Which one you first choose? በቅድሚያ የሚፈልጉት

Wednesday, March 4, 2020

አጤ ምኒሊክ የብሔር/ብሔረሰቦች ትልቅ ባለውለታ – አንድነት ይልቃል


ማስረጃችንን የዶክተር ነገሶ ጊዳዳን በወለጋ ሰዮ ኦሮሞ ጎሣ ታሪክ ላይ የተደረገ የሶስተኛ ዲግሪ ማሟያ ጥናት ዋቢ እናድርግ። ” የኦሮሞ ሕዝብ ታሪክ ” ፣ ምእራፍ ሦስት፣ ገጽ 97 – 145፣ 2008 ዓ.ም። የሚከተለው በኦሮሞ መስፋፋት ወቅት ሕልውናቸውን ያጡ ወይም ተጨፍልቀው የተዋጡ እና oromized የሆኑ ሕዝቦች ዝርዝር ነው። የደብተራ ታሪክ ነው ተብሎ ማምለጥ የማይቻልበት የኦሮሞ ብሔርተኛና የታሪክ ምሁር የምርምር ውጤት ነው። በኦሮሞ ተውፊትም ውስጥ የሚገኝ ነው። ነጋሶ እራሳቸውም ከጠፋው የዳሞት ሕዝብ ዝርያ እንደሚመዘዙ በማስረጃ አስደግፈው ተውፊት ጠቅሰው ጽፈዋል። ራስ ጎበና ዳጬም ከጋንቃ ሕዝብ ዝርያ እንደሆኑ ምስጢር ነግረውናል። ጎበና ከምኒሊክ ጋር ለሕዝብ ኅልውና ነው የታገሉት ወደሚለው መደምደሚያ ለመድረስ ትንሽ ማስረጃ ያስፈልገናል። ግን አዝማሚያው ይኸው ነው። ዝርዝሮቹ፦
1.ሙጩጮ፣
2.ገብቶ፣
3.መጮ(መጫ?)፣
3.ጉጂ፣
4.ኢናንጎ፣
5.ገራዶ፣
6.  ቦጢ፣
7. አጋዲ፣
8.ካዛ
9.ያበታ
10. ኢልመጉዛዊት
11. ዳሞታ፣
12.ወረጎ፣
13.ጋንቃ፣
14.ከንቺ. (በካንቺ ወንዝ አቅራቢያ እና በኮንቺ አካባቢ በተለምዶ “አማረ” ተብለው የሚጠሩ አሮሚፋ ተናጋሪ ጎሳዎች ይኖራሉ)፣
15.ማኦ ቡሳሴ
16. ካቾ፣
17.ጌራቾ፣
18.ሐቾ፣
19.ሒሚሮ
20.አንችፎ፣
21.ጌሬቾ
22.ኬዌጉ (ኮጎ)
23. ክዋማ (ኮሞ)
24.መዥንገር
25.ጋፋት
26.ማያ
27.ሐርላ
እነዚህ በጦርነት ተጨፍጭፈው፣ ተፈናቅለው እና ተሰድደው የተረፉ ምርኮኞች  ሙሉ በሙሉ በሜዲቻ በሞጋሣ በጉዲፈቻ በደለታ በረኮ ወደ ኦሮሞነት የተቀየሩ ናቸው። እንደ መዠንገር አይነቶች ዛሬም ተርፈው የም ተብለው አሉ። አማረ የተባሉት አማሮች ናቸው። ሲዳማ ከምባታ እና ሐዲያ በብዛት በባሌ በአርሲ በከረዩ በኢሉባቡር ወዘተ ተውጠው ኦሮሞ ሆነዋል። ከሌላ ብሔር የተለወጡት ሲዳም ጀላ ወይም በጥቅሉ ሲዳመ ተብለው እስከዛሬ ይጠራሉ።
ሶማሌዎች  በሐረርጌ በብዛት ተቀይረዋል። ብዙ ቦታዎች በጠፉ ብሔረሰቦች መጠራታቸው እነዚያን አካባቢዎች በመስፋፋቱ ወቅት የሠፈሩበት እነርሱ መሆናቸውን አመላካች ሊሆን ይችላል። ለምሳሌ ማያ በምሥራቅ ሸዋ ይኖሩ የነበሩ እውቅ ቀስተኞች ነበሩ። ከረዩ አካባቢ። ከተቀየሩ በኋላ ወደ ምሥራቅ ኢትዮጵያ ተንቀሳቅሰው ሐሮማያ የሠፈሩት እነርሱ ሳይሆኑ አይቀሩም። ማያ ጉዶ፣ ማያ ቀሎ ወዘተ የተባሉ ሥፍራዎችም ይታወቃሉ።
አንድምታ

ይህን ያህል ማስረጃ ዶ/ር ነጋሶ ከፃፉት “የኦሮሞ ሕዝብ ታሪክ” መጽሐፍ ካቀረብን እስቲ በኦሮሞ እና ትግራይ ጠባብ ልሂቃን የተጠመዱት አፄ ምኒሊክ ጨፍልቀው ያጠፉት አንድ ብሔረሰብ እና ቋንቋ በማያወላዳ ማስረጃ ይቅረብ። የለም። ዛሬ 80+ ብሔረሰብ ኅልው ሆኖ መገኘቱ የእርሳቸው ውለታ ነው።
የኦሮሞ ገዳ በአደረጃጀቱ ወደር የማይገኝለት ስለነበር ሌሎችን እየጨፈለቀ እና እየዋጠ ከመቀጠል ማንም ሀይል አይገታውም ነበር፣ ምኒሊክ ባይደርሱ ኖሮ። የኦሮሞ ጠባብ ልሂቃን ምኒሊክ በኦሮሞ ጨፍላቂ እንቅስቃሴ ላይ ደንቃራ እንደሆኑ ስለሚያውቁ ይኸው እስከዛሬ ጠምደው ይዘዋቸዋል። ይህ የዐድዋ በዓል ሲዘከር ምኒሊክ በአገር ውስጥ ጨፍላቂዎች እና በአውሮፓ ቅኝ ገዢዎች ላይ ያስመዘገቡትን ድሎች በማሰብ ሊሆን ይገባል።

TRENDING ARTICLES

No comments:

Post a Comment

wanted officials