Which one you first choose? በቅድሚያ የሚፈልጉት

Wednesday, March 4, 2020

ቀነኒሳ የሞ ፋራህን የግማሽ ማራቶን ክብረ-ወሰን ሰበረ


በለንደን ከተማ በተካሄደው የቫይታሊቲ ቢግ ግማሽ ማራቶን፤ ቀነኒሳ በቀለ ክብረ-ወሰን በመስበር አሸንፏል።
የ5 ሺህ እና 10 ሺህ ሜትር ውድድሮች የዓለም ክብረ ወሰን ባለቤቱ ቀነኒሳ በዚህ ውድድር ሲሳተፍ የመጀመሪያው ነው።
1:00:22 በሆነ ሰዓት የገባው ቀነኒሳ፤ በእንግሊዛዊው ሯጭ ሞ ፋራህ የተያዘውን የቫይታሊቲ ቢግ ግማሽ ማራቶን ክብረ-ወሰን ሰብሯል።
ከቀነኒሳ ጋር ይፋጠጣል ተብሎ የተጠበቀው ሞ ፋራህ ከጥቂት ቀናት በፊት በህመም ምክንያት እንዳይማሰተፍ አሳውቆ ነበር።
x
© The Vitality Big Half
የቢቢሲ አማርኛ

No comments:

Post a Comment

wanted officials