ዋሽንግተን ዲሲ —
ከሰሞኑ ከመላው ኢትዮጵያ የተላኩ የቡና ናሙናዎች አዲስ አበባ ላይ መዓዛቸው ሲለካ፣ ጣዕማቸው ሲወዳደር ሰንብቷል።ይህ Cup of excellence የተሰኘ የላቀ ጣዕም ያላቸውን የቡና ዐይነቶች የማወዳደር መርሃ-ግብር ልዩ ጣዕም ያላቸውን ቡናዎች የማስተዋወቅ፣ የተሻለ ገበያ ዕድል እንዲያገኙ ማገዝ ዓላማው እንደሆነ አስተባባሪው ተቋም ይፋ አድርጓል።
ሀብታሙ ስዩም ውድድሩን የማስተባበር ኃላፊነት ከተሰጣት ቅድስት ሙሉጌታ ጋር ያደረገውን ምጥን ቆይታ ያዳምጡ።
*ቃለ-ምልልሱ ከተደረገ በኋላ በውድድሩ ያሸነፉ የቡና ናሙናዎች ዝርዝር ይፋ ተደርጓል።በዚህም መሰረት:-መቀመጫውን በኦሮሚያ ክልል ጉጂ ዞን፣ ቡቃ ሳይሳ ቀበሌ ያደረገው -ቡቃ ሳይሳ የቡና አምራች ድርጅት ያቀረበው የቡና ናሙና የአንደኛ ደረጃን አግኝቷል።የምዕራብ ጉጂ ስቄ ቦኮሳ ቀበሌው ታምራት ኢደና የቀረቡት የቡና ናሙና የሁለተኛ ደረጃን እንዲሁም የምዕራብ ጉጂ ሃሮዋቹ ቀበሌው ገሬ ዋሌ ያቀረቡት ቡና ሶስተኛ ደረጃን ማግኘታቸውን አወዳዳሪው አካል በማህበራዊ ገጹ ይፋ አድርጓል።
አሸናፊው ቡና በበይነ መረብ ላይ በሚደረግ የጨረታ ስነስርዓት ዓለም አቀፍ ገበያተኞች እንዲፎካከሩበት እንደሚደረግ ይጠበቃል።https://amharic.voanews.com/pp/5315087/ppt0.html
No comments:
Post a Comment