Which one you first choose? በቅድሚያ የሚፈልጉት

Monday, November 26, 2018

ኦነግ አዲስ ፓርቲ አይደለሁም እንደ አዲስ አልመዘገብም አለ

በአቶ ዳውድ ኢብሳ የሚመራው የኦሮሞ ነፃነት ግንባር(ኦነግ) ከምርጫ ቦርድ ጋር የጀመረው ውዝግብ ቀጥሏል፡፡ ከውጭ አገር የገቡ ፓርቲዎች በሙሉ በቦርዱ እንዲመዘገቡ ጥሪ የተላለፈ ሲሆን ኦነግ ግን አልመዘገብም ብሏል፡፡
ለዚህ ያቀረበው ምክንያት ደግሞ በ1983 የሽግግር መንግስቱ ጊዜ የተመዘገብኩ ስለሆነ ድጋሚ መመዝገብ አያስፈልገኝም የሚል ነው፡፡ ይህንኑ ምክንያት ጠቅሶ ለምርጫ ቦርድ ማመልከቻ አስገብቶ የነበረ ቢሆንም በዛሬው እለት ማመልከቻው ውድቅ እንደሆነበት ከምንጮች ሰምተናል፡፡ አሁን በስራ ላይ ባለው የቦርዱ ህግ መሰረት አንድ ፓርቲ ለሁለት የምርጫ ወቅቶች ካልተወዳደረ ምዝገባው እንደሚሰረዝ መደንገጉን ለማወቅ ችለናል፡፡
በመሆኑም ፓርቲው እንደአዲስ እንደሚመዘገብ በህጉ ላይ ተቀምጧል፡፡ እንደአዲስ ለመመዝገብ መተዳደሪያ ደንብ ማቅረብ፣ ጠቅላላ ጉባኤ ማከናወን፣ አባላትን ማሳወቅና ሌሎችም ሂደቶችን ማለፍ ይጠይቃል፡፡ የኦነግ ቃል አቀባይ አቶ ቶሌራ አዳባ ግን የቦርዱን ውሳኔ እንደማይቀበሉት ገልፀው ይግባኝ እንደሚሉ ተናግረዋል፡፡

No comments:

Post a Comment

wanted officials