Which one you first choose? በቅድሚያ የሚፈልጉት

Friday, April 7, 2017

"Tigeray is equal to Ethiopia and Ethiopia is equal to Tigeray"

"እናት ሀገር ትግራይ"
ቻይናዊው በጉዋንዙ
"Tigeray is equal to Ethiopia and Ethiopia is equal to Tigeray"
አብርሃ ገ/ዋህድ-የትግራይ ወጣቶች ማህበርና ሊግ ፕሪዚዳንት በጉዋንዙ ቻይና።
የህወሃቶች ትግራይን እንደ ሀገር አድርገው የሚያደርጉት የተናጥል ግንኙነት።
****
[ወንድወሰን ተክሉ]Image may contain: sky and outdoor
***
በቅርቡ አለቃ ጸጋዪ በእስራኢል የኢትዮጵያ አምባሳደር ተደርጎ ሲሾም ለእስራኢላውያኑ እራሱን ሲያስተዋውቅ "My name is Aleka Tsegaye I came from Tigray country a land of Sheba" ብሎ እንደነበር ሁላችንም የምናስታውሰው የቅርብ ግዚ ትዛታ ነው። በወቅቱም የሰውዪውን አባባል ከእውቀት ማነስና ከድንቁርና ጋር አያይዘው በማየት አባባሉን አቃላው ለማየት ሲሞክሩ ብዙዎች ታይተዋል። ጉዳዪ ግን በእውቀት ማነስ የተከሰተ ተራ ስህተት ሳይሆን ሆን ተብሎ የተደረገ፣ ቀደም ብሎም ሲደረግ እንደነበረ መሆኑን የምንረዳው ከዚህ ቀጥሎ ያቀረብኩትን እውነተኛ ተመሳሳይ ክስተት ከዓመታት በፊት በምድረ ቻይና መፈጸሙን ስናይ ነው። ክስተቱን የዓይን ምስክር ሆኖ በጻፈው ሰው አጻጻፍ እንደወረደ አቅርቢዋለሁ።
*****
በቻይና ጉዋንዙ ፕሮቪንስ ለጉብኝት የሂድን 12ካድሪዎች በሳምንት እንድንጎበኝ የተመረጠው በቻይና የሚገኘውን ትልቁን የአውቶሞቢል ፋብሪካ ነበር። ስንሂድም በጣም የደመቀ አቀባበል ተደረገልን። ከእኛ ጋር ከዘጥኝ የአፍሪካ አግሮች የተውጣጡ ወጣት አመራሮች የተገኙበት ጉብኝት ስለነበረ ብቻችንን አልነበርንም። የፋብሪካው ዋና ስራ አስኪያጅ ገለጻውን ከመጀመሩ በፊት ሁላችንም ወደ ፖዲየሙ ቀርበን የመጣንበትን አገር እንድናስተዋውቅ ጠየቀን። መጀመሪያ ከደቡብ አፍሪካ ቀጥሎም ከግብጽ የመጡት ወጥተው የመጡበትን አገር በተወካያቸው እንደተናገሩ ቀጥሎ የእኛ ተራ ሆነና የቡድናችን መሪ መድረክ ላይ ወጥቶ የመጣነው ከኢትዮጵያ ነው ብሎ አስተዋወቀ። ቻይናዊው ስራ አስኪያጅ የቡድናችን መሪ ከኢትዮጵያ ብሎ ሲያስተዋውቅ ባለማወቅ ግራ ሲጋባ በመታየቱ የቡድናችን መሪ ኢትዮጵያ ማለት በምስራቃዊው አፍሪካ ቀንድ ያለች አገር የ13ወር የጸሀይ ጸጋ..የሰው ልጅ መገኛ..ቅኝ ያልተገዛች ብቸኛዋ አፍሪካዊት አገር...እያለ ደረደረ። ቻይናዊው ስራ አስኪያጅ ግን "ምንድነው እምትቀባጥረው" በሚል አስተያየት አሁንም ኢትዮጵያ ስለተባለችው አገር አለማወቁን ይገልጻል።በዚህ ግዚ እኛን አጅቦን ወደ ፋብሪካው የወሰደን ባለስልጣን የቻይና ኮሚኒስር ፖርቲ ወጣቶች ሊግ ፕሪዚዳንት ወደ ስራ አስኪያጁ ጆሮ ጠጋ ብሎ በቻይኒኛ ለእኛ ያልገባንን ነገረው። በዚህን ግዚ ስራ አስኪያጁም በሚያስፎግር ሁኒታ ፈገግ ብሎ ኦው "ኢፈርት..ትግራይ ኢፈርት። ባለፈው ሳምንት ከአንባሳደራችሁ አዲስ-ዓለም ባሊማ ጋር እራት በልተናል። እዚህ እምታዩቱን አውቶሞቢል ትግራይ ለመገጣጠም ፍላጎት እንዳላት ነግሮኛል።... ትግራይ በጣም ቆንጆ ሀገር እንደሆነች ነግሮኛል። እኒም ለጉብኝት ከወራቶች በሃላ እመጣለሁ" በማለት የመጣንበትን አገር ኢትዮጵያን ሳይሆን ሀገረ ትግራይን እንደሚያውቅ ተናገረ.*****
[ጸሃፊውን ላቃርጥ እዚህጋ-ልብ በሉ-በቻይና ጉዋንዙ ያለው አውቶሞቢል ፋብሪካ ስራ አስኪያጅ እነዚህ ጎብኚዎች ከመምጣታቸው በፊት ከአምባሳደር አዲስ-ዓለም ባሊማ ጋር የስራ ስምምነት አድርጋል-ስምምነቱ የተካሂደው በኢትዮጵያን አምባሳደር ነኝ በሚለው አዲስ-ዓለም ባሊማ እና በቻይናው አውቶሞቢል ፋብሪካ መካከል የሆነ ሆኖ ሳለ አምባሳደሩ ግን እራሱን የገለጸውና እውክለዋለሁ ብሎ ለስራ አስኪያጁ የነገረው ትግራይ የምትባል አገር እንጂ ኢትዮጵያ የምትባልን አገር እንዳልሆነች ልብ ልንል ይገባል.***]
ከስራ አስኪያጁ ንግግር በሃላ ሁላችንም [ኢትዮጵያውያኑ] ተያየን። ሰውዪው ኢትዮጵያን በስም እንካን አያውቃትም። ስለ ኢፈርት እና ትግራይ ግን ብዙ እውቀት አለው። ኢትዮጵያ የምትባለዋ ታላቅ ሀገር ትግራይ በምትባል ሀገር ውስጥ ያለች ክፍለ ሀገር አድርጎ ተገንዝባል። ትግራይን ሀገር-ኢትዮጵያን ክፍለ ሀገር አድርጎ ነው እንደተነገረው የተረዳው። ሰውዪው [ቻይናዊው ስራ አስኪያጅ]በዚህም ቢያበቃ መልካም ነበር። ቆይቶ በተዘጋጀልን ቅልጥ ያለ የእራት ግብዣ ላይ [ከኢትዮጵያ ለመጡት ብቻ ተነጥሎ የተዘጋጀ] "እናት ሀገር ትግራይ" እያለ ደጋግሞ መግለጽና መጥራት ቀጠለ።ሁኒታው አልመችህ አለኝ። ከዚህ በሃላ አስተካክሎ እንዲናገር ስለፈለኩ በግብዣው ላይ የመናገር ተራዪ ሲደርስ ሀገራችን ኢትዮጵያ መሆናንና ህዝባም ከ90 ሚሊዮን በላይ እንደሆነ፣ ትግራይ ደግሞ የኢትዮጵያ አካል ሆና ወደ 5ሚሊዮን የሚጠጋ ህዝብ የሚኖርባት አንድ ክልል እንደሆነች ተናገርኩ። ትግራይ በኢትዮጵያ ውስጥ ያለች ክፍለ ሀገር መሆናን ረገጥ አድርጊ አስረዳሁ። ሰውዪው በመሳሳቱ ይቅርታ ጠይቆን ከዚህ በሃላ ኢትዮጵያ እያለ እንደሚጠራ ቃል ገባ። [ቻይናዊው ስራ አስኪያጅ ምንም ስህተት እንዳለደረገ የምናውቀው ሰውዪው ቀደም ብሎ በአምባሳደር አዲስ-ዓለም ባሊማ የተነገረውን የትግራይን ሀገርነትን ተንተርሶ ሊናገር እንደቻለ በማስታወስ ነው]
ከእኒ ቀጥሎ የተናገረው የትግራይ ወጣቶች ማህበርና ሊግ ፕሪዚዳንት አብርሃ ገ/ዋህድ ነበረ። አብርሃ በእኒ አባባል የተቆጣ ስሚት ውስጥ ሆኖ "Tigeray is equal to Ethiopia and Ethiopia is equal to Tigeray" በማለት ለቻይናዊው ለማስረዳት ሞከረ። የአዲስ አበባ ወጥቶች ፕሪዚዳንት ታጠቅን ጨምሮ የሁሉም ክልል ተወካዮች አብርሃን ተቃውመው ተናገሩ። አብርሃ በንዲት ተናጋሪዎችን እያቃረጠ እሱ እንዳለው እንዱያስተካክሉ ሲሞክር እኒም ተናድጂ አብርሃ እዚህ ውስጥ ካለነው 12 ኢትዮጵያውያን 11 ያህሉ ትግራይ አይደለንም በማለት እቅጩን ነገርኩት።
****
በእስራኢል እኒ ከትግራይ ሀገር የመጣሁ ነኝ ያለው አለቃ ጸጋዪ ተሳስቶ ወይም የእውቀት ማነስ አጥቅቶት እንዳልሆነ በደንድ መረዳት ይቻላል። ሰዎቹ በኢትዮጵያን ህዝብ ስምና ንብረት የኢትዮጵያ አምባሳደር እየተባሉ በኢትዮጵያን ህዝብ ገንዘብ እየተዳደሩ ግን በየሂዱበት አገር ያልተፈጠረችውን ትግራይ እንደ ሀገር እያስተዋወቁ የሚሰሩ መሆናቸውን የሚያሳይ ነው።
አምባሳደርነቱን የሚሾሙት በኢትዮጵያ ስም፣ ደሞዝ ከፋይ የኢትዮጵያ ህዝብ፡ ስራቸው ግን ትግራይን እንደ ሀገር ማስተዋወቅና ውል መዋዋል ብሎም የኤፈርትን ንግድ ማጣጣፍ ሆናል። ይህች ናት በህወሃት ስር እየተገዛች ያለችው አገራችን ሁኒታ።
[ምንጭ- የመለስ ልቃቂት።በኢርሚያስ ለገሰ መጽሃፍ]

No comments:

Post a Comment

wanted officials