜውም ይበልጥ ቀንሷል ስትል ቻይና ተናገረች። ወረርሺኙ ከሁለት ወራት በላይ በፊት ከተቀሰቀሰ ወዲህ ቻይና ውስጥ ከሁለት ሺህ የሚበልጥ ህዝብ ገድሏል።
የሃገሪቱ የብሄራዊ ጤና ኮሚሽን ባወጣው መግለጫ እንዳለው በትናንትናው ዕለት የተመዘገቡት አዲስ የኮሮናቫይረስ ተጠቂዎች ቁጥር 394 ብቻ ነበር። ለንጽጽር ማክሰኞ ዕለት 1749 ተመዝግቧል።
ተጨማሪ 114 ሰዎች በበሽታው ምክንያት በመሞታቸው እስካሁን የሞቱት ሰዎች ቁጥር 2118 ደርሷል። አጠቃላይ የተረጋገጡ የቫይረሱ ተጠቂዎች ቁጥር ደግሞ 74,576 መድረሱ ተጠቁሟል።
በዘገባዎች መሰረት ከቻይና ውጭ በቫይረሱ ሳቢያ ቢያንስ አስራ አንድ ሰዎች ለህልፈት ተዳርገዋል። አንድ በደቡብ ኮሪያ ሁለት ሰዎች በኢራን በተጨማሪም ከጃፓን ዮኮሃማ ወደብ እንዳትንቀሳቀስ የተደረገችው ዳያመንድ ፕሪንሰስ በተባለችው መዝናኛ መርከብ ላይ የነበሩ በሰማንያዎቹ ዕድሜ የነበሩ ባልና ሚስት ይገኙባቸዋል።
ቻይና መጋለጣቸው የተረጋገጠ አዲስ የኮሮና ተጠቂዎች ቁጥር ቀንሷል ብትልም የዓለም የጤና ድርጅት ሰዎች የባሰው ጊዜ አልፉል፣ ብለው ከመዘናጋት እንዲቆጠቡ አሳስቧል።

አምስት የኦነግ ከፍተኛ አመራሮችን ጨምሮ ሌሎች አባላቱ በአዲስ አበባ በቁጥጥር ስር ዋሉ


የኦነግ ሥራ አስፈጻሚ አባላትን ጨምሮ ዘጠኝ ግለሰቦች በዛሬው ዕለት (ቅዳሜ) በቁጥጥር ስር መዋላቸውን የድርጅቱ ቃል አቀባይ ለቢቢሲ ተናገሩ።
አቶ ቶሌራ አደባ፣ ለቢቢሲ እንዳረጋገጡት ዛሬ ማለዳ አመራሮቹ በጋራ ይኖሩበት የነበረው ቤት በፖሊስ የተበረበረ ሲሆን፣ አካባቢውም በፖሊስ ተከብቦ ቆይቷል።
ከዚያም በተለምዶ ሶስተኛ ወደሚባለው ፖሊስ ጣቢያ መወሰዳቸውን ይገልጻሉ።
በቁጥጥር ስር ከዋሉት ሥራ አስፈፃሚ አባላቱ መካከል አቶ አብዲ ረጋሳ እና አቶ ሚካዔል ቦረን የሚገኙ ሲሆን የድርጅቱ የማህበረሰብ ጉባዔ አባል አቶ ኬነሳ አያና፣ የኢኮኖሚ ጉዳዮች አማካሪ አቶ ያዴ አብዱልሽኩር፣ የዲፕሎማሲ አማካሪ ዶ/ር ሽጉጥ ገለታ እንዲሁም ሁለት ሹፌሮችና ሁለት ጠባቂዎችም ጨምሮ መታሰራቸውን ቃል አቀባዩ ተናግረዋል።
አቶ ቶሌራ አክለውም “ዛሬ ማለዳ የአመራሮቹ ቤት መበርበር ከጀመረበት ሰዓት አንስቶ ልናገኛቸው ስላልቻልን የታሰሩበትን ምክንያት አላወቅንም”
አቶ ቶሌራ እንደሚሉት ዛሬ ማለዳ በአባላቶቹና በአመራሮቹ መኖሪያ የተደረገው ብርበራ ያለ ፍርድ ቤት ማዘዥ የተካሄደ ነው።
እነዚህ በቁጥጥር ስር የዋሉት የኦነግ አመራሮች በጋራ ይኖሩ የነበረው አዲስ አበባ ካራ ቆሬ በሚባል አካባቢ መሆኑን የሚናገሩት አቶ ቶሌራ፣ እስካሁን በቁጥጥር ስር ያዋላቸው አካል ማን እንደሆነ እንዳላወቁ ለቢቢሲ ተናግረዋል።
ይህንን ጉዳይ ለማጣራት ወደ አዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ሕዝብ ግንኙነት ደጋግመን ብንደውልም ምላሽ ማግኘት አልቻልንም።
ከአንድ ሳምንት በፊት የኦሮሞ ነፃነት ግንባር ባወጣው መግለጫ 350 የሚሆኑ አባላቶቹ በአዲስ አበባና፣ በኦሮሚያ የተለያዩ አካባቢዎች ታፍሰው እንደታሰሩበት አስታውቆ ነበር።
BBC

አጤ ምኒሊክ የብሔር/ብሔረሰቦች ትልቅ ባለውለታ – አንድነት ይልቃል


ማስረጃችንን የዶክተር ነገሶ ጊዳዳን በወለጋ ሰዮ ኦሮሞ ጎሣ ታሪክ ላይ የተደረገ የሶስተኛ ዲግሪ ማሟያ ጥናት ዋቢ እናድርግ። ” የኦሮሞ ሕዝብ ታሪክ ” ፣ ምእራፍ ሦስት፣ ገጽ 97 – 145፣ 2008 ዓ.ም። የሚከተለው በኦሮሞ መስፋፋት ወቅት ሕልውናቸውን ያጡ ወይም ተጨፍልቀው የተዋጡ እና oromized የሆኑ ሕዝቦች ዝርዝር ነው። የደብተራ ታሪክ ነው ተብሎ ማምለጥ የማይቻልበት የኦሮሞ ብሔርተኛና የታሪክ ምሁር የምርምር ውጤት ነው። በኦሮሞ ተውፊትም ውስጥ የሚገኝ ነው። ነጋሶ እራሳቸውም ከጠፋው የዳሞት ሕዝብ ዝርያ እንደሚመዘዙ በማስረጃ አስደግፈው ተውፊት ጠቅሰው ጽፈዋል። ራስ ጎበና ዳጬም ከጋንቃ ሕዝብ ዝርያ እንደሆኑ ምስጢር ነግረውናል። ጎበና ከምኒሊክ ጋር ለሕዝብ ኅልውና ነው የታገሉት ወደሚለው መደምደሚያ ለመድረስ ትንሽ ማስረጃ ያስፈልገናል። ግን አዝማሚያው ይኸው ነው። ዝርዝሮቹ፦
1.ሙጩጮ፣
2.ገብቶ፣
3.መጮ(መጫ?)፣
3.ጉጂ፣
4.ኢናንጎ፣
5.ገራዶ፣
6.  ቦጢ፣
7. አጋዲ፣
8.ካዛ
9.ያበታ
10. ኢልመጉዛዊት
11. ዳሞታ፣
12.ወረጎ፣
13.ጋንቃ፣
14.ከንቺ. (በካንቺ ወንዝ አቅራቢያ እና በኮንቺ አካባቢ በተለምዶ “አማረ” ተብለው የሚጠሩ አሮሚፋ ተናጋሪ ጎሳዎች ይኖራሉ)፣
15.ማኦ ቡሳሴ
16. ካቾ፣
17.ጌራቾ፣
18.ሐቾ፣
19.ሒሚሮ
20.አንችፎ፣
21.ጌሬቾ
22.ኬዌጉ (ኮጎ)
23. ክዋማ (ኮሞ)
24.መዥንገር
25.ጋፋት
26.ማያ
27.ሐርላ
እነዚህ በጦርነት ተጨፍጭፈው፣ ተፈናቅለው እና ተሰድደው የተረፉ ምርኮኞች  ሙሉ በሙሉ በሜዲቻ በሞጋሣ በጉዲፈቻ በደለታ በረኮ ወደ ኦሮሞነት የተቀየሩ ናቸው። እንደ መዠንገር አይነቶች ዛሬም ተርፈው የም ተብለው አሉ። አማረ የተባሉት አማሮች ናቸው። ሲዳማ ከምባታ እና ሐዲያ በብዛት በባሌ በአርሲ በከረዩ በኢሉባቡር ወዘተ ተውጠው ኦሮሞ ሆነዋል። ከሌላ ብሔር የተለወጡት ሲዳም ጀላ ወይም በጥቅሉ ሲዳመ ተብለው እስከዛሬ ይጠራሉ።
ሶማሌዎች  በሐረርጌ በብዛት ተቀይረዋል። ብዙ ቦታዎች በጠፉ ብሔረሰቦች መጠራታቸው እነዚያን አካባቢዎች በመስፋፋቱ ወቅት የሠፈሩበት እነርሱ መሆናቸውን አመላካች ሊሆን ይችላል። ለምሳሌ ማያ በምሥራቅ ሸዋ ይኖሩ የነበሩ እውቅ ቀስተኞች ነበሩ። ከረዩ አካባቢ። ከተቀየሩ በኋላ ወደ ምሥራቅ ኢትዮጵያ ተንቀሳቅሰው ሐሮማያ የሠፈሩት እነርሱ ሳይሆኑ አይቀሩም። ማያ ጉዶ፣ ማያ ቀሎ ወዘተ የተባሉ ሥፍራዎችም ይታወቃሉ።
አንድምታ

ይህን ያህል ማስረጃ ዶ/ር ነጋሶ ከፃፉት “የኦሮሞ ሕዝብ ታሪክ” መጽሐፍ ካቀረብን እስቲ በኦሮሞ እና ትግራይ ጠባብ ልሂቃን የተጠመዱት አፄ ምኒሊክ ጨፍልቀው ያጠፉት አንድ ብሔረሰብ እና ቋንቋ በማያወላዳ ማስረጃ ይቅረብ። የለም። ዛሬ 80+ ብሔረሰብ ኅልው ሆኖ መገኘቱ የእርሳቸው ውለታ ነው።
የኦሮሞ ገዳ በአደረጃጀቱ ወደር የማይገኝለት ስለነበር ሌሎችን እየጨፈለቀ እና እየዋጠ ከመቀጠል ማንም ሀይል አይገታውም ነበር፣ ምኒሊክ ባይደርሱ ኖሮ። የኦሮሞ ጠባብ ልሂቃን ምኒሊክ በኦሮሞ ጨፍላቂ እንቅስቃሴ ላይ ደንቃራ እንደሆኑ ስለሚያውቁ ይኸው እስከዛሬ ጠምደው ይዘዋቸዋል። ይህ የዐድዋ በዓል ሲዘከር ምኒሊክ በአገር ውስጥ ጨፍላቂዎች እና በአውሮፓ ቅኝ ገዢዎች ላይ ያስመዘገቡትን ድሎች በማሰብ ሊሆን ይገባል።

TRENDING ARTICLES

አማራን የማሽመድመዱ ዕኩይ ተግባር ተጠናክሮ እንደቀጠለ ነው – አምባቸው ደጀኔ (ከወልዲያ)


ብሶት የወለደው ጀግናው የኦነግ ሠራዊት ወያኔ/ኢሕወደግ ሲጠቀምበት የነበረውን የምኒልክ ቤተ መንግሥት ለሕዝብ ጥቅም ተቆጣጥሮ ሲያበቃ በግንቦት ሰባት/ኢዜማ አማካሪነት አማራን ከምድረ ገጽ ለማጥፋት ጠንክሮ እየሠራ መሆኑን ለመገንዘብ እንደተቻለ ሰሞነኛ ፖለቲካዊ እንቅስቃሴዎች ቁልጭ ባለ ሁኔታ እያሳዩ ናቸው፡፡ ግንቦት 20/83 እንዴት አሁን ትዝ አለኝ በል?
ለብልኅ አይነግሩም ለአንበሣ አይመትሩም፡፡ በአቢይ አህመድ የሚመራው የድውያን ፖለቲከኞች አማራን እጉያው ድረስ ገብቶ ከኢትዮጵያ የማጥፋት ዕኩይ ተግባር በተለይ ካለፈው ዓመት የሰኔ 15 ጭፍጨፋ ወዲህ ያለ አንዳች ሀፍረት በገሃድ እየታዬ ነው፡፡
ለአማራ ሕዝብ ኅልውና የሚቆረቆሩ ድርጅቶችና ግለሰቦች በየትኛውም ተቋም ይታቀፉ ቅንጥ ቅንጣቸውን እየተመቱ አንድም በነፍስ አንድም በአካል ከትግል ሜዳው እንዲርቁ እየተደረጉ ነው፡፡ ንቁ ንቁ የአማራ ሕዝብ አለኝታዎች በዚህ መልክ ከሜዳው ገለል ሲሉ አማራን ከወያኔው ዘመን በከፋ በምን መልክ ሊያጠፉት እንደሚችሉ ከወዲሁ መገመት አይከብድም፡፡ ከብቶችን ለመዝረፍ በቅድሚያ እረኞችን ማጥፋት ተገቢ መሆኑ ለማንም የተሠወረ አይደለም፡፡ ስለሆነም በብአዴንም ውስጥ ቢሆን ለአማራው ደግ የሚያስቡና የሚቆረቆሩ ካሉ አማራን ለማጥፋት በቅድሚያ እነዚያን ማጥፋት ለነገ የሚያሣድሩት አይደለም፡፡ ለዚህም ተግባር ቆሞ ቀር አእሩግ ፖለቲከኞች ለአማካሪነት አሰፍስፈዋል፡፡
አማራ አለመሆናቸው ከጉዳይ የማይጣፍ ሆኖ – ለምን ቢባል ሰውን ለመውደድ ሰው መሆን ብቻውን በቂ በመሆኑ – የግንቦት ሰባት ሰዎችና ኢዜማ በሚባለው የነዚሁ ሰዎች ጥፍጥፍ ድርጅት ውስጥ ያሉ አማራ ጠል ግለሰቦች እያከናወኑት ያለው ድብቅ ሤራ ሳይጠቀስ አይታለፍም፡፡ ሁሉም ሒሣብ ማወራረዱ የማይቀር ቢሆንም አሁን ነገረ ሥራችንን ትክ ብለው ካዩት ብዙ የሚያንገበግብ ጉዳይ አለ፡፡ ሁል ጊዜም አንድ የሚጽናናኝ ነገር ደግሞ አለ – እሱም ሁሉም ነገር ባለበት አለመኖሩ፡፡
ያቺን “ፍኖተ ካርታውን ለአቢይ የሰጠነው እኛ ነን” የምትለዋን የአንዳርጋው ጽጌን ቀዳሚ ቃል ይዘን ከዚያ በፊትና በኋላ የተደረጉና እየተደረጉ ያሉ ፖለቲካዊ እንቅስቃሴዎችን ስንመለከት ሁሉም ነገር እየተቀጣጨ የሚገኘውና የሁሉም ባለድርሻ አካላት አቢይ ተግባር የሆነው አማራን ሸኮና ሸኮናውን እየቀጠቀጡ ማሽመድመድ ነው፡፡ ይህ ዘመቻ የሚካሄደው በአፋቸው ኢትዮጵያውያን ነን በሚሉ ሰዎች ይሁን እንጂ መነሻው የዓለም አቀፍ ኢሉሚናቲዎች ፀረ-አማራና ፀረ-ኦርቶዶክስ በድምሩም ፀረ-ኢትዮጵያ ነባር ዘመቻ ቅጣይ መሆኑን ለመረዳት ቂጥኛም ከውርዴ የሚሞዳሞድበትን የወቅቱን ሀገራዊ የፖለቲካ ዐውድ ማጤን ብቻ በቂ ነው – ባጭሩ የሕወሓት አማራንና ኦርቶዶክስን የማጥፋት የለካቲት 68 ማኒፌስቶ ግዘፍ በነሳ መልክ እየተተገበረ ነው፤ከዚያም ባለፈ ሴቴኒዝም እንዲስፋፋ በስፋት ጥረት እየተደረገ ነው – ለማየት ያብቃችሁ በቅርቡ ሴትና ሴት፣ ወንድና ወንድ ሲጋቡ ጠ/ሚኒስትሩ ለክብር እንግድነት ይታደማል …፡፡ እነዚህ ጊዜ ሰጠን ብለው ከላይ እስከታች እንደቀትር እባብ የሚቅነዘነዙ የፖለቲካ ሴተኛ አዳሪዎች (ይቅርታ – ቃሉ ትንሽ ስለሚያስጠይፍ “ሸርሙጦች” ላለማለት ነው) አማራን ለማጥፋት ከዚህ ጊዜ በላይ ምቹ አጋጣሚ እንደሌለ አምነው በሙሉ አቅማቸው እየተራወጡ ይገኛሉ፡፡ እውነታቸውን ነው – ጌቶቻቸው አንድ ፈሊጥ አላቸው:- Hit the iron when it is hot! የሚል፡፡ በርግጥም ከወርቃማው ኢትዮጵያዊ ዘመን በፊት ታሪክ በአዳፋ እጆቹ አስተናግዶ መቀመቅ የሚከታቸው የመጨረሻዎቹ እንክርዳዶች ናቸው፡፡ ይህን ጠብቁ!!
እነአምባቸውንና አሣምነውን በይቺ ባቄላ ካደረች … ተረት በጊዜ አጠፉ፡፡ በሰበቡም የሚያስሩትንና ከፖለቲካ ጨዋታ ውጭ ማድረግ የሚፈልጉትን ሁሉ ባቀዱት መሠረት አደረጉ፡፡ በምትካቸውም የግንቦት ሰባት ሰዎችን በአማራው ላይ መደቡ፡፡ ለዚህና ለመሰል ተግባሮቻቸው ግንቦቶች ከጀርባ ሆነው እሥር ቤት የነበሩ ጅላጅል አማሮችን ከፊት በማሰለፍ አማራውን ለማነሁለል ሞከሩ – እምብዝም ባይሳካም፡፡ አማራ – በነገራችን ላይ አውቆ የተታለለ ይመስላል እንጂ – በቀላሉ አይታለልም፡፡ እንዲያውም የተታለለ እየመሰለ አጋጣሚውን ሲያገኝ ጉድ የሚሠራ ነው – አማራ፡፡ ምንም ያልተማረውን ባላገር አማራ ሂድና ለማታለል ሞክር – እየሣቀ አንተኑ ያነሆልልሃል፡፡
የአማራ ጠላቶች አሁን ከዳዴ አልፈው ቆመው እየሄዱ ያሉ ይመስላሉ፡፡ ሰሞኑን ደግሞ ትንታጎቹን እነዮሐንስ ቧ ያለውንና ተፈራ ወንድማገኝን ገለል አደረጉ፡፡ ሁለቱም ጎበዝ ነበሩ፡፡ አማራው በተስፋ የሚጠብቃቸው ነበሩ፡፡ ግን የአቢይ ሠይፍ በነፍስ ባይሆንም በአካል ከድርጅታቸው – ከእጅ አይሻል ዶማ አሽከር ድርጅታቸው – ገለል እንዲሉ አደረጋቸው፡፡ በነፍስ አይምጡባቸው እንጂ ይህስ ቀላል ነው፡፡ ይሄ አቢይ የሚሉት ጉድ ግን በዚህ ዕድሜው ይህን ሁሉ ፖለቲካዊ ሤራና ሸፍጥ፣ አፍዝ አደንግዛዊ የማጭበርበርና ሰውን በ“ፍቅሩ” የማነሁለል አጋንንታዊ ድግምትና መተት ከየት አገኘው? ያቺን የዐፄ ኃ/ሥላሤን ጦሰኛ የጣት ቀለበት አቀብለውት ይሆን? መጠርጠር ነው!
በተለይ ተፈራ ወንድምአገኝ ብርቱ ሰው ነበር፡፡ ለአማራውም ሆነ ለኢትዮጵያ ተቆርቋሪ እንደነበር ከሚያደርጋቸው ንግግሮች መረዳት ይቻል ነበር፡፡ ነገር ግን ጥሩ ዜጋ ሆኖ መገኘት ለአቢይ የቆረጣ ውጊያ ይዳርጋልና ሌሎችም ተጨምረው ተንሳፈፉ፡፡ አቢይ የክፋቱ ክፋት ዮሐንስን በሕይወት መኖር አለመኖሩ እንኳን የማይታወቀውን የመለስ ፋውንዴሽን የሚባል ሙትቻ ተቋም የበላይ ጠባቂ አድርጎ “መሾሙ” ነው፡፡ ይህ “ሹመት” ሰውዬውን በሞራልም ለመግደል የታሰበ መሆኑን አመላካች ነው፡፡ በትግርኛ “ውፃዕ አይትበሎ ከምጽወፅዕ ግበሮ” ይባላል – በአማርኛ ስለመኖሩ አላውቅም፡፡ “ውጣ አትበለው እንዲወጣ ግን አድርገው” እንደማለት ነው፡፡ በነሱ ቤት ብልጥ ሆነው ሞተዋል፡፡
ኢዜማም በሉት ግንቦት ሰባት አቢይም በሉት ጃዋር እንደሚመጡ እናውቅ ነበር – በስማቸውና በያዙት መልክና ቁመት ሳይሆን በዕኩይ ምግባራቸው ፡፡ እንደሚያልፉም እናውቅ ነበር፡፡ማለፊያቸው ቀጭን መንገድም ልትመጣ በግንባር እየገሰገሰች ናት፡፡ ኢትዮጵያውያን ጸንታችሁ ቁሙ፡፡ ይህ ግብስብስ ዘመን ወደ ታሪክ ማኅደርነት ሊጠቀለል የቀረው እጅግ ጥቂት ጊዜ ነውና ከስህተት ተጠብቃችሁ ወደ ላይ አንጋጡ፡፡ ወጣቶችና ጎልማሦች ጊዜው የሚያዛችሁን የጀግንነት ተግባር ለመፈጸም የጊዜን ትዕዛዝ በተጠንቀቅ ጠብቁ – ጊዜና ፈጣሪ ጀግኖችን በጊዜው ይወልዳሉና በምታዩት ጽልመት አትደናገጡ፤ ሊሆን ግድ ነውና፡፡ ይህችን አገር ለመጉዳት የተሰባሰበ የጥፋት ሠራዊት ሁሉ የዶግ ዐመድ የሚሆንበት ዘመን እጅግ የተቃረበ በመሆኑ ደስ ይበላችሁ፤ የሚባለው ሁሉ ሳይሆን ያልቀረ በመሆኑ የምንለው ሁሉ እውነት ነው፡፡ ችግሩ ሞት ሲዘገይ የቀረ መምሰሉ ነው፡፡
እነቁጭ በሉዎችም ለጊዜው ተደሰቱ፡፡ በአማራው ላይ እንደልባችሁ ናኙበት፡፡ ቦርቁበት፡፡ ቋቱ እስኪሞላ እንደፈለጋችሁ አሽቃንጡበት፡፡ ቋቱ ሲሞላ ግን ወዮ ለእናንተ! በፋሲካ የተቀጠረች ገረድ ሁሌ ፋሲካ ይመስላታል፡፡ በትዕቢትና በዕብሪት የተወጠረ አካልም ሁሌ በአሸናፊነት ስሜት እንደታወረ ነው፡፡ጋዳፊም እኮ ከተደበቀበት የቆሻሻ ቱቦ ወጥቶ ሣንጃ በእንትኑ እስኪወደወድበት ድረስ የሊቢያ መሪ እንደሆነ ይሰማውና ያምንም ነበር፡፡ አምባገነኖች እንደዚህና እስከዚህም ገገማዎች ናቸው፡፡ ነገ የሚሞት አምባገነን ዛሬ ሚሊዮኖችን ሲጨፈጭፍና ሲያስጨፈጭፍ በውስጡ የመሸገው ዕብሪትና ትዕቢት አይፈቅድለትምና አንድም ርኅራሔ የለውም፤ ይህ ዓይነቱ ተፈጥሮም ያሣዝናል፡፡
አምባቸው ደጀኔ (ከወልዲያ)

“ለመንግስት ልጆቻችን አገናኙን ብለን ብንጠይቅ ኢንተርኔት የለም ተባልን።” የታገቱ አማራ ተማሪዎች ወላጆች

“ለመንግስት ልጆቻችን አገናኙን ብለን ብንጠይቅ ኢንተርኔት የለም ተባልን።” የታገቱ አማራ ተማሪዎች ወላጆች

“ለመንግስት ልጆቻችን አገናኙን ብለን ብንጠይቅ ኢንተርኔት የለም ተባልን።” የታገቱ አማራ ተማሪዎች ወላጆች

የጥላቻ ንግግር ህግ አዋጅ አንድምታዎች – ሰማሃኝ ጋሹ (ዶ/ር)


መግቢያ
የኢትዮጵያ መንግስት በአገሪቱ ያለዉን አለመረጋጋት ለመቆጣጠር ያስችለኛል ያለዉን የጥላቻ ህግ ረቂቅ አዋጅ ይፋ በማድረግ ህጉን በማፅደቅ ተግባራዊ ለማድረግ በእንቅስቃሴ ላይ ይገኛል። አገሪቱ ዉስጥ ያለዉ የፖለቲካ አለመረጋጋት መፍትሄ የሚሻ ጉዳይ መሆኑ አከራካሪ አይደለም። ዶ/ር አብይ ወደ ስልጣን ከመጡበት መጋቢት 24 2010 ዓ.ም ጊዜ ጀምሮ አግሪቱ በከፍተኛ የፖለቲካ ለዉጥና ነዉጥ ዉስጥ ትገኛለች። ለዉጡን ተከትሎ የመጣዉ የፖለቲካ ምህዳሩ መከፈት ግለሰቦች፥ የብሄር ድርጅቶችና ሚድያዎች ሃሳባቸዉን በአንፃራዊ ነፃነት የሚገልፁበት ሁኔታ ተፈጥሮ ነበር። የአገሪቱ የፖለቲካ አወቃቀር ብሄርን መሰረት ያደረገ በመሆኑ የፖለቲካ ምህዳሩ መከፈት ተከትሎ ብሄር ተኮር የፖለቲካ ሃይሎች በተለያዩ የአገሪቱ አካባቢዎች ተጠናክረዉ በመዉጣታቸዉ የብሄር ግጭት፥ መፈናቀል፥ ዝርፊያና አለመረጋጋት በተለያዩ አካባቢዎች ተከስቷል። በቅርቡ በአማራና በደቡብ ክልሎች የተከሰቱትን ግጭቶች ተከትሎ መንግስት የሃይል እርምጃ በመዉሰድ ብዙዎች ለእስር ተዳርገዋል። መንግስት ከፍተኛ ተቃዉሞ የቀረበበትን የ ፀረ ሽብርተኝነት ህጉን በመጠቀም የሰብአዊ መብት ተከራካሪዎች ላይ ክስ ማቅረቡ ለዉጡ እየተቀለበሰ ነዉ የሚል ስጋት አድሮባቸዋል። አገሪቱ ዉስጥ ካለዉ ዘርን መሰረት ባደረገዉ የፖለቲካ ስርአት ምክንያት የዘር መከፋፈልና ጥላቻ እየተስፋፋ በመምጣቱ የጥላቻ ህግን ማዉጣት በመርህ ደርጃ አስፈላጊ ቢሆንም የህጉ መዉጣት የሚያስከትለዉን ችግር ማንሳት አስፈላጊ ነዉ። ይህ ፅሁፍ የጥላቻ ህግ ታሪካዊ አመጣጥ ፥ አለም አቀፍ ልምዶችና በኢትዮጵያ ተጨባጭ ሁኔታ ባለዉን ህገ መንግስታዊ ስርአትና ፖለቲካዊ ሁኔታ አንፃር በመዳሰስ የመፍትሄ ሃሳቦችን ለመጠቆም ይሞክራል።
1. የጥላቻ ህግ ታሪካዊ አመጣጥና አለም አቀፍ ልምዶች
የጥላቻ ህግ ታሪካዊ አመጣጥ ሃሳብን በነፃነት ከመግለፅ ጋር በቅርብ የተቆራኘ ነዉ። ሃሳብን በነፃነት የመግለፅ መብት በጥንታዊ አቴንስ ከክርስቶስ ልደት በፊት በስድስተኛዉ ክፍለ ዘመን ጀምሮ ትኩረት ያገኘ መሰረታዊ መብት ነዉ። ሃሳብን በነፃነት የመግለፅ መብት በ17ኛዉ ክፍለ ዘመን በነበረዉ የእንግሊዝ የመብት ትግል እንዲሁም እ.ኤ.አ. በ1789 ዓም በፈረንሳይ አብዮት ወቅት የወጣዉ የሰዉ ልጆች መብት ድንጋጌ ሃሳብን በነፃነት የመግለፅ መብት ትልቅ ዋስትና ሊኖረዉ የሚገባ ጉዳይ መሆኑን አፅኖት አድርጎበታል። እ.ኤ.አ. በ 1789 ዓም የወጣዉ የአሜሪካ ህገ መንግስት የመጀመርያዉ ማሻሻያ ( First Amendment) የአሜሪካ ም/ቤት ሃሳብን የመግለፅ ነፃነትን የሚገድብ ምንም አይነት ህግ ማዉጣት እንደማይችል በመደንገግ የንግግር ነፃነት በአሜሪካ ማህበረሰብና በአለም አቀፍ ደረጃ ገደብ እንዳይደረግበት ከፍተኛ አስተዋፅኦ እንዲኖረዉ አድርጓል።
የተባበሩት መንግስታት ድርጅት እ.ኤ.አ. 1945 ዓም ከተመሰረተበት ወቅት ጀምሮ ትኩረት ያገኘዉ የሰብአዊ መብት ጥበቃ ሃሳብን በነፃነት የመግለፅን መብት በአለም አቀፍ ደረጃ ትኩረት እንዲያገኝ አድርጎታል። እ.ኤ.አ. በ 1948 ዓም የወጣዉ አለም አቀፉ የሰብአዊ መበት ድንጋጌ
( Universal Declaration of Human Rights) በአንቀፅ 19 ላይ እንዳስቀመጠዉ ማንኛዉ ሰው ሃሳቡን በነፃነት የመግለፅና የማሰራጨት ያለገደብ መብት እንዳለዉ አረጋግጧል። እንዲሁም እኤአ በ 1966 ዓም የወጣዉ አለም አቀፉ የሲቪልና የፖለቲካ መብቶች ድንጋጌ ( International Covenenat on Civil and Poltical Rights) አንቀፅ 19 ላይ የተቀመጠዉ ሃሳብን በነፃነት የመግለፅ መብት አሁን በአለም አቀፍ ደረጃ ትኩረት ላጋኘዉ ህሳብን በነፃነት የመግለፅ መብት እንቅስቃሴ መሰረት ጥሎአል። የቀዝቃዛዉን ጦርነት ማብቃት ተከትሎ በጭቆና ስር የነበሩት ታዳጊ አገሮችም ሳይቀሩ ሀሳብን በነፃነት መብትን እውቅና የሚሰጥ የህገ መንግስትና የፖለቲካ ስርአት ደንግገዋል።
ከቅርብ ጊዜ ወዲህ የተከሰቱ አለም አቀፍ ሁኔታዎች የጥላቻ ንግግር እንዲስፋፉ ምክንያት እንደሆኑ ይታመናል። ሉላዊነት ( globalaization) በአሜሪካና አዉሮፓ በሃብታምና ድሃዎች መካከል የፈጠረዉ ልዩነትና ስደተኞች ያለ ገደብ ድንበር አቋርጠዉ መግባታቸዉ በስደተኞች ላይ ጥላቻን መሰረት ያደረጉ ወንጀሎች እንዲስፋፉና ቀኝ አክራሪ ብሄርተኛ ፖለቲከኞች የፖለቲካ ስልጣን እንዲይዙ ምክንያት ሆንዋል። ከዚህም በተጨማሪ በድህረ ገፆችና ማህበራዊ ሚድያዎች የሚሰራጩ የጥላቻ ንግግሮችና ሀሰተኛ ወሬዎች ( fake news) በከፍተና ደረጃ በመጨመሩ መንግስታት ይህንን አካሄድ ለመቆጣጠር ከፍተኛ ሙከራ እያደረጉ ነዉ። ከቅርብ አመታት ወዲህ የመገናኛ ብዙሃን ቴክኖሎጂ በከፍተኛ ሁኔታ በማደጉ ምክንያት ሃሳብን በነፃነት የመግለፅ መብት በከፍተኛ ደረጃ እድገት አሳይቷል።

በተለይም ደግሞ በኢንተርኔት ቴክኖሎጂ እድገት ምክንያት የመረጃ አቅርቦትና ስርጭትን ታላቅ እምርታ የታየበት ሲሆን ማህበራዊ ሚዲያዉ መደበኛ የመገናኛ ብዙሃንን በመተካት ሃሳብን በነፃነት የመግለፅ ነፃነትን አስገራሚ በሆነ ሁኔታ ቀይሮታል። አለማችንን ያስተሳሰረዉ የቴኖሎጂ እድገት ግን የራሱን ችግሮች ይዞ ብቅ ብሎአል። የመገናኛ ብዙሃንን በመጠቀም የሚፈፀሙ የሽብርና የጥላቻ ንግግሮች የፈጠሩት ተፅእኖ ቴክኖሎጂዉን ለመቆጣጠር አቅም የሌላቸዉን ብቻ ሳይሆን በቴክኖሎጂ የበለፀጉትንም አገራት ስጋት ላይ ጥሎአል። ይህ ችግር በተለይ በታዳጊ አገሮች ላይ ከፍተኛ ችግር እየፈጠረ ይገኛል። እንደ ኢትዮጵያ ያሉ ለዘመናት በጭቆና ዉስጥ ያሉ አገሮች ማህበራዊ ሚድያዉ ከፍተኛ የመረጃ ምንጭ ተደርጎ ስለሚቆጠር የራሱ በጎ ቢኖረዉም የጥላቻና ሃሰተና ወሬዎች በማሰራጨትና ከፈተኛ ችግር ይፈጥራል። በአደጉትም ሆነ በታዳጊ አገሮች በማህበራዊ የትስስር መድረኮች የሚተላለፉ የጥላቻ ንግግሮች ስደተኞችንና በቀለም ወይም በዘር ከህብረተሰቡ ለየት ያሉ ግለሰቦች ለጥቃት እንዲጋለጡ ማድረጉን ጥናቶች አረጋግጠዋል። በተለይ በአዉሮፓና አሜሪካ ቀኝ ዘመም የፖለቲካ መሪዎች ወደ ስልጣን መምጣት ብሄረኝነትንና ዘረኝነትን አልፈዉታል የሚባሉትንም ዴሞክራሲያዊ ስርአት የገነቡትን አገሮችንም የጥላቻ ንግግር እየናጣቸዉ ይገኛል። የተባበሩት መንግስታት ድርጅት በቅርቡ በአወጣዉ መግለጫ ፀትላቻ ንግግሮች በለም ዙርያ በከፍተኛ ደረጃ እያደጉ መምጣታቸዉን በመግለፅ ይህን ለመቋቋም የሚያስችል የድርጊት መርሃ ግብር ቀይሷል።
ምንም እንኳን የጥላቻ ንግግር በአለም አቀፍ ደረጃ ትኩረት እያገኘ ቢመጣም የጥላቻ ንግግር ምን ማለት እንደሆነ የሚያስረዳ አለም አቀፍ ስምምነት ግን የለም። የአዉሮፓ ም/ቤት ያወጣዉ አንድ ሰነድ የጥላቻ ንግግርን ማንኛዉም ዘርን ፥ የዉጭ አገር ዜጎችን፥ አይሁዳውያንን አስመልክቶ የሚያሰራጭ፥ የሚያነሳሳና የሚያስፋፋ ማንኛዉም ሃሳብን የመግለፅ መንገድ በተለይም ህዳጣንንና ስደተኞችን የሚያገል ፅንፈኛ ብሄርተኝነት፥ አድልዎና ጥላቻ የሚያካትት መሆኑን ይገልፃል። አለም አቀፍ የሰብአዊ መብት ድንጋጌዎች የጥላቻ ንግግር ምን እንደሆነ ግልፅ ትርጉም ባይሰጡም ሃሳብን በነፃነት የመግለፅ መብት የጥላቻ ንግግሮች ለመቆጣጠር ገደብ ሊጣልበት እንደሚችል ይደነግጋሉ። እ. ኤ. አ. በ1966 ዓም የወጣዉ አለም አቀፉ የሲቪልና ፖለቲካዊ መብቶች ስምምነት ሃሳብን በመነፃነት የመግለፅ መብትን መሰረታዊ የሰብአዊ መብቶች አካል አድርጎ ቢቀበለዉም ማንኛዉም የብሄርን፥ የዘርና የሃይማኖት ጥላቻ የሚያስፋፋ ንግግር መድልዎን፥ ጥላቻንና ጥቃትን የሚያነሳሳ ስለሆነ በህግ እንደሚከለከል ይደነግጋል።
እ.ኤ.አ. በ 1965 የወጣዉ አለም አቀፉ የፀረ መድልዎ ስምምነት ማንኛዉንም የዘር የበላይነትን፥ ጥላቻንና የዘር መድልዎን ወይም ጥቃት እንዲደርስ የሚገፋፉ ማንኛዉንም ግግሮችን ማሳራጨት በወንጀል እንዲቀጡ አባል አገራትን ያሳስባል ።
የዴሞክራሲያ ስርአት አገሮች የጥላቻ ህግን የሚያስተናግዱበት መንገድ ይለያያል። በተለይም የዴሞክራሲያዊ ስርአት በሚከተሉት አሜሪካንና አዉሮፓ አገሮች የጥላቻ ህግን አስመልክቶ ያላቸዉ ልምድ በእጅጉ ይለያያል። በሁለተኛዉ የአለም ጦርነት ወቅት ናዚ ጀርመን በአይሁዳዉያን ላይ በፈፀመዉ ጥላቻን መሰረት ያደርገ ዘር ማጥፋት ወንጀል ምክንያት በአዉሮፓ የንግግር ነፃነትን የሚገድብ ጠንከር ያሉ የጥላቻ ህጎች ወጥተዋል። ዴንማርክ፥ ፈረንሳይ፥ ኔዘርላንድና እንግሊዝን በመሳሰሉት አገሮችም ማንኛዉም ዘርን፥ ሃይማኖትንና ፆታን መሰረት ያደርገ የጥላቻ ንግግርም ሆነ ስድብ የተከለከለ ነዉ። በአዉሮፓ ዉስጥ ሃሳብን በነፃነት የመግለፅ መብት እዉቅና ያለዉ ቢሆንም በርካታ ገደቦች ይጣሉበታል። ከጦርነቱ ማብቃት በሁዋላ የአዉሮፓ አገሮች የተስማሙበትና እ.ኤ.አ. በ1950 ዓም በአዉሮፓ ም/ቤት የፀደቀዉ የአዉሮፓ የሰብአዊ መብት ስምምነት ሃሳብን በነፃነት የመግለፅ መብትን እውቅና ቢሰጥም ገደብ ሊጣልባቸዉ የሚቻልበትን ምክንያቶች ይዘረዝራል። በዚህም መሰረት ሃሳብን በነፃነት የመግለፅ መብት የዴሞክራሲ ስርአት ለመገንባት፥ ለብሄራዊ ደህንነት፥ የሃገር አንድነትና የህዝብ ደህንነት ለመጠበቅ፥ ሁከትን ወይም ወጀልን ለመከላከል፥ የህዝብን ጤና ወይም ግብረገብነትን ፥ የሌሎች ሰዎችን ክብርና ደህንነት ለመጠበቅ በህግ ገደብ ሊጣልበት ይችላል። ይህንንም ድንጋጌ መሰረት በማድረግ በርካታ የአዉሮፓ አገሮች የጥላቻ ህግን የሚቆጣጠር ህጎችን አዉጥተዋል። ሌሎች የአዉሮፓ አቀፍ ተቋማትም የጥላቻ ህግን በማስመልከት በርካታ ህግጋትን ደንግገዋል። የአዉሮፓ ም/ቤት የሚኒስትሮች ኮሚቴ ያወጣዉ የጥላቻ ንግግር ትርጉም ሰፋ ያለ ዝርዝር ያለው ነዉ። ኮሚቴዉ የጥላቻ ንግግርን ማንኛዉም የዘር ፥ የዉጭ ዜጎችን፥ ፀረ ሴማዊነት ጥላቻን የሚያንሳሳ፥ የሚያሰራጭና የሚያስፋፋ ንግግር ወይም መቻቻልን የሚፃረር ፅንፈኛ የሆነ ብሄርተኝነት እንዲሁም የህዳጣንንና ስደተኞችን መድልዎና ጠላትነት የሚያስፋፋ ንግግርን ያጠቃልላል። የአዉሮፓ ፀረ ዘረኝነት ኮሚሽን ምክረ ሃሳብም የጥላቻ ንግግርን ምንነት በእጅጉ በመለጠጥ ማንኛዉንም ግለሰብ ወይም ቡድን ዘር፥ ፆታ፥ ሃይማኖት፥ ቋንቋ፥ ወይም ሌላ መለያ መሰረት በማድረግ የሚደረግ ስድብ፥ ማንቋሸሽና አሉታዊ ንግግር ሁሉ የጥላቻ ንግግር ተደርጎ እንደሚቆጠር ይገልፃል። የአዉሮፓ ህብረት ምክረ ሃሳብ የዘር ፍጅት መካሄዱን መካድ ፥ ማጣጣል ወይም መደገፍን አባል ሃገራት እንደ ጥላቻ ንግግር በመቁጠር በወጀለኛ ህጋቸው ዉስጥ እንዲያካትቱ ያሳስባል።
በአንዳንድ የአዉሮፓ አገሮችን ያለዉን የጥላቻ ህግ መዳሰሱ በአዉሮፓ ዉስጥ ያለዉን ሁኔታ ለመረዳት ያስችላል። ጀርመን በሁለተኛዉ የአለም ጦርነት ከደረሰባት ከፍተኛ ዉድቀት የተነሳ ጠንካራ የሚባል የጥላቻ ህግ አውጥታለች። በጀርመን የወንጀለኛ መቅጫ ህግ ማንኛዉም ሰዉ የህዝብን ሰላም ለማወክ አንድን የብሄር፥ ዘር፥ ሃይማኖት ማህበረሰብ ወይም ግለሰቦችን ያላቸዉን ሃይማኖት ወይም ዘር መሰረት በማድረግ የጥላቻ ቅስቀሳ ያደረገ ወይም እነዚህን የህብረተሰብ ክፍሎችን ክብር የሚነካ ስድብና ማዋረድ ያደረገ ከሶስት ወር እስከ አምስት አመት እስራት ያስቀጣል። ጀርመን ዉስጥ የናዚን ምልክት ማሳየት ወይም በአይሁዳዉያን ላይ የደረሰዉን የዘር እልቂት መካድም እንደ ጥላቻ ወንጀል በመቆጠር ያስቀጣል።
ከዚህ ባለፈ ጀርመን በቅርቡ ያወጣችዉ በኢንተርነኔት የሚተላለፉ የጥላቻ ወይም ህገወጥ መልእክቶችን የሚቆጣጠር አዋጅ የማህበራዊ የትስስር መረብ ባላቤቶች ህገወጥ የሆኑ መልእክቶችን በአጭር ጊዜ ዉስጥ ካላነሱ ድርጅቶች በሚልዮን ዶላር የሚቆጠር ቅጣት እንዲጣልባቸዉ ያዝዛል። የጀርመን ወንጀለኛ መቅጫ ህግ የጥላቻን ህግ ከመከልከል ባለፈ ‘ኢ ህገ መንግስታዊ’ የፖለቲካ ድርጅቶችን አርማዎችና ምልክቶች በአደባባይ መያዝን ህገ ወጥ በማድረግ በተለይ የናዚ ፓርቲ መለያዎች ለምርምርና ትምህርታዊ አላማዎች ዉጪ በማንኛዉም መልኩ መጠቀም የተከለከለ የጥላቻ ንግግር አካል አድርጎ ያስቀምጠዋል። ፊንላንድም ማንኛዉም ዘርንና ሃይማኖትን መሰረት አድርገው የሚነዙ የጥላቻ ቅስቅሳዎችን በህግ ከልክላለች። በተለይም የጥላቻ ንግግሩ የዘር ፍጅት እንዲከሰት የሚቀሰቅስ ከሆነ ከበድ ያለ ቅጣትን ያስከትላል። እንግሊዝም በተመሳሳይ ማንኛዉም ሰዉ ጥላቻን መሰረት ያደረገ የፅሁፍም ሆነ ሌላ አይነት ምልክት በመጠቀም የዘር ጥላቻን ለመቀሰቀሰ የሞከረ ከባድ የእስር ጥቃት ያስከትላል። በሁሉም የአዉሮፓ አገሮች የጥላቻ ንግግርን የሚቆጣጠሩ ህግጋት ተግባራዊ ተደርገዋል።
ከአዉሮፓ በተቃራኒዉ በአሜሪካ የጥላቻ ንግግር ሃሳብን በነፃነት የመግለፅ አካል ተደርጎ ስለሚቆጠር ንግግሩ ብቻዉን አያስቀጣም። በአሜሪካ ዉስጥ ያለዉን ሰፊ ሃሳብን በነፃነት የመግለፅ መብት የመጀመርያዉ የህገ መንግስት ማሻሻያ ተብሎ በሚታወቀዉ ህግ ዋስትና ያገኘ ነዉ። በዚህ ህግ መሰረት የአሜሪካ ኮንግረስ ሃሳብን በነፃነት የመግለፅን፥ የመሰብስብንና የእምነት ነፃነትን የሚገድብ ምንም አይነት ህግ ማዉጣት አይችልም። የአሜሪካ ጠቅላይ ፍ/ቤት የጥላቻን ንግግሮችን አስመልክቶ የተለያዩ ዉሳኔዎች የሰጠ ቢሆንም የጥላቻ ህግን እንደ ወንጀል ቆጥሮአቸዉ አያዉቅም። ፍ/ቤቱ እ.ኤ.አ. በ 1969 ዓም በሰጠዉ ዉሳኔ መንግስት የጥላቻ ንግግሩ ረብሻን የመቀስቀስ እድሉ የማይቀር ከሆነ ብቻ መንግስት እንዲህ አይነቱ ንግግር ገደብ ሊጥልበት እንደሚችል ይፈቅዳል። ከዚህ ዉጭ ግን አንድ ንግግር የዘር ጥላቻን የሚመመለከት ነው በሚል ብቻ በህግ አያስጠይቅም። የጥላቻ ንግግር ገደብ እንዲዲደረግበት የሚጠይቁ እንቅስቃሴዎች ቢኖሩም እስከ አሁን የጥላቻ ንግግርን የሚፈቅደዉ ህግ አልተሻሻለም። አሜሪካ ህገ መንግስት ሃሳብን በነፃነት መግለፅ ያለ ገደብ የተጠበቀ በመሆኑ ከጥላቻ ንግግር ( hate speech) ይልቅ የጥላቻ ወንጀል ( hate crime) በህግ ከባድ ቅጣት ያስከትላል። ማንኛዉም የዘር ጥላቻን መሰረት አድርጎ በንብረት ወይም በሰዉ ላይ የሚፈፀም የጥላቻ ወንጀል ተደርጎ ይቆጠራል። በአሜሪካን ህግ አንድ ሰዉ በዘር ወይም ሃይማኖታዊ ጥላቻ ላይ ተመስርቶ የሚፈፅመዉ ማንኛዉም ጥቃት ከፍተኛ የሆነ የወንጀል ተጠያቂነት ያመጣል። የሜሪካን ህግ ከፍተኛ ትኩረት የሚያደርገዉ ከጥላቻ ንግግር ይልቅ የጥላቻ ወንጀሎች በጥብቅ መከታተል ላይ ነዉ ።
2. ዘር ተኮር ፖለቲካና የጥላቻ ንግግር
በአለማችን ያሉት ዴሞክራሲያዊ አገሮች መሰረት የሆነዉ ሌብራል አስተሳሰብ ዜጎች ያላቸዉን የሃይማኖትና የዘዉግ ማንነት ወደ ጎን በመተዉ ዜጎች በሰዉነትወይም ዜግነት እኩል መብት እንዲኖራቸዉ በማድረግ ከጎሳና ሀይማኖት ልዩነት ምክንያት ሊፈጠር የሚችለዉን ግጭት በማስወገድ የተረጋጋና የበለፀገ ማህበረሰብ እንዲፈጠር አስችሎአል። አዉሮፓውያን ለረጅም ዘመናት በሃይማኖትና ቋንቋ ልዩነት እርስ በርስ በጦርነት ሲታመሱ ከኖሩ በሁዋላ በመጨረሻዉ ብቸኛ መፍትሄ አድርገዉ የወሰዱት ሃይማኖትንና ብሄርን ከፖለቲካ ሂደቱ በማስወጣት በሲቪል ብሄርተኝነት (civic nationalism) ላይ የተመሰረተ የፖለቲካ ስርአት ማካሄድ ነው። በተቃራኒው ከሊብራል ፖለቲካዊ እሳቤ ያፈነገጠዉ ፋሽዝም በሁለተኛዉ የአለም ጦርነት ወቅት የፈጠረው እልቂት፤ አክራሪ ብሄርተኝነት የሚወልደዉ ጥላቻ ምን ያህል ጥፋት እንደሚያደርስ በመረዳት መረዳት ይቻላል።
በታዳጊ አገሮች ያለዉ ሁኔታ ከአውሮፓ በእጅጉ የተለየ ነዉ። ቅኝ ገዥዎች በአፍሪካ ዉስጥ ያላቸዉን ስልጣን ለማስጠበቅ ህዝቡን እርስ በርስ በጎሳ እንዲከፋፈል በማድረግ ፖለቲካዊ ትርጉም ያልነበራቸዉን የቋንቋ ልዩነቶች በማራገብ ህዝቡን የጎሪጥ እንዲተያይ በማድረግ ያልተቋረጠ ግጭት እንዲፈጠር አድርገዋል። ለዚህ ጥሩ ምሳሌ የሚሆነው ቤልጅየም በሩዋንዳ የፈፀመችው የዘር መከፋፈል ነዉ። አንድ ቋንቋ የሚናገሩትን የሁቱና የቱትሲ ጎሳዎች አንዱን የበላይና ሌላዉን የበታች አድርጎ በማቅረብ እርስ በርስ እንዲቃቃሩ በማድረግ በመጨረሻ ለተፈፀመዉ የሩዋንዳ ዘር ማጥፈት ወንጀል ምክንያት ሆነዋል። በ 1994 ዓም በሩዋንዳ ከተፈፀመዉ የዘር ማጥፋት ወንጀል በሁዋላ ሩዋንዳ ዉስጥ ማንም ሰዉ ሌላዉን ጎሳህ ምንድን ነዉ ብሎ እንዳይጠይቀዉ በመከልከሉ አገሪቱ ብሄርን መሰረት ካደረገ ጥላቻና ግጭት ነፃ ሆናለች። በሌሎች የአፍሪካ አገሮችም ቅኝ ገዥዎች ያመጡትን የዘር መከፋፋል በማስወገድ ማንኛዉም የዘር ጥላቻን መሰረት አድርጎ በንብረት ወይም በሰዉ ላይ የሚፈፀም የጥላቻ ወንጀል ተደርጎ ይቆጠራል። የብሄር ፖለቲካ የሚያመጣዉን ጠንቅ በመረዳት ብዙዎች የአፍሪካ አገሮች በህገ መንግስታቸዉ በዘር ወይም በሃይማኖት ላይ የተመሰረት የፖለቲካ አደረጃጀትንም ከልክለዋል።
3. የብሄር ፖለቲካ የጥላቻ ንግግር በኢትዮጵያ
ጥንታዊ ሃገረ መንግስት የነበራትና ብቸኛዋ በአዉሮፓዉያን ቅኝ ያልተገዛችዉ ኢትዮጵያ ደግሞ በተቃራኒዉን ዘርን መሰረት ባደረገ ፖለቲካ ተጠላልፋ ህልዉናዋ አሳሳቢ ደረጃ ላይ ይገኛል። በሰኔ 2019 የወጣዉ የሎስ አንጀለስ ታይምስ ጋዜታ እንደዝገበዉ ኢትዮጵያ በአገሪቱ በተፈጠረዉ ዘርን ማዕከል ባደረገ ጥቃት ወደ ሶስት ሚልዮን የሚቆጠሩ ዜጎች ከቀያቸዉ እንደተፈናቀሉ ገልጿል። ይህም ሁኔታ አገሪቱን በተፈናቃዮች ቁጥር በአለም አቀፍ ደረጃ ግንባር ቀደም እንድትሆን አድርጓታል። የዚህ መፈናቃልና ስደት ብቸናው ምክንያት አገሪቱ ለአለፉት 28 አመታት ተግባራዊ ያዳረገችዉ ዘርን መሰረት ያደረገዉ የፖለቲካ ስርአት መሆኑ ግልፅ ነዉ።
በተማሪዎንች እንቅሳቅሴ በ 1960ዎቹ ወደ ኢትዮጵያ ፖለቲካ ብቅ ያለዉ የብሄር ፖለቲካ ከጅምሩም በጥላቻ የተወለደ ነዉ። ማርክሲዝምንም ሆነ የአገሪቱን ታሪክ ያልተገነዘቡት የዩንቨርስቲ ተማሪዎች የኢትዮጵያ ችግር ‘የብሄር ጭቆና ነዉ’ በሚል በወስዱት አቋም ባለፉት 50 አመታት የአገሪቱን ፖአቲካ ትርምስ ዉስጥ ከቷታል ። በተለይ ህወሃት፥ ሻእብያና ኦነግን የመሳሰሉት የብሄር ድርጅቶች ‘አማራ ጨቁኖናል’ በሚል ተንሳስተዉ ተከታዮቻቸዉ ፀረ አማራ አስተሳሰብ እብዲኖራቸው በማድረግ አማራዉ ማህበረሰብ በሌሎች ቋንቋ ተናጋሪዎች እንደ ጠላት እንዲያታይ አድርገዉታል። በተለይም ህወሃት በ1968 ዓም ባወጣዉ የፖለቲካ ፕሮግራም አማራዉ የትግራይ ጠላት እንደሆነ በማስቀመጥ የትጥቅ ትግል አድርጎ የፖለቲካ ስልጣን በመያዝ የጥላቻ ፕሮግራሙን ወድ ተግባር የሚቀይርበት እድል አግኝቶ አማራዉ በገዛ አገሩ እንደ ጠላት የሚታይበት ስርአት ላለፉት 28 አመታት ተግባራዊ ተደርጓል።
ይህ ስርአት በ 1983 ዓም ከተደረገዉ ህወሃት መራሹ የሽግግር ሂደት ጀምሮ አማራዉን ያገለለና አማራን እንደ ጠላት የሚቆጠር ሀገ መንግስት ቀራጾ የህዋሀትን ማኒፌስቶ ተግባራዊ አድርጓል። ህውሃት በጠራዉና በሰኔ 1983 ዓም በተካሄደው የሽግግር መንግስት ጉባኤ ሁሉም ብሄረሰቦች ከሞላጎደል ሲወከሉ አማራዉ ግን ሆነ ተብሎ እንዲገለል ተደርጓል። ሀወሃት ህገ መንግስት ወደ ማርቀቅና ማፅደቅ ሂደት ሲገባም አጠቃላይ ውይይቱና ቅኝቱ አማራውን በማግለልና በአማራ ጥላቻ ላይ ያተኮረ ነበር። የህገ መንግስቱ መግቢያ እንደሚስረዳዉ የህገ መንግስቱና የፌዴራል ስርአቱ ዋና ግብ ‘በታሪካችን የወረስነዉን የተዛባ ግንኙነት በማረም’ ላይ ያተኮረ ነዉ በሚል አማራዉ በቀደመዉ ዘምን የተለየ ጥቅም እንደነበረዉ በማስመሰል የተቀመጠው መርህ ህገ መንግስታዊ ስርአቱ አንድን ብሄር ለማትቃት የተዘጋጀ ሰነድ መሆኑን የሚያሳይ ነዉ።
ህገ መንግስቱ ከመውጣቱ በፊት የህዋሀት ማኒፌስቶን መሰረት በማድረግ አማራን ሊጎዳ በሚችል መልኩ አገሪቱ በዘር እንድትሸነሸን ከመደርጉም በላይ በህገ መንግስት የዘር ፓለቲካን በመፍቀድ አሁን ላለልበት መስቀለኛ መንገድ ዳርጎናል። በተለይ በመላ የአገሪቱ ክፍሎች ተበትኖ የሚኖረዉን የአማራ ማህበረሰብ በሚጎዳ መልኩ የተካለለው የክልሎች ድንበር አማራዉ በገዛ አገሩ ሁለተኛ ዜጋ ሆኖ እንዲኖር አድርጎታል። ክልሎቹ ሲካለሉ አማራው ወኪል ስላልነበረዉና ህወሃት አማራዉን ለመበቀል በውሰደው እርምጃ በአማራ እርስትነት የሚታወቁት አካባቢዎች እንዲውሰዱበት ተድርጓል። ባለፉት 28 አመታት አማራዉ ከተለያዩ የአገሪቱ ክልሎች እንዲባረርና እንዲሰደድ ተደርጓል። ህወሃት አማራዉን ከፖለቲካና ኤኮኖሚያዊ መዋቅሮች በማባረር የበይ ተመልካች አድርጎታል። የአማራ ክልል ተብሎ በተዋቀረዉ አካባቢ የልማት ስራዎች እንዳይሰሩ በማድረግ ህቡን የማቆርቆዝ ስራዎች ተሰርተዋል። የማራዉን ሃብት ህውሃት ያለከልካይ በመዝረፍ የትግራይ ክልልን ለማልማት ተጠቅሞበታል። ህውሃት ፖአቲካዉን፥ ደህንነትና መከከላከያዉን በመቆጣተር የአንድን ዘር የበላይነት ለማረጋገጥ ከፍተና ጥረት አድርጓል።
እንዲህ ስር የሰደደ መዋቅራዊ ችግር ባላበት አገር የጥላቻ ህግ ማዉጣት ያለዉን ችግር ምን ያህል ሊቀርፈዉ ይችላል የሚል ጥያቄ ያስነሳል። ኢትዮጵያ ዉስጥ ያለዉን ጥላቻና ግጭት ለማስወገድ የመጀመርያዉና ዋናው ህገ መንግስታዊ ስርአቱ ዘርን መሰረት አድርጎ የተዋቀረዉን በሌላ ዴሞክራሲያዊ ስርአት መተካት ነዉ። የስርአቱ መሰረታዊ መዋቅር እስካልተስተካከለ ድረስ እንደ ሰደድ እሳት እየተቀጣጣለ ያለዉ ጥላቻና ግጭት የጥላቻን ህግ በማዉጣት አይፈታም ። ስለዚህ መንግስት ቅድሚያ ሊሰጠዉ የሚገባዉ ይህ አንድን ብሄር በጠላትነት በመፈረጅ የተቋቋመዉን ህገ መንግስት ማሻሻልና የዜጎች መብት በእኩልነት የሚያስተናግድ የፖለቲካ ስርአት መፈጠር ላይ ነዉ።
4. የጥላቻ ንግግር ህግ ሃሳብን በነፃነት የመግለፅ መብት ላይ የሚያመታዉ ተፅዕኖ
ተግባራዊ እንዲሆን የታሰበዉ የጥላቻ ህግ በአገሪቱ ያለዉን ዉሱን ሃሳብን በነፃነት የመግለፅን መብት የበለጠ ሊያዳክመዉ እንደሚችል ስጋት አለ ። በ1987 ዓም ባወጣዉ ህገ መንግስት በአንቀፅ 29 ሃሳብን በነፃነት የመግለፅ መብት የተረጋጋጠ ቢሆንም ላለፉት 28 እንደታየዉ ሃሳብን የመግለፅ መብት ሙሉ በሙሉ ተገድቦ ቆይቷል። ህወሃት ስልጣን እንደያዘ በርካታ ጋዜጦችና መፅሄቶች በብዛት ይታታሙ ነበር። ነገር ግን መንግስት በህገ መንግስቱ ያስቀመጠዉን ሃሳብን በነፃነት የመግለፅ ነፃነት ወድ ጎን በመተዉ በትቂት አመታት ዉስጥ ሁሉንም የግል ጋዜጦች በመዝጋት በመንግስት ሚድያዎች ብቻ ፕሮፓጋንዳ እንዲያስተላልፉ ይደረግ ነበር ።
በተለይም የ1997 ምርጫ ተከትሎ የፖለቲካ ምህዳሩ ሙሉ በሙሉ በመዘጋቱ ዜጎች ሃሳባቸዉን መግለፅ አይደለም አገዛዙን ያልደገፉ ዜጎች ሰርቶ የመኖር መብታቸዉን ሳይቀር አደጋ ዉስጥ ወድቆ ነበር። መንግስት ሃሳብን በነፃነት የመግለፅ መብትን ለመገደብ በርካታ አፋኝ ህጎችን አዉጥቶ ተግባራዊ አድርጓል። ከነዚህ አፋኝ ህጎች ዋና ዋናዎቹ መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች ህግ፥ የፕሬስና የመረጃ ነፃነት መብትና የፀረ ሽብር ህግ ዋና ዋናዎቹ ናችዉ። በተለይም በ 2001 ዓም የወጣዉ የፀረ ሽብር ህግ ሃሳብን የመግለፅ መብትን ሙሉ በሙሉ በመገደብ የፖለቲካ ምህዳሩና ኢኮኖሚዉ ሙሉ በሙሉ በአገዛዙ ቁጥጥር ስር እንዲወድቅ ተደረገ። የሽብርተኝነትን ትርጉም አለአግባብ በመለጠጥ ህጋዊ የፖለቲካ ተቃዉሞንና ሃሳብን በነፃነት መግለፅን እንደ ሽብርተኛ በመቁጠር በርካታ የፖለቲካ መሪዎችና አባላት፥ ጋዜጠኞችና የመብት ታጋዮች ወህኒ እንዲወርዱ ተደርጓል። ዶ/ር አብይ ወደ ስልጣን ከመጡበት ጊዜ ጀምሮ ይህንን የፀረ ሽብር ህግ ለማሻሻል ሂደቶች ተጀምረዋል ቢባልም ሰኔ 15, 2011 ዓም የተከሰተዉን ግድያ ተከትሎ በርካታ የሰብአዊ መብት ተከራካሪዎች፥ ጋዜጦችና የፖለቲካ ፓርቲዎች በአለም አቀፍ ደረጃ በተወገዘዉ የፀረ ሽብር ህግ ክስ ቀርቦባቸዋል። ይህ አካሄድ ስርአቱን ለ ዴሞክራሲያዊ ስርአት ግንባታ ያለዉን ቁርጠኝነት ጥያቄ ዉስጥ አስገብቶታል። መንግስት ለስልጣኑ ያሰጉኛል ያላቸዉን የፖለቲካ ቡድኖች ለማጥቃት የፀረ ሽብር ህጉንና ሌሎች መደበኛ ህጎችን የሚጠቀም አገዛዝ ሊወጣ የታሰብዉን የጥላቻ ህግ ተቃዋሚዎችን ለማጥቃት ሊጠቀምበት እንደሚችል ያሳያል።
በተለይም ስልጣን ላይ ያለዉ መንግስት ሁሉንም የተቃዋሚ ሃይሎች በእኩል ዓይን እንደማይመለከት የሚያሳዩ ሁኔታዎች እየተበራከቱ መምጣታቸዉ የጥላቻ ህጉን የተወሰኑ የፖለቲካ ሃይሎችን ለይቶ ለማጥቃት እንደሚያዉለዉ አመላካች ነዉ። ይህንን ጥርጣሬ የሚያጠናክረዉ ባለፈዉ አንድ አመት የተካሄደዉ የፖለቲካ ለዉጥ አቅጣጫ የሌለዉ፥ ተቋዋማዊ ለዉጡ አስተማማኝ ያልሆነና የኦሮሞ አክራሪ ብሄርተኞች በተረኝነት ስም ፈላጭ ቆራጭ የሆኑበት ስርአት እየተፈጠረ መሆኑ ነዉ። ዶ/ር አብይ ኢትዮጵያዊነትንና አንድነትን ቢሰብኩም ዋና ዋና የስልጣን ቦታዎች በአንድ አካባቢ ሰዎች እየተያዘ እንደሆን በመታየቱ የህዝብ ቅቡልነታቸዉን በከፍተኛ ደረጃ እንዲቀንስ አድርጓል ። አሁንም ስልታዊ በሆነ ሁኔታ ዋና ዋና የፍትህ ተቋማት በኦዴፓ ሰዎችና የዶ/ር አብይ የቅርብ ወዳጆች የተያዙ መሆናቸዉ የጥላቻ ህጉን በመጠምዘዝ ለፈለጉት አላማ ሊያዉሉት የሚችሉበት እድል ከፍተኛ ነዉ።
ከዚህም በተጨማሪ የህወሃት ስርአት የሚመራባቸዉ ፀረ ዴሞክራሲያዊ አስተሳሰቦችና አደረጃጀቶች አሁንም ስራ ላይ ባሉበት ሁኔታ የጥላቻ ህጉ ቀደም ሲል የፀረ ሽብር ህጉ በመንግስት ላይ የሚደረጉትን ተቃዉሞዎች ለማዳፈን ጥቅም ላይ እንደዋለ አሁንም ለተመሳሳይ አላማ የማይዉልበት ምክንያት አይኖርም። ህወሃት ያቋቋማቸዉ ህገ መንግስታ ተቋማት ባልተለወጡበት ሁኔታና ተቃዋሚ ሃይሎችን ለማጥቃት ስራ ላይ እየዋሉ መሆኑ ሲታይ የጥላቻ ህጉን ተግባራዊ ማድረግ በተለየ መልኩ ስርአቱን የሚቃወሙ ሃይሎችን ለማጥቃት ስራ ላይ እንደሚዉል እርግጠኛ መሆን ይቻላል። ስለዚህ ይህ ህገ መንግስትና ጨቋኝ ተቋማት በተገቢዉ መልኩ ተሻሽለዉ በገለልተኛ ተቋማት ሳይተኩ ይህንን የጥላቻ ንግግር ህግ ተግባራዊ ማድረግ ላለፉት 28 አመታት የቀጠለዉን ፀረ ዴሞክራሲያዊ አገዛዝ በአዲስ መልኩ ለማክናወን የታሰብ አዲስ እቅድ ተደርጎ ሊታይ ይችላል።
5. ረቂቅ የጥላቻ ንግግር ህጉ ያሉበት ክፍተቶች
በጠቅላይ አቃቢ ህጉ አማካኝነት የተሰራጨዉ ረቂቅ የጥላቻ ንግግርና የሃሰተኛ መረጃ ስርጭትን ለመከላከል የወጣ አዋጅ ህጉን ለማወጅ ያስፈለገበትን ምክንያት ሲያስረዳ የጥላቻ ንግግርና የሃስተኛ መረጃ ስርጭት የሚያስከትሉት ግጭትና ጉዳት ለእኩልነት፣ለሰላም፣ ለዲሞክራሲና ለሕዝቦች አንድነት ትልቅ ጠንቅ በመሆኑ ይህንን ለማስቆም አላማ ያደረገ መሆኑን ያትታል። በረቂቅ ህጉ ላይ እንደተገለፀዉ የጥላቻ ንግግር ከፍተኛ ችግር እየፈጠረ እንደሆነ ምንም አጠያያቂ አይደለም። ነገር ግን የጥላቻ ንግግርን ለመቆጣጠር የተለየ ህግ ማዉጣት ያስፈልጋል ወይ የሚለዉ አንዱ ጥያቄ ነዉ። በኢትዮጵያ ህግ ዘርን፥ ሃይማኖትንና የፖለቲካ አመለካከት መሰረት ያደረገ ጥላቻ በወንጀል ህጉ የተከለከለ ነዉ። ህዝብን በማንኛዉም መንገድ ወደ ግጭት የሚመሩ ንግግሮችና ድርጊቶች በኢትዮጵያ ህግና ኢትዮጵያ በተቀበለቻቸዉ አለም አቀፍ ስምምነቶች የተከለከሉ ድርጊቶች ናችዉ። ምንም እንኳን በማህበራዊ የትስስር መድረኮች የሚተላለፉትን የጥላቻ ንግግሮች ለመቆጣጠር ራሱን የቻለ ህግ ማስፈለጉ ቢታወቅም መንግስት የጥላቻ ንግግርን መቆጣጠር ከፈለገ በስራ ላይ ያሉትን ህጎች ተጠቅሞ ህግና ስርአትን በማስከበር ረገድ ብዙ እርቀት መሄድ ይችል ነበር። ያሉትን የህግ ድንጋጌዎች ተጠቅሞ የጥላቻ ንግግርን ለማስወገድ ጥረት በማድረግ ተቋማትን ማጠናከርና አቅሙን መፈተሽ ሲገባዉ በቀጥታ አዲስ ህግ ወደ ማርቀቅ መሄዱ ምን ያህል ዉጤታማ ሊሆን ይእላል የሚል ጥያቄ ያስነሳል።
ሌላዉ ስጋት በረቂቅ ህጉ ዉስጥ የሚታዩት ክፍተቶች ናቸዉ። ረቂቅ ህጉ የጥላቻ ንግግርን ሲተረጉመዉ የሌላን ግለሰብን፤ የተወሰነ ቡድንን ወይም ማህበረሰብን ብሄርን፤ ሀይማኖትን፤ ቀለምን፤ ጾታን፤ አካል ጉዳተኝነትን፤ ዜግነትን፤ ስደተኝነትን፤ ቋንቋን፤ ዉጪያዊ ገጽታን፤ መሰረት በማድረግ ፣ሆነ ብሎ እኩይ አድርጎ የሚስል፤ የሚያንኳሰስ፤ የሚያስፈራራ፤ መድልዎ እንዲፈጸም፤ ወይም ጥቃት እንዲፈጸም የሚያነሳሳ ንግግር ነው በማለት ይገልፀዋል። ይህ አገላለፅ እጅግ ለትርጉም የተጋለጠና ቀደም ሲል የፀረ ሽብር ህጉን በመጠምዘዝ ሃሳብን በነፃነት መግለፅ መብትን ለመደፍጠጥ በቀላሉ ጥቅም ላይ መዋል የሚችልበትን እድል ሊፈጥር ይችላል። በአዋጁ’ እኩይ አድርጎ ማቅረብ፥ ማንኳሰስ’ ማለት ምን ማለት ነዉ? መንግስታዊ ስርአቱ ዘርን መሰረት አድርጎ በተዋቀረበት አገር አንዱ ብሄርን ማንኳሰስ ብርቅ ነው ወይ? አማራዉ 28 አመታት ሙሉ በመንግስት ደረጃ ነፍጠኛና ትምክህተኛ እየተባለ ሲንኳሰስ አልነበረም ወይ? አሁንስ እየተንኳሰሰ አይደለም ወይ? ይህን ስርአት እንዲቀትል እየፈለጉ ብሄርን የሚያንንኳስስ ንግግር እንዴት ህገ ወጥ ማድረግ ይቻላል? አንድን ግለሰብ ወይም ቡድን ’ እኩይ አድርጎ ማቅረብ፥ ወይም ማንኳሰስ’ ትችት ከማቅረብ በምን ይለያል? ማነዉ አንድን ድርጊት ’ እኩይ አድርጎ ማቅረብ ወይም ማንኳሰስ’ ነዉ ብሎ ብይን የሚሰጠዉ? ይህንን ስራ በብቃትና በገለልተኛነት ሊወስን የሚችል ፖሊስ፥ አቃቢ ህግ ወይም ፍርድ ቤት አለ ወይ? የሚሉ ጥያቄዎችን ያስነሳል። እንደተለመደዉ ስልጣኑን የተቆጣጠሩት መሪዎች ይህንን ህግ አምርረዉ የሚተቹዋቸውን ተቃዋሚዎች ለመምታት ሊጠቀሙበት የመቻላቸዉ እድል ከፍተኛ ነዉ።
በረቂቅ አዋጁ አንቀፅ 4 እና 5 የጥላቻ ንግግርንና የሃሳት መረጃን አስመልክቶ የተገለፀዉ የበለጠ ስጋትን የሚጭር ነዉ። አንቀፅ 4 የጥላቻ ንግግርን አስመልክቶ ሲያስቀምጥ ‘ሆነ ብሎ የሌላን ግለሰብን፤ የተወሰነ ቡድንን ወይም ማህበረሰብን ብሄርን፤ ሀይማኖትን፤ ቀለምን፤ ጾታን፤ አካል ጉዳተኝነትን፤ ዜግነትን፤ ስደተኝነትን፤ ቋንቋን፤ ዉጪያዊ ገጽታን፤ መሰረት በማድረግ ፣ እኩይ አድርጎ የሚስል፤ የሚያንኳስስ፤ የሚያስፈራራ፤ መድልዎ እንዲፈጸም፤ ወይም ጥቃት እንዲፈጸም የሚያነሳሳ ጥላቻ አዘል መልእክቶችን በመናገር፤ ፅሁፍ በመፃፍ፤ ምስል፤ ስእል፤ የኪነጥበብ እና እደ ጥበብ ውጤት፤ የድምጽ ቅጂ ወይም ቪድዮ በማተም፤ በማሳተም ወይም በማሰራጨት፤ መልእክቶችን ብሮድካስት ማድረግ ወይም በማህበራዊ ሚዲያ ማሰራጨት፤ ወይም በሌሎች ማናቸዉም መገናኛ መንገዶች ለህዝብ መልእክቱ እንዲደርስ ማድረግ ክልክል ነው ’ ይላል።
ከፍ ሲል እንደተገለፀዉ ይህም ክፍል እጅግ ሰፊና ለትርጉም በቃላሉ የተጋልጡ አባባሎችን የያዘ ነዉ። ብሄርን ፥ ሃይማኖትን፥ ፆታን፥ ቋንቋን መሰረት በማድረግ የሚቀርቡ ትችቶችን በቀላሉ በዚህ አንቀፅ መሰረት የጥላቻ ንግግሮች ናቸዉ በሚል ክስ ለማቅረብ ያስችላል። በተለይ ሁሉም ወገን በብሄር ተደራጅቶ ዳርና ዳር ቆሞ በሚሰዳደብበትና አገሪቱን ለሚንጣት የጎሳ ፖለቲካ ፖለቲካዊ መፍትሄ ባልተቀመጠበት በዚህ ወቅት እንዲህ አይነት ህግን በማዉጣት የጥላቻ ንግግር እቆጣጠራለሁ ማለት የማይቻልና ይልቁንም በቀላሉ መንግስትን የሚቃወሙትን ለማጥቃት ስራ ላይ ሊዉል የሚችል አንቀፅ ነዉ። በተለይም ይህ አንቀፅ በማህበራዊ ሚድያ የሚደረጉትን የሃሳብ ልዉዉጦች ለመቆጣጠር ያለመ እንደሆነ ግልፅ ነዉ።
አዋጁ በአንቀፅ 5 የሚደነግገዉ የሃሰተኛ መረጃ አንቀፅም ሃሳብን የመግለፅ መብትን የሚገድብ ነዉ። ይህ አንቀፅ ‘የፍሬ ነገር ወይም አንኳር ይዘቱ ውሸት መሆኑን እያወቀ ወይም ማወቅ ሲገባው፣ ሁከት ወይም ግጭት የማስነሳት፣ ወይም ጥቃት እንዲደርስ የማድረግ እድሉ ግልጽ በሆነ መልኩ ከፍ ያለ መረጃን ሆነ ብሎ በማንኛውም መንገድ ማሰራጨትና ለህዝብ እንዲደርስ ማድረግ የተከለከለ ነው’ ይላል ። መረጃ በፈጠን መንገድ በሚተላልፍበት በዚህ ዘመን አንድ ሰዉ የሚያሰራጨዉ መረጃ እዉነት አለዉ ብሎ ያመነበት ከሆነ ከማሰራጨት ሊገደብ አይገባም። ይህንን ሁኔታ ለመቆጣጠርም እጅግ አዳጋችም ነዉ። ማህበራዊ ሚድያዉ በአለም አቀፍ ደረጃ የሃሰት መረጃን በማሰራጨት የሚነቀፍ መሆኑ ቢታወቅም ችግሩ ግን የሚቀረፈዉ ግልፅ እና ተጠይቂነት ያለው የመንግስት አሰራርና ተቋማት በመገንባት ነዉ። የመንግስት አካላት ተጠያቂነት ሳይኖራቸዉና ራሱ መንግስት የሃሰት መረጃን በሚያሳራጭበት አገር ህዝብን ለማፈን የሚደረግ እንቅስቃሴ በቋፍ ያለዉን የአገሪቱን ሁኔታ የበለጠ ሊያባብሰው ይችላል ። የሰብአዊ መብት ተከራካሪ ድርጅት የሆነዉ የሂማን ራይትስ ዋች ( Human Rights Watch) በቅርቡ ለቂቅ የጥላቻ ንግግር ህጉን አስመልክቶ ባወጣዉ መግለጫ እንደገልችፀዉ ሊወጣ የታሰበው ህግ ሃሳብን በነፃነት የመግለፅ መብትን ሊጎዳ እንደሚችልና የጥላቻ ንግግር ለመቆጣጠር የተሻለዉ አካሄድ ህዝብን ማስተማርና መንግስት ግልፅነትንና ተጠያቂነትን ሲያዳብር መሆኑን አስገንዝቧል።
ማጠቃለያ
የጥላቻ ንግግር በኢትዮጵያ ዉስጥ ባለዉ የፖለቲካ ሁኔታ የተነሳ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተባባሰና ከፈተኛ ችግር እየፈጠረ ይገኛል። ከዚህ አንፃር መንግስት በስራ ላይ ያሉትንም ሆነ አዳዲስ ህጎችን በማዉጣት ችግሩን ለመቅረፍ ጥረት ቢያደርግ ክፋት የለዉም። ነገር ግን በአገራችን ሁኔታ የጥላቻ ንግግርን ለመከላከል ምን አይነት መፍትሄ ያስፈልጋል የሚለዉ ትልቅ ትኩረት የሚጠይቅ ጉዳይ ነዉ። በቅርቡ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የጥላቻ ንግግርን ለማስወገድ ባወጣዉ የድርጊት መርሃ ግብር መሰረታዊ መፍትሄዎችን ያስቀምጣል። የመንግስታቱ ድርጅት የድርጊት መርሃ ግብር የጥላቻ ንግግርን ለማስወገድ ትልቅ ትኩረት የሰጠዉ የጥላቻ ንግግር ዋናዉ መነሻ ምክንያትና የሚያባብሱትን ሁኔታዎችን መለየት ነዉ። ይህን ሁኔታ በአገራችን ሁኔታ ስናየዉ አሁን በከፈተኛ ደረጃ እየተስፋፋ ላለዉ የጥላቻ ንግግር ስር መሰረቱ አገሪቱ ባልፉት 28 አመታት የተከተለችዉ ጎሳን መሰረት ያደረገ የፖለቲካ ስርአት መሁኑን ብዙዎች ይስማሙበታል። ይህ ስርአት የብሄር መብቶችን ለማከበር ነዉ የሚል ትርጉም ቢሰጠዉም መነሻዉና መድረሻዉ ግን ጥላቻ ነዉ። ይህንን ህገ መንግስት ተሸክመን የጥላቻ ንግግርን ዋጅ በማዉጣት እናሶግደዋለ ማለት የዋህነት ነዉ። ስለዚህ የመንግስት ትልቁ ትኩረት ሊሆን የሚገባዉ ይህን ጥላቻን የሚፈለፍል ስርአት ዜጎች በእኩልነት በሚኖሩበት ስርአት መቀየር ካልተቻለ ጥላቻ የማህበረሰቡ ጠንቅ ሆኖ መቀጠሉ የማይቀር ነገር ነዉ።
የመንግስታቱ ድርጅት የጥላቻ ንግግርን ለማስወገድ ሌላዉ ትኩረት ያደረገባቸዉ ጉዳዮች የጥላቻ ንግግር ሰለባዎችን መርዳት፥ የጥላቻ ንግግር የሚያራምዱትን እንዲቀራረቡ ማድረግ፥ ቴክኖሎጂን በመጠቀም ማስተማርና ሁሉንም ተጠቃሚ የሚያደርግ አሳታፊ አሰራር ማስፈን ናቸዉ። ከዚህ ዝርዝር የጥላቻ ህግን መጠቀም የመጨረሻው አማራጭ እንደሆነ እንረዳለን። አገራችንን ከጥላቻና መለያየት ለማዳን ዋናዉ መንገድ ፖለቲካዊና ማህበራዊ መፍትሄዎች ላይ ማተኮር ነዉ። ብሄራዊ እርቅና መግባባት፥ ህብረተሰቡም ማስተማር፥ መንግስታዊ ተቋማት ከአድልዎ ነፃ ማደረግ፥ ግልፅነትና ተጠያቂነት ያለበት ስርአት መገንባት የጥላቻ ንግግርን ለማስወገድ ትልቅ ፋይዳ ይኖራቸዋል። የጣላቻ ንግግር ህግ ማዉጣት በራሱ ችግር ባይሆንም ውስብስብ ከሆነው የአገራችን ሁኔታ አንፃር ይህን ህግ ተግባራዊ በማድረግ ችግሩን ለመፍታት መሞከር ትልቅ ችግር ሊፈጥር ስለሚችል ጥንቃቄ ያስፈልገዋል።

Reference
[1] ይህን ጥናት  በአማራ ባለሙያዎች ማህበር (አምባ) ድጋፍ የተሰራ ነዉ።
[2] Ethiopia: 3 million internally displaced in escalating humanitarian crisis, https://www.euronews.com/2019/01/31/ethiopia-3-million-internally-displaced-in-escalating-humanitarian-crisis
[3] In era of reform, Ethiopia still reverts to old tactics to censor press, https://cpj.org/blog/2019/07/ethiopia-coup-internet-censored-blocked-jailed-journalists.php


[4] Hate Speech on Social Media: Global Comparisons, https://www.cfr.org/backgrounder/hate-speech-social-media-global-comparisons

wanted officials