Which one you first choose? በቅድሚያ የሚፈልጉት

Saturday, October 14, 2017

በኦሮሚያ ክልል ሶዳ ከተማ ዛሬ የመከላከያ ሰራዊት በወሰደው ርምጃ ስድስት ሰዎች ተገደሉ


 በኦሮሚያ ክልል ቦረና ዞን ድሬ ወረዳ ሶዳ ከተማ ዛሬ የመከላከያ ሰራዊት በወሰደው ርምጃ ስድስት ሰዎች ተገደሉ።
ከ20 በላይ ሰዎች መቁሰላቸውም ታውቋል።
መሳሪያ ጭነው ወደሶማሌ ክልል እያጓጓዙ ነው ተብለው በነዋሪው መንገድ የተዘጋባቸው ስምንት የመከላከያ ተሽከርካሪዎች ላይ የነበሩ የመከላከያ ሰራዊት አባላት ህዝቡ ላይ ተኩስ መክፈታቸውንም ከአካባቢው የደረሰን መረጃ አመልክቷል።
ማምሻውን በሶዳ ሜጋ ያቤሎ፣ ዱብሉቅና ሞያሌ መንገዶች መዘጋታቸው የተገለጸ ሲሆን መሳሪያ ጭነዋል የተባሉት የመከላከያ ተሽከርካሪዎችም ከሶዳ ከተማ እስከምሽት ድረስ መውጣት እንዳልቻሉ ታውቋል።
በሶማሌና ኦሮሚያ ክልሎች የተነሳው ግጭት ከተከሰተባቸው አከባቢዎች አንዱ በሆነው የቦረና ዞን ዳግም ውጥረት እንዲነግስ ያደረገው የዛሬው ግድያ መነሻው መሳሪያ ጭነዋል የተባሉት የመከላከያ ተሽከርካሪዎች ናቸው።
መነሻቸው ከመሃል ሀገር እንደሆነ የሚገመተውና በፒክ አፕ መኪና ፊት መሪነት ወደሶማሌ ክልል አቅጣጫ እየገሰገሱ የነበሩት ስምንት የመከላከያ ከባድ ተሽከርካሪዎች ዲሬ ወረዳ ሶዳ ከተማ ሲደርሱ በህዝብ ተቃውሞ ጉዟቸውን መቀጠል አልቻሉም።
ነዋሪዎች እንደሚሉት የጫኑት መሳሪያ በመሆኑ ህዝቡ ሊያሳልፋቸው አልፈቀደም። መንገድ ዘግቶ አቆማቸው።
እዚያው በግጭቱ ስፍራ ከተገደሉት በተጨማሪ ሆስፒታል ከተወሰዱት አንድ ሰው ተጨምሮ በድምሩ ስድስት ሰዎች በመከላከያ ሰራዊት ተኩስ መገደላቸውን ነው ለማወቅ የተቻለው።
ነዋሪው እንደሚለው ተሽከርካሪዎቹ የጫኑት የጦር መሳሪያ ነው። ይዘው የሚጓዙት ደግሞ ለሶማሌ ክልል ልዩ ሃይል ነው።
የምንገደልበት መሳሪያ በአጠገባችን ሲያልፍ ዝም ብለን ማየት አንችልም ያሉት የሶዳ ከተማ ነዋሪዎች ከያሉበት ተጠራርተው መንገድ በመዝጋት ያቆሟቸው ሲሆን ከግድያውም በኋላ መሳሪያ የጫኑት ተሽከርካሪዎች እስከምሽት ድረስ ማለፍ እንዳልቻሉ መረጃዎች ያመለክታሉ። አሁንም መከላከያና ህዝቡ ተፋጦ እንዳለ ይነገራል።
መከላከያ ሰራዊት በወሰደው እርምጃ ከ20 በላይ ሰዎች ቆስለዋል።
የኦሮሚያ ፖሊስ ከሀገር ሽማግሌዎች ጋር በመሆን ድርድር የተጀመረ ሲሆን በአብዛኛው የቦረና ዞን አካባቢ የህዝብ ቁጣ ቀስቅሷል።
ዱብሉቅ፣ ሞያሌ፣ ያቤሎ፣ ሜጋና በሌሎች አከባቢዎችም መንገዶች የተዘጉ ሲሆን መሳሪያ ጭነዋል የተባሉት ተሽከርካሪዎች እንዳያልፉ በየቦታው መንገዶች በድንጋይና በትላልቅ ዛፎች መዘጋታቸውንም የደረሰን መረጃ ያመለክታል።

ከኦሮሚያ ወደ አማራ ክልል የተንቀሳቀሱት ወጣቶች የእምቦጭ አረሙን የመንቀል ዘመቻ ጀመሩ

Image may contain: 1 person, crowd and outdoor

(ኢሳት ዜና–ጥቅምት 3/2010)
የአባይ ዋና ምንጭ በሆነው ጣና ሐይቅ ላይ እምቦጭ በተባለው አረም እየደረሰ ያለውን ጉዳት ለመከላከል ከኦሮሚያ ክልል ወደ አማራ ክልል የተንቀሳቀሱት ወጣቶች አረሙን የመንቀል ዘመቻ መጀመራቸው ታወቀ።
ጣና ኬኛ ወይንም ጣና የኛ ነው በሚል መሪ ቃል ወደ ጎጃም የተንቀሳቀሱት ወጣቶች በየስፍራው በተለይም በደብረማርቆስ ከተማ ደማቅ አቀባበል ተደርጎላቸዋል።
በበርካታ አውቶቡሶች ተሳፍረው ጣና ሃይቅን ከአረም ለመታደግ በሚደረገው ዘመቻ ተሳታፊ ለመሆን የተንቀሳቀሱት ወጣቶች ከሳምንቱ አጋማሽ ጀምሮ አረሙን በመንቀል ጣናን ለመታደግ በመንቀሳቀስ ላይ መሆናቸውን በምስል ተደግፈው ከተሰራጩት መረጃዎች መመልከት ተችሏል።
ይህን የኦሮሚያ ክልል ወጣቶችን እንቅስቃሴ ብዙዎች በአድናቆት እየጠቀሱ በማህበራዊ መድረኮች አስተያየታቸውን እየሰጡ ይገኛሉ።
በ2008 ሐምሌና ነሐሴ መንግስት በኦሮሚያና በአማራ ክልል ተወላጆች ላይ ያካሄደውን ግድያ ተከትሎ በጎንደርና በአዳማ የሁለቱ ክልል ወጣቶች አንዱ ለሌላው የሰጠውን አጋርነትም በማስታወስ ላይ ይገኛሉ።
በኢትዮጵያ ትልቁ ሃይቅ የሆነውና የአባይ ወንዝ አብይ ምንጭ እንደሆነ የሚታወቀው ጣና እምቦጭ በተባለው አረም በከፍተኛ ደረጃ መወረሩ ይታወሳል።
ይህም በመንግስት በኩል በቂ ትኩረት አላገኘም በሚል ተቃውሞዎች እየቀረቡ ሲሆን በአደጋው መጠን ችግሩን ለመፍታት የሚደረጉ ጥረቶችም አልታዩም።
84 ኪሎ ሜትር ርዝመት እንዲሁም 66 ኪሎ ሜትር ያህል የጎን ስፋት ባለው የኢትዮጵያ ትልቁ ሃይቅ ጣና ላይ በእምቦጭ አረም እየደረሰ ያለው ጉዳት ከሀይቁ ባሻገር በአባይ ውሃ ፍሰት ላይም ተጽእኖው የጎላ እንደሚሆን ባለሙያዎች ያሳስባሉ።
ይህ በእንዲህ እንዳለም የጣና ሃይቅን የወረረውን እምቦጭ አረምን ለመከላከል ወደ አማራ ክልል የተንቀሳቀሱት የኦሮሚያ ክልል ወጣቶች በደብረማርቆስ ከተማ የጠበቃቸው ደማቅ አቀባበል ወጣቶቹ በባህር ዳር እንዳያልፉ ምክንያት መሆኑ ተመልክቷል።
የባህር ዳር ከተማ ነዋሪዎችም የድምጽ መሳሪያዎችን ጭምር ይዘው ወደ አደባባይ በመውጣት የኦሮሚያ ክልል ወጣቶችን ለመቀበል ከተዘጋጁ በኋላ በባህርዳር እንዳያልፉ የተከለከሉበት ምክንያት ግልጽ አልሆነም።
ተልኳቸውን ጨርሰው ሲመለሱም ባህርዳር በምሽት እንዲገቡና በማለዳ እንዲወጡ ፕሮግራም መደረጉም እያነጋገረ ይገኛል።

ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ እስራቱን ቢጨርስም ከወህኒ ቤት አለመፈታቱ ታወቀ

Image may contain: 1 person, smiling, text

 የሶስት አመታት እስራት ተፈርዶበት ከ2007 ጀምሮ በወህኒ ቤት የሚገኘው ጋዜጠኛው ተመስገን ደሳለኝ እስራቱን ቢጨርስም ከወህኒ ቤት አለመፈታቱ ታወቀ።
ጋዜጠኛ ተመስገን የሶስት አመታት እስራቱን ጥቅምት 3/2010 ሙሉ በሙሉ መጨረሱንም ማረጋገጥ ተችሏል።
በፍትህ ጋዜጣና በተለያዩ የፕሬስ ውጤቶች ላይ በቀረበው ጽሁፍ አመጽ በመቀስቀስ ተወንጅሎ የሶስት አመታት እስራት ተፈርዶበት በመስከረም 2007 ቃሊቲ ወህኒ የወረደው ተመስገን ደሳለኝ ያለፉትን ሶስት አመታት በይበልጥ ያሳለፈው በዝዋይ ወህኒ ቤት እንደሆነም ተመልክቷል።
በሀገሪቱ ህግ መሰረት እስረኛው ከተፈረደበት ሁለትሶስተኛውን ካጠናቀቀና በወህኒ ቤት ውስጥ የተለየ ነገር ካልፈጸመ አንድሶስተኛው የእስር ጊዜው ተነስቶለት በአመክሮ እንደሚፈታ ይታወቃል።
ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ ይህንንም መብት በመነፈጉ ለተጨማሪ አንድ አመት ወህኒ ቤት ውስጥ ቆይቷል።
የአመክሮ መብቱ ለምን እንደተነፈገው ግን እንዳልተገለጸለት መረዳት ተችሏል።
ያለበቂ ምክንያት ለተጨማሪ አንድ አመት በወህኒ መቆየቱ የተገለጸው ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ በፍርድ ቤቱ ውሳኔ መሰረት የሶስት አመታት እስራቱን ሙሉ በሙሉ ጥቅምት 3/2010 ላይ ቢያጠናቅቅም ይህ ዘገባ እስከተጠናቀረበት አርብ ምሽት ድረስ ከእስር አልተለቀቀም።

Friday, October 13, 2017

ኤች አር 128 በኮንግረስ ድምጽ እንዳይሰጥበት ያዘገየው በአሜሪካ ምክር ቤት የመከላከያ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ነው ተባለ


(ኢሳት ዜና –ጥቅምት 2/2010) በኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች እንዲከበሩና ሁሉን አቀፍ አስተዳደር እንዲኖር ግፊት የሚያደርገው ኤች አር 128 በኮንግረስ ድምጽ እንዳይሰጥበት ያዘገየው በአሜሪካ ምክር ቤት የመከላከያ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ መሆኑ ተጠቆመ።
የቋሚ ኮሚቴው ስብሳቢ ማክ ቶርንቨሪ በምክር ቤቱ አብላጫ ድምጽ ላለው ሪፐብሊካን ፓርቲ መሪ ኬቨን ማካርቲ በረቂቅ ሕጉ ላይ የ30 ቀን ጊዜ እንዲሰጣቸው በመጠየቃቸው የድምጽ አሰጣጥ ስነስርአቱ እንደዘገየ ጉዳዩን በቅርበት የሚከታተለው የኢትዮጵያ አድቮኬሲ ኔትዎርክ ስብሳቢ ዶክተር አርአያ አምሳሉ ገልጸዋል።
እንደ ዶክተር አርአያ ገለጻ የመከላከያ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ኤች አር 128 እንዲዘገይ የፈለገው በኢትዮጵያ ያለው አገዛዝ ረቂቅ ሕጉ ከጸደቀ በጸረ ሽብር ጉዳይ ላይ ከአሜሪካ ጋር ያለውን ትብብር እንደሚያቆም በመግለጹ ነው።
ይህም ቢሆን ግን በአሜሪካ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን አሁንም ወደ ኮንግረስ አባላት ስልክ በመደወል ረቂቅ ሕጉ እንዲጸድቅ ግፊታቸውን ይበልጥ እንዲያጠናክሩ ዶክተር አርአያ ጥሪ አቅርበዋል።
ኤች አር 128 በኢትዮጵያ የተፈጸመው አጠቃላይ ግድያና እስር በገለልተኛ አካል ተጣርቶ በፈጻሚዎች ላይ ተጠያቂነት እንዲመጣ የሚያስገድድ የውሳኔ ሀሳብ ነው።
በኮንግረስ ክሪስ ስሚዝ ስፖንሰር አድራጊነት የተረቀቀው ኤች አር 128 ከአሜሪካ የተወካዮች ምክር ቤት አባላት ከ66 በላይ የሚሆኑት ድጋፋቸውን ሰጥተውበታል።
ረቂቅ የውሳኔ ሀሳቡም በምክር ቤቱ የውጭ ጉዳይ ኮሚቴ በሙሉ ድምጽ ጸድቆ ከ4 መቶ በላይ አባላት ባሉት ኮንግረስ ሊጸድቅ ቀነ ቀጠሮ ከተያዘለት በኋላ ድንገት እንዲዘገይ ተደርጓል።
ይህንኑ ረቂቅ ህግ እንዲጸድቅ በዋና ደጋፊነት ከሚያስተባብሩት መካከል ዋነኛው የኮሎራዶው ኮንግረስ ማን ማይክ ኮፍማን የድምጽ አሰጣጥ ስነስርአቱ የዘገየው በአሜሪካ የኢትዮጵያ አምባሳደር ሕጉ የሚጸድቅ ከሆነ በጸረ ሽብር ዘመቻው ካሁን በኋላ አንተባበርም ሲሉ በመዛታቸው መሆኑን ከዚህ ቀደም ገልጸው ነበር።
ጉዳዩን በቅርበት እየተከታተለና ሕጉ እንዲጸድቅ ዘመቻውን እያስተባበረ ያለው የኢትዮጵያ አድቮኬሲ ኔትወርክ ሰብሳቢ ዶክተር አርአያ አምሳሉ በበኩላቸው በአሜሪካ ምክር ቤት የመከላከያ ቋሚ ኮሚቴ ሊቀመንበር ማክ ቶርንቨሪ የአምባሳደሩን ዛቻ መነሻ በማድረግ የ30 ቀን ጊዜ እንዲሰጣቸው መጠየቃቸውን ነው የተናገሩት።
በኢትዮጵያ ያለው አገዛዝ ይህን ካደረገ በኋላ ረቂቅ ሕጉ እንዳይጸድቅ በውጭ ባሉ ደጋፊዎች አማካኝነት ተቃውሞ የሚል ዘመቻ መጀመሩንም ዶክተር አራአያ አምሳሉ ይናገራሉ።
ይህም ደግፍ ከሚለው የኢትዮጵያውያን ዘመቻ በመኮረጅ እየተደረገ ያለ ተቃራኒ እንቅስቃሴ መሆኑን ነው የገለጹት።
በሕወሃት ኢህአዴግ የሚመራው አገዛዝ ረቂቅ ሕጉ እንዳይጸድቅ እየተሯሯጠና ከፍተኛ ገንዘብ በማውጣት ወትዋቾችን እስከመቅጠር የደረሰው ኤች አር 128 በኢትዮጵያ ባለስልጣናት ላይ የጉዞ እቀባና የገንዘብ እገዳ እንዲጣል የሚጠይቅ አንቀጽ ስላለበት ነው ብለዋል።
እናም ኢትዮጵያውያን ኤች አር 128 የተባለው ረቂቅ የውሳኔ ሀሳብ በኮንግረሱ ከጸደቀ በአገዛዙ ላይ ከፍተኛ በትር ስለሚያሳርፍ ግፊታቸውን አጠናክረው መንቀሳቀስ እንዳለባቸው ዶክተር አርአያ አምሳሉ ጥሪ አቅርበዋል።
እንደ ዶክተር አርአያ ገለጻ ኢትዮጵያውያን ምን ማድረግ እንዳለባቸው ለማወቅና በኮንግረስ አባላት ላይ የሚደረገውን ግፊት ለማጠናከር ኤች አር 128.org ከተባለው ድረ ገጽ መረጃውን ማግኘት ይችላሉ።

Thursday, October 12, 2017

የኢትዮጵያ አየር መንገድ አውሮፕላን አቅጣጫ ቀይሮ ካናዳ ሀሊፋክስ ስታንፊልድ አውሮፕላን ማረፊያ ለማረፍ ተገደደ


 ከአዲስ አበባ ከተማ ተነስቶ ወደ ዋሽንግተን ዲሲ ይበር የነበረ ቦይንግ 777 የበረራ ቁጥር 500 የኢትዮጵያ አየር መንገድ አውሮፕላን አቅጣጫ ቀይሮ ካናዳ ሀሊፋክስ ስታንፊልድ አውሮፕላን ማረፊያ ለማረፍ ተገደደ።
የአየር መንገዱ ምንጮች እንደገለጹት ዋሽንግተን ዲሲ ጥቅምት 1/2010 ከጠዋቱ 2 ሰአት ከ40 ደቂቃ መድረስ የነበረበት አውሮፕላን እስከ ከሰአት 7 ሰአት ከ22 ድረስ መዘግየቱም ታውቋል።
ማክሰኞ ምሽት ከአዲስ አበባ ቦሌ አለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ የተነሳው የበረራ ቁጥር 500 የሆነው የኢትዮጵያ አየር መንገድ ቦይንግ 777 አውሮፕላን ደብሊን አየርላንድ ነዳጅ ለመሙላት ያደረገው ጉዞ በተያዘው ፕሮግራም መሰረት የተካሄደ ነበር።
ነገር ግን ከደብሊን ወደ ዋሽንግተን ዲሲ ሲጓዝ አንድ መንገደኛ አውሮፕላኑ ወስጥ ሕይወታቸው በማለፉ ካናዳ ሀሊፋክስ ስታንፊልድ አውሮፕላን ማረፊያ በካናዳ ሰአት አቆጣጠር ከጠዋቱ 3 ሰአት ከ55 ደቂቃ አርፏል።
እስከ ቀትር 6 ሰአት ከ15 በዚያው አውሮፕላን ማረፊያ ቆይታ አድርጎ ከ1 ሰአት 5 ደቂቃ በረራ በኋላ ወደ አሜሪካ ዋሽንግተን ዲሲ መድረሱ ታውቋል።
የበረራ ቁጥር 500 የሆነው የኢትዮጵያ አየር መንገድ የበረራ መስመሩን ለመቀየር ምክንያት የሆነውና ካናዳ ለማረፍ የተገደደው አንዲት ናይጄሪያዊት ተሳፋሪ በመታመማቸውና በኋላም ህይወታቸው በማለፉ እንደሆነ ታውቋል።

በኦሮሚያ ክልል የተቀሰቀሰው ተቃውሞ ለሶስተኛ ቀን ቀጥሎ መዋሉ ተሰማ


 በኦሮሚያ ክልል የተቀሰቀሰው ተቃውሞ ለሶስተኛ ቀን ቀጥሎ መዋሉ ተሰማ።
በተለይም በምዕራብና ምስራቅ ወለጋ ህዝባዊ ተቃውሞ በበርካታ ከተሞች የተካሄደ ሲሆን በቡሌ ሆራ ዩኒቨርስቲ ተቃውሞው ጠንካራ እንደነበር ለማወቅ ተችሏል።
በወለጋ ጊምቢ የተካሄደው ተቃውሞ በብዙ ሺህ የሚቆጠር የከተማዋ ነዋሪ የታደመበት ሲሆን የህወሀት መንግስት ከስልጣን እንዲወርድም ተጠይቋል።
ሆለታ፣ በሀረርጌ ኮምቦልቻ ተቃውሞ ከተካሄደባቸው አካባቢዎች የሚጠቀሱ ሲሆን ባለፈው ረቡዕ ዘጠኝ ሰዎች ወደ ተገደሉባት ሻሸመኔ ተጨማሪ የፌደራል ሃይል እንዲገባ መደረጉ ታውቋል።
ሶስተኛ ቀኑን የያዘው የኦሮሚያ ክልል ተቃውሞ አድማሱን እያሰፋ ሌሎች ከተሞችንና መንደሮችን እየጨመረ ቀጥሏል።
በምዕራብና ምስራቅ ወለጋ በዛሬው ተቃውሞ በርካታ ከተሞች ተሳታፊ ሆነዋል።
ትላንት በነቀምት የተጀመረው ተቃውሞ ዛሬም ቀጥሎ በስልጣን ላይ ላለው የህወሀት መንግስት ግልጽ መልዕክት የተላለፈበት ሆኖ ተጠናቋል።
የኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረስ የውጭ ድጋፍ ሰብሳቢ አቶ ነጌሶ ኦዳ ለኢሳት እንደገለጹት ከረቡ ጀምሮ እየተካሄደ ያለው ተቃውሞ በዋናነት ሁለት መልዕክቶችን የማስተላለፍ አላማ አንግቧል።
በዛሬው ተቃውሞ ከተሳተፉት አካባቢዎች የቡሌ ሆራ (ሀገረማርያም) ዩኒቨርስቲ ተማሪዎች ያደረጉት ከስርዓቱ ታጣቂዎች ጋር ግጭትን የፈጠረ ነበር።
ተማሪዎች በአመጽ የዩኒቨርሲቲውን ቅጥር ግቢ በማጥለቅለቅ ተቃውሞ ሲያሰሙ የስርዓቱ ታጣቂዎች የሃይል እርምጃ መውሰዳቸውንና በርካታ ተማሪዎች መጎዳታቸውን የደረሰን መረጃ ያመለክታል።
ትላንት በቦረና ዲሬ ወረዳ ስድስት ሰዎች በህወሀት ሰራዊት መገደላቸውን ተከትሎ እስከሞያሌ ያለው መንገድን ጨምሮ በዱብሉቅ፣ ያቤሎና ወደ ሌሎች ዋና ዋና ከተሞች የሚወስዱ መንገዶችም መዘጋታቸው የተገለጸ ሲሆን በቡሌ ሆራ የተፈጠረው ግጭትም በአካባቢው የሚገኙ መንገዶችን እንዲዘጉ ማድረጉን መረጃዎች ያመለክታሉ።
በወለጋ ጊምቢ የተካሄደው በከተማዋ ታሪክ ከፍተኛ ቁጥር ያለው ህዝብ የተሳተፈበት ሲሆን የተቃውሞው ማሳረጊያ መልዕክትም የህወሀት መንግስት በአስቸኳይ ከስልጣን እንዲወርድ የሚጠይቅ እንደነበረ ለማወቅ ተችሏል።
በሆለታ በተካሄደው ተቃውሞ ህዝቡ የመንግስት መስሪያ ቤቶች ድረስ በመሄድ የህወሀት መንግስት በአስቸኳይ ከስልጣን እንዲወርድ በመጠየቅ ድምጻቸውን አሰምተዋል።

Wednesday, October 11, 2017

(ኢሳት ዜና–ጥቅምት 2/2010) በወሊሶ ከተማ ዛሬ ህዝባዊ ተቃውሞ ተካሄደ።



በወሊሶ ከተማ ዛሬ ህዝባዊ ተቃውሞ ተካሄደ




ትላንት በሻሸመኔ ስምንት ሰዎች መገደላቸው ያስቆጣቸው የወሊሶ ከተማ ነዋሪዎች አደባባይ በመውጣት የህወሀት መንግስት በአስቸኳይ ከስልጣን እንዲወርድ ጠይቀዋል።

ፖሊስ በአስለቃሽ ጭስ ተጠቅሞ ሊበትን መሞከሩ ተገልጿል።

በሌላ በኩል በቱሉቦሎና በሱሉልታም ተመሳሳይ ህዝባዊ ተቃውሞ መካሄዱን የደረሰን መረጃ ያመለክታል።

ይህ በእንዲህ እንዳለም ከሶማሌ ክልል የተፈናቀሉት ዜጎች በችግር ላይ መሆናቸው እየተነገረ ነው።

ዘግይተው የሚወጡ መረጃዎች እንደሚያመለክቱት ዛሬም በበርካታ የኦሮሚያ ክልል ከተሞች ተቃውሞዎች ተካሂደዋል።

ትላንት አምቦ፣ ሻሸመኔን፣ አዳባንና ኮፈሌን ጨምሮ በሀረርጌ የተለያዩ ከተሞችን ያዳረሰው ህዝባዊ ተቃውሞ ዛሬም በሌሎች ከተሞች በመካሄድ ቀጥሏል። ወሊሶ፣ ምዕራብ ወለጋ ጊምቢ፣ ቄሌም ወለጋ፣ አጋርፋ ፣ቱሉ ቦሎ፣ ሱሉልታ ዛሬ ህዝባዊ ተቃውሞ ተደርጎባቸው ውለዋል።

ትላንት ስምንት ሰዎች የተገደለባት ሻሸመኔ ዛሬም መረጋጋት እንደሌለ የተነገረ ሲሆን ተቃውሞ ቀጥሎ መዋሉን ነው መረጃዎች የሚያመለክቱት።

ከፍተኛ ቁጥር ያለው የመንግስት ሃይል ወደሻሸመኔ መግባቱንም ለማወቅ ተችሏል።

ለኢሳት የደረሰው መረጃ እንደሚያመለክተው አምቦ ለሁለተኛ ቀን ተቃውሞ ተካሂዶባታል። በተለይ በአምቦ ዩኒቨርሲቲ የመንግስት ለውጥ የሚጠይቅ የተቃውሞ ድምጽ ሲሰማ እንደነበረ ከስፍራው የደረሰን መረጃ አመልክቷል።

ዛሬ በወሊሶ ከንጋት ጀምሮ ህዝቡ በዋና ዋና መንገዶች ላይ በመውጣት ተቃውሞውን ማሰማቱን ከስፍራው ያነጋገርነው ነዋሪ ገልጾልናል።

ትላንት በሻሸመኔ የተፈጸመው ግድያ የወሊሶን ነዋሪ ማስቆጣቱን የተገለጸ ሲሆን የህወሀት መንግስት በአስቸኳይ ከስልጣን እንዲለቅም ጠይቋል።

የወሊሶውን ተቃውሞ የመንግስት ታጣቂዎች በአስለቃሽ ጭስ ለመበተን እንደሞከሩ ታውቋል።

የሁለተኛ ደረጃ ተማሪዎች ትምህርታቸውን አቋርጠው ተቃውሞውን በመቀላቀላቸው ሁኔታው ከፖሊስ አቅም በላይ ሊሆን እንደቻለም ያነጋገርነው ነዋሪ ገልጿል።

በወሊሶው ተቃውሞ አቶ አባይ ጸሀዬ ተለይተው ስማቸው ተጠርቶ ተወግዘዋል።

የህወሀት መንግስት ከእንግዲህ አይገዛንም የሚለው መልዕክት ከፍ ብሎ ተሰምቷል። ከተማሪ እስከ አርሶ አደር የተሳተፉበት ይህው ተቃውሞ በሰላም መጠናቀቁን ነው ያገኘነው መረጃ የሚያመለክተው።

በሌሎች የኦሮሚያ ክልል ከተሞችና አነስተኛ መንደሮች የተካሄዱት የተቃውሞ ትዕይንቶች ተመሳሳይ መልዕክቶች የተላለፉ ሲሆን የኦፌኮ መሪዎች ይፈቱ፣በሶማሌ ልዩ ሃይል የሚካሄደው ማፈናቀልና ግድያ ይቁም፣ የሚሉት ዋናዎቹ መፈክሮች ነበሩ።

በተለይ በምዕራብ ወለጋ ጊምቢና ቄሌም ወለጋ መንገዶች ተዘግተው ተቃውሞ እንደተደረገባቸው ለማወቅ ተችሏል።

በሌላ በኩል ከሶማሌ ክልል የተፈናቀሉ ዜጎች ችግር ውስጥ መሆናቸውን ኢሳት ያነጋገራቸው የወሊሶ ነዋሪ ገልጸዋል።

በወሊሶ በየቀበሌው ተጠልለው የሚገኙ ተፈናቃዮች ምግብ የሚያቀርብላቸው እንደሌለ የተገልጸ ሲሆን በመንግስት በኩል እስከአሁን ምንም ድጋፍ አልተደረገላቸውም ተብሏል።








Tuesday, October 10, 2017

How Many People Have Ever Lived on Planet Earth?


How Many People Have Ever Lived on Planet Earth?





It’s easy to think that our lifetime and the world around us is unique and definitive. But thinking about how many people have ever lived on this planet can add some perspective to our instinctive self-centeredness. And it’s not only a matter of how many people lived before we appeared, but how many have died.

So what’s the answer? According to estimates by demographic researchers at the Population Reference Bureau (PRB), as of 2015, there have been 108.2 billion who have ever been born. Taking away the roughly 7.4 billion who are alive today, we get 100.8 billion who have died before us.

There are almost 14x more people dead than alive! That would make for one massive army of zombies, ghosts and White Walkers. Or, if you prefer to be more optimistic, you can think that the living are about 6.8% percent of everyone who’d ever lived. For the sake of simplicity (and to take into account the people born in the past year), lets round up the percentage to 7. We are the 7%2. Let’s make the most of it!

How do the researchers come up with these estimates? The starting point that the Population Reference Bureau takes for the beginning of what it considers human history is 50,000 BC, when the modern Homo Sapiens appeared. This date in itself is debatable as early hominids walked the earth millions of years ago. The date of 50,000 BC is taken from the United Nations Determinants and Consequences of Population Trends.

Coming up with how many people were born after that is certainly based on informed speculation. Plagued by low life expectancy (up to 10 years during the Iron Age) thanks to lack of medicine, food supply issues, climate changes, killing each other and other problems, human population grew at a slow rate. Early infant mortality was as high as 500 infant deaths per 1,000 births or higher.

Here’s a chart from PBR estimating how population expanded (at least until 2011).



Interestingly, you can see how the rate of growth was lower from 1AD until 1650 AD, mainly due to such events as the outbreak of the plague, known as Black Death. You can also see the great population expansion from about the time of the Industrial Revolution to our current day. From 1850 till now, the planet’s living population increased by about 6 times!

Certainly, some of these numbers are to be argued. The researchers made guesstimates on the birth rates and set a constant rate of population growth, which surely fluctuated. Still, this estimate gives us a useful perspective on our place in the life of our planet.

Here’s Carl Haub from PRB talking about his methodology:

Monday, October 9, 2017

በኢትዮጵያና ኬንያ ድንበር ስኳር ጭነው የቆሙት ከባድ ተሽከርካሪዎች ባለንብረቶች ችግር ውስጥ መውደቃቸውን ገለጹ

Bildergebnis für moyale sugar carryng lorries

(ኢሳት ዜና–መስከረም 24/2010)
 በኢትዮጵያና ኬኒያ ድንበር ሞያሌ ላይ ከሁለት ወራት በላይ ስኳር ጭነው የቆሙት ከባድ ተሽከርካሪዎች ባለንብረቶች ከፍተኛ ችግር ውስጥ መግባታቸውን በተለይ ለኢሳት ገለጹ።
ከ100 በላይ የሚሆኑትና እያንዳንዳቸው 400ኩንታል ስኳር የጫኑት እነዚህ ተሽከርካሪዎች ለከፍተኛ ብልሽት እየተዳረጉ ሲሆን የጫኑት ስኳርም በመቅለጥ ላይ መሆኑን አስታውቀዋል።
በባንክ ብድር የገዟቸው ተሽከርካሪዎች ያለስራ ከሁለት ወራት በላይ በመቆየታቸው ለባንክ የሚከፍሉት ገንዘብ እንደሌላቸው የጠቀሱት ባለንብረቶቹ አቶ ሃይለማርያም ደሳለኝን ለማነጋገር ያደረጉት ጥረትም እንዳልተሳካላቸው ገለጸዋል።
በሌላ በኩል የሕወሃት መንግስት ከአየን ንብረት ለውጥ ጋር በተያያዘ በሀገሪቱ ከፍተኛ የሆነ የስኳር እጥረት መከሰቱን ገልጿል።
መነሻቸው ወንጂ መዳረሻቸው ናይሮቢ ኬኒያ ነበር። ብራይት ድንበር ተሻጋሪ ከተሰኘ ማህበር ጋር ውል ፈጽመው ከ44ሺህ ኩንታል በላይ ስኳር ወደ ናይሮቢ ለመውሰድ የተስማሙት 110 ከባድ ተሽከርካሪ ባለንብረቶች፡ ከሁለት ወራት በፊት ጉዞ ይጀምራሉ። የኢትዮጵያን ድንበር ከማቋረጣቸው በፊት ሞያሌ ላይ ያልተጠበቀ ነገር ገጠማቸው። ወደፊት የማያስኬድ ባሉበት እንዲቆሙ የሚያደርግ ጉዳይ። ከቀረጥ ነጻ እንዲገባ የተፈቀደለት ስኳር ሞያሌ ላይ ተገታ።
ምክንያቱ በእርግጥ አልታወቀም። የሚቀበላችሁ ሰው ጠፍቷል የሚል መልስ ግን ይሰማሉ። ከቀረጥ ነጻ ይሆናል የተባለበት ጊዜ ገደብ በማለፉ እንዲገባ አልተፈቀደለትም የሚል ወሬም አለ።
የኬንያ መንገዶች ይህን ያህል ጭነት መሸከም የማይችሉ በመሆናቸው ጭነቱን ካልቀነሱ አይገቡም የሚል ምክንያትም ይነሳል።
ከየትኛውም የሁለቱ ሀገራት መንግስታት ትክክለኛው ምክንያት እስከአሁን አልታወቀም። መመለስ የማይቻል ሆነ። ወደፊት መቀጠልም ተከለከለ። ከ100 በላይ ከባድ ተሽከርካሪዎች መንገድ ዘግተው ከጫኑት ስኳር ጋር ለቀናት ፣ለሳምንታትና ለወራት ባሉበት እንዲቆሙ ተደረጉ።
ከወዲህም ከወዲያም መፍትሄ የሚሰጥ ያጡት ባለንብረቶች ለከፍተኛ ችግር መጋለጣቸውን ነው በተለይ ለኢሳት የገለጹት።
ጸሀይና ቅዝቃዜ እየተፈራረቁባቸው የሚገኙት ተሽከርካሪዎች የጫኑት ስኳር በመቅለጡ በንብረት ላይ የሚያደርሰው ጉዳት ለከፍተኛ ኪሳራ እየዳረጋቸው እንደሆነም ገልጸዋል።
ኪሳራው ያለስራ በመቀመጣቸው ተበድረው ለገዟቸው ተሽከርካሪዎች የሚከፍሉት ገንዘብ እንዳይኖራቸው በማድረግ ህልውናቸው አደጋ ላይ መውደቁንም ባለንብረቶቹ ይናገራሉ።
ከ44ሺህ ኩንታል በላይ ስኳር የጫኑት ተሽከርካሪዎቹ በአሁኑ ሰዓት በመከላከያ ሰራዊት እየተጠበቁ ባሉበት ይገኛሉ። ባለንብረቶቹ መንግስት ጉዳዩን እልባት እንዲሰጠው ያደርጉት ሙከራ ሊሳካ አልቻለም።
አቶ ሃይለማርያም ደሳለኝን ለማነጋገር ስድስት ተወካዮቻቸውን ቢልኩም እንዳልተፈቀደላቸው ገልጸዋል። መፍትሄ የሚሰጠን አጣን ሲሉም በምሬት ይናገራሉ።
በስልጣን ላይ ያለው መንግስት ባለፈው ዓመት በተያዘው 2010 መጀመሪያ አንስቶ ስኳር ወደ ውጭ መላክ እንደሚጀመር መናገሩ ይታወሳል።
በሀምሌ ወር ላይም ወደኬንያ ስኳር መላክ መጀመሩን የመንግስት መገናኛ ብዙሃን መግለጻቸው ይታወሳል።–ተላከ የተባለው ስኳር ሞያሌ ላይ ተገቶ ቀረ እንጂ።
ዛሬ የስኳር ኮርፖሬሽን በይፋ እንደገለጸው በኢትዮጵያ የስኳር እጥረት አጋጥሟል። ችግሩን በመደበቅ የቆየው መንግስት እጥረት መከሰቱን ባመነበት በዛሬ መግለጫው የእጥረቱን ምክንያት ከአየር ንብረት ለውጥ ጋር ማያያዙ አስገራሚ ሆኗል።
ከ77ቢሊየን ብር በላይ የተመደበለትና በህወሀት ጄኔራሎች በሚመራው ሜቴክ የተዘረፈውን ገንዘብ በመደበቅ ምክንያቱን በአየር ንብረት ላይ ማላከኩን ታዛቢዎች ይገልጻሉ።

Ethiopia’s ethnic federalism is being tested (The economist)

Ethiopia’s ethnic federalism is being tested

Violence between ethnic groups has put the country on edge
FOR centuries the city of Harar, on the eastern fringes of the Ethiopian highlands, was a sanctuary, its people protected by a great wall that surrounded the entire city. But in the late 19th century it was finally annexed by the Ethiopian empire. Harar regained a bit of independence in 1995, when the area around it became the smallest of Ethiopia’s nine ethnically based, semi-autonomous regions. Today it is relatively peaceful and prosperous—and, since last month, a sanctuary once more.
In recent weeks thousands of Ethiopians have poured into areas around Harar, fleeing violence in neighbouring towns (see map). Nearly 70,000 people have sought shelter just east of the city. Several thousand more are huddling in a makeshift camp in the west. Most are Oromo, Ethiopia’s largest ethnic group. Its members clashed with ethnic Somalis in February and March, resulting in the death of hundreds. The violence erupted again in September, when more than 30 people were killed in the town of Awaday. Revenge killings, often by local militias or police, have followed, pushing the death toll still higher. In response, the government has sent in the army.

Latest updates

See all updates
Ethnic violence is common in Ethiopia, especially between Oromos and Somalis, whose vast regions share the country’s longest internal border. Since the introduction of ethnic federalism in 1995, both groups have tried to grab land and resources from each other, often with the backing of local politicians. A referendum in 2004 that was meant to define the border failed to settle the matter. A peace agreement signed by the two regional presidents in April was no more successful.
When the ruling Ethiopian People’s Revolutionary Democratic Front (EPRDF) swept to power in 1991 after a bloody 15-year civil war, federalism was seen as a way to placate the ethnic liberation movements that helped it to power. The previous regime had been dominated by the Amhara, the second-largest ethnic group (the Eritreans broke away to form a new state). Eventually ethnic loyalties would wither as people grew richer, went the thinking of the Marxist-inspired EPRDF.
But the way federalism was implemented caused problems from the start. New identity cards forced people to choose an ethnicity, though many Ethiopians are of mixed heritage. Territories often made little sense. In the Harari region, a minority of Hararis rule over much bigger populations of Oromos and Amharas, a source of resentment. Boundaries that were once porous became fixed, leading to disputes.
For years the EPRDF sought to dampen the tension by tightly controlling regional politics. But its grip has loosened over time. Local governments have grown stronger. Regional politicians are increasingly pushing ethnic agendas. The leaders of Oromia, the largest region, have drafted a bill demanding changes to the name, administration and official language of Addis Ababa, the capital, which has a special status but sits within Oromia. They have stoked ethnic nationalism and accused other groups of conspiring to oppress the Oromo.
Politicians in the Somali region are no more constructive. They have turned a blind eye to abuses by local militias and a controversial paramilitary group known as the Liyu. The region’s president “has a fairly consistent expansionist agenda”, says a Western diplomat. “He may have spied an opportunity.” The federal government, now dominated by the Tigrayan ethnic group, was rocked by a wave of protests last year by the Oromo and other frustrated groups.
Many complain that the rulers in Addis Ababa are doing too little. They have been slow to respond to the recent violence, fuelling suspicions that they were complicit. “We are victims of the federal government,” shouts Mustafa Muhammad Yusuf, an Oromo elder sheltering in Harar. “Why doesn’t it solve this problem?”
Federalism may have seemed the only option when it was introduced in 1995. But some now suggest softening its ethnic aspect. “In the past the emphasis was too much on ethnic diversity at the expense of unity,” says Christophe Van der Beken, a professor at the Ethiopian Civil Service University. “The challenge now is to bring the latter back.”
This article appeared in the Middle East and Africa section of the print edition under the headline "Unity v diversity"

Sunday, October 8, 2017

በላስቬጋስ የጅምላ ግድያን ከፈጸመው ግለሰብ የሆቴል ክፍልና ከቤቱ በአጠቃላይ 42 መሳሪያዎች ተገኙ

Bildergebnis für las vegas shoots 42

በኔቫዳ ግዛት ላስቬጋስ ከተማ የተፈጸመውና በአሜሪካ ታሪክ ከፍተኛ የተባለው የጅምላ ግድያን ከፈጸመው ግለሰብ የሆቴል ክፍልና ከቤቱ በአጠቃላይ 42 መሳሪያዎችን ማግኘቱን የግዛቲቱ ፖሊስ አስታወቀ።
በአደጋው የሞቱት ሰዎች ቁጥር 59 ሲደርስ የቆሰሉት ደግሞ 527 ደርሰዋል።
አለም አቀፉ አሸባሪ ቡድን አይ ሲስ ስቴፈን ፓዶክ እምነቱን የቀየረ አባላችን ነው ሲል መግለጫ ሰጥቷል።
የአሜሪካ ባለስልጣናት ድርጊቱን ከሽብር ጋር የሚያገናኘው ምልክት አላየንም ሲሉ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ደግሞ የድርጊቱን ፈጻሚ በሽተኛ በማለት ጠርተውታል።
ጡረተኛውና ሐብታሙ አካውንታንት የ64 አመቱ ስቴፈን ፓዶክ በበረሃማዋ ውብ የቁማር ከተማ ላስቬጋስ ውስጥ የፈጸመው ድርጊት የአለም አቀፍ መገናኛ ብዙሃን መነጋገሪያ ሆኖ ቀጥሏል።
በላስቬጋስ ከተማ ማንዳላይ ቤይ ከሚባለው ሆቴል 32ኛ ፎቅ ከመኝታ ክፍሉ ውስጥ ቁልቁል በመተኮስ ፍጅት ያነገሰው የ64 አመቱ አሜሪካዊና የላስ ቬጋስ ከተማ ነዋሪ የአባቱን የባንክ ዘራፊነት የሚያስታውሱ ሪፖርቶች እንዲወጡም ምክንያት ሆኗል።
ምን እንደተፈጠረ መረዳት ቸግሮኛል በማለት በተከሰተው ሁኔታ ግራ መጋባቱን ለመገናኛ ብዙሃን የገለጸው በፍሎሪዳ ኦርላንዶ ነዋሪ የሆነው የነፍሰ ገዳዩ ወንድም ኤሪክ ፓዶክ ነው።
በግድያው ማግስት ሰኞ ለመገናኛ ብዙሃን እንደተናገረው ወንድሙ ሚሊየነርና በጡረታ ላይ የሚገኝ አካውንታንት ቢሆንም ጤናማ የሚባል አይነት ሰው አልነበረም ሲል ገልጾታል።
ቪዲዮ ፖከር በተባለው የቁማር አይነት የተለከፈ ሰው እንደነበርም ተናግሯል።
በሪል ስቴት ቢዝነስ ላይ የሚገኘው ሚሊየነሩ ስቴፈን ፓዶክ ኪሳራ ይድረስበት አይድረስበት የማውቀው ነገር የለም ያለው ኤሪክ ፓዶክ በቅርቡ ለ90 አመቷ እናታቸው ለእግር ጉዞ የሚያግዛቸው መሳሪያ በፖስታ ቤት እንደላከላቸውም ገልጿል።
በልጅነቱ ሳንቲሞችን የማጠራቀም ፍቅር እንጂ የመሳሪያ ፍላጎት እንዳልነበረውና በየትኛውም ሰራዊት ውስጥ እንዳላገለገለ ወንድሙ ኤሪክ ፓዶክ ለመገናኛ ብዙሃን ገልጿል።
59 ንጹሃን ዜጎችን በመጨፍጨፍ 527 ሰዎችን ያቆሰለው ፓዶክ ከቀደመ የቤተሰቡ ታሪኩ መረዳት እንደተቻለውም አባቱ የታወቀ የባንክ ዘራፊና በኤፍ ቢ አይ ተፈላጊዎች ዝርዝር ውስጥ የተመዘገበ ወንጀለኛ ነበር።
እንደ አውሮፓውያኑ አቆጣጠር ከ1969 እስከ 1977 በአሜሪካ የፌደራል ምርመራ ቢሮ እጅግ በጣም ተፈላጊ ተብለው ከሚታደኑ 10 ወንጀለኞች የላስቬጋሱ ጨፍጫፊ ስቴፈን ፓዶክ አባት ቤንጃሚን ፓዶክ አንዱ ነበር።
ማንዳሊን ቤይ ከሚባለው ሆቴል 32ኛ ፎቅ አልጋ ከያዘበት ክፍል ቁልቁል የሙዚቃ ትርኢት ይከታተል በነበረው ሕዝብ ላይ መሳሪያ እየለዋወጠ ፍጅት ያነገሰው ስቴፈን ፓዶክ ድርጊቱን ለምን እንደፈጸመ እስካሁን የተረጋገጠ ነገር የለም።
ፖሊሶች ግለሰቡን በቁጥጥር ስር ለማድረግ በተንቀሳቀሱበት ወቅት አስቀድሞ ራሱን በመግደሉ ምርመራውን ይበልጥ ውስብስብ አድርጎታል።
አለም አቀፉ የሽብር ቡድን አይ ሲስ ስቴፈን ፓዶክ እምነቱን ወደ እስልምና የቀየረ አባላችን ነው በማለት ለድርጊቱ ሃላፊነቱን ወስዷል።
ጥምሩ ሃይል ለከፈተብን ጥቃት አጸፋ ነው ሲልም በድርጊቱ መደሰቱን ገልጿል።
የአሜሪካ ባለስልጣናት ጉዳዩ እየተመረመረ መሆኑን የገለጹ ሲሆን ሆኖም ድርጊቱ ከየትኛውም የሽብር ቡድን ጋር ግንኙነት እንዳለው የሚያመላክት ምንም አይነት ፍንጭ አለማግኘታቸውን አስታውቀዋል።

Saturday, October 7, 2017

በኢየሩሳሌም የሚገኘው ዴር ሱልጣን ገዳም አደጋ ላይ መሆኑ ተገለጸ

Bildergebnis für ዴር ሱልጣን ገዳም

በኢየሩሳሌም የሚገኘው ዴር ሱልጣን ገዳም አደጋ ላይ መሆኑ ተገለጸ።
ከላይ በግሪክ ቤተክርስቲያን የተጀመረው ግንባታ ገዳሙን እያፈረሰው በመሆኑ አንደኛው ቤተክርስቲያን ሙሉ በሙሉ መዘጋቱን በእስራኤል የኢትዮጵያ ማህበረሰብ በተለይ ለኢሳት ገልጿል።
የሚካኤል ቤተክርስቲያን በጣሪያው ላይ በደረሰበት መደርመስ የተዘጋ ሲሆን የመድሃኒዓለም ቤተክርስቲያንም የመናድ አደጋ አንዣቦበታል ተብሏል።
ጉዳዩ ያሳሰባቸው ኢትዮጵያውያን በእስራኤል ከሚገኙ የቤተክርስቲያኒቱ አባቶች ጋር ትላንት ስብሰባ ማድረጋቸው ታውቋል።
የኢትዮጵያ ኤምባሲም ሆነ የኢትዮጵያ ኦሮቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ እስከአሁን ያደረጉት ነገር ባለመኖሩ የዴር ሱልጣን ይዞታን ኢትዮጵያ ልታጣ ትችላለች የሚለው ስጋት በሰፊው እየተሰማ ነው።
በዴር ሱልጣን የሚካኤል ቤተክርስቲያን ባለፈው መስከረም 12 የሚካኤል ንግስ ይከበር ነበር። ምዕመናን የዕለቱን መርሃግብር ተከታትለው ጨርሰው ከወጡ በኋላ የቤተክርስቲያኒቱ ጣሪ መደርመሱ ተሰማ።
በአጋጣሚ መርሃግብሩ ተጠናቆ በመሆኑ እንጂ በሰው ህይወት ላይ አደጋ የሚፈጥር ክስተት እንደነበር በዕለቱ የታደሙ ሰዎች ይናገራሉ።
ከላይ የግሪክ ቤተክርስቲያን እያካሄደ ያለው ግንባታ ለመደርመሱ ምክንያት እንደሆነም ይነገራል። በእስራኤል የኢትዮጵያ ማህበረሰብ ሰብሳቢ አቶ ተስፋሁን እሸቱ እንደሚሉት ሁለቱ ቤተክርስቲያናት አደጋ ውስጥ ወድቀዋል።
የሚካኤል ቤተክርስቲያን ጣራ በመደርመሱ ምክንያት ተዘግቷል። በፖሊስ እንዲታሸግም ተደርጓል። በዚህም የተነሳ ምንም አይነት መንፈሳዊ አገግልግሎት አይሰጥም።የመድሃኒያዓለም ቤተክርስቲያንም እየፈረሰ ነው።
በገዳሙ አናት ላይ በግሪክ ቤተክርስቲያን ላለፉት ስድስት ዓመታት እየተካሄደ ያለው ግንባታ በእርጅና ላይ ያለውን ዴር ሱልጣንን ጨርሶ እንዳያጠፋው የሚሰጉ ኢትዮጵያውያን ድምጻቸውን ማሰማት ጀምረዋል።
ይህ ገዳም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ይዞታ፣ በኢትዮጵያ ስም የሚታወቅ ገዳም መሆኑን በመጥቀስ እየደረሰበት ያለው የመደርመስ አደጋ አፋጣን መፍትሄ ሊፈለግለት እንደሚገባ እየተነገረ ነው።
ቅርሶች እየተበላሹና እየተሰባበሩ መሆናቸው ደግሞ አደጋውን የከፋ አድርጎታል ይላሉ አቶ ተስፋሁን።
የገዳሙ ህልውና ያሳሰባቸው ኢትዮጵያውያን ትላንት እስራዔል ከሚገኙ የቤተክርስቲያኒቱ አባቶች ጋር ስብሰባ አድርገዋል።
በእስራኤል የሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲ በጉዳዩ ላይ እስከአሁን ዝምታ መምረጡ ይነገራል።
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያንም ትኩረት ባለመስጠቷ ገዳሙ ባለቤት እንደሌለው ተቆርቋሪ በማጣቱ ወደፊት ዴር ሱልጣን ላይ ኢትዮጵያ ያላት መብት ሊነጠቅ ይችላል የሚል ስጋት በብዙዎች ዘንድ አድሯል።
የኢትዮጵያ ማህበረሰብ ሰብሳቢ አቶ ተስፋሁን እሸቱ ይህ የኢትዮጵያ ቅርስ የገጠመው አደጋን ለመታደግ የሁሉም ኢትዮጵያዊ ርብርብ ያስፈልጋል ብለዋል።

wanted officials