ዋሽንግተን ዲሲ —
በዮናይትድ ስቴትስ ውጭ ጉዳይ መስሪያቤት ፊት ለፊት ትውልደ ኢትዮጵያዊያን ሰለማዊ ሰልፍ አድርገዋል።ሰላማዊ ሰልፍ አድራጊዎቹ ዮናይትድ ስቴትስ የህዳሴ ግደብ ድርድርን በተመለከተ ለግብጽ ያደላ አቋም ይዛለች ፣ኢትዮጵያ ላይም ጫና እያሳደረች ነው ሲሉ ወቅሰዋል።
የኢትዮጵያ መንግስት የሀገሪቱን ጥቅም አሳልፎ የሚሰጥ ድርድር እንዳይፈርም፣ የእስከአሁኑን ድርድር ይዘት በግልጽ እንዲያሳውቅም ጠይቀዋል።
ሰልፉን የተከታተለው ሀብታሙ ስዩም ቀጣዩን ዘገባ አሰናድቷል። https://amharic.voanews.com
No comments:
Post a Comment