ከትላንት ጀምሮ በአዲስ አበባ ነዳጅ በመጥፋቱ ከፍተኛ የመኪናዎች ሰልፍ እየታየ ነው፡፡ ለእጥረቱ ምክንያቱ ምን
እንደሆነ የተጠየቁት የሚመለከታቸው ባለስልጣናት እጥረቱ የተከሰተው ህገወጥ የነዳጅ ገበያ በመጨመሩ ነው ብለዋል፡፡
በተለይም ለሪፖርተር ጋዜጣ መግለጫ የሰጡት የኢትዮጵያ ነዳጅ አቅራቢ ድርጅት ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ ታደሰ ኃይለ ማርያም ለእጥረቱ ዋነኛ ምክንያት በሕገወጥ መንገድ ከነዳጅ ማደያዎች ነዳጅ እየተቀዳ በየመንደሩ ስለሚሸጥ ነው ብለዋል፡፡ ይህን ህገ ወጥ የነዳጅ ንግድ ለመቆጣጠር ባለመቻሉ እጥረቱ ከቀን ወደቀን እየተባባሰ መምጣቱን አስረድተዋል፡፡ ‹‹በአሁኑ ወቅት ከማደያዎች ውጪ በተለይ ቤንዚን በኪዮስኮች ጭምር እየተሸጠ ነው›› ያሉት ሃላፊው ይህንን ለመቆጣጠር እየተደረገ ያለ ጥረት የላላ መሆኑ ደግሞ ችግሩን እንዳባባሰው ጠቁመዋል፡፡
ይህ አንዲህ እንዳለ የመስሪያ ቤቱ የህዝብ ግንኙነት ባለሙያ ህገ ወጥ የነዳጅ ሽያጩ የተባባሰው ወደጎረቤት አገራት ስለሚሸጥም ነው ሲሉ ለሸገር ሬዲዮ ተናግረዋል፡፡ ስለዚህም ከጎረቤት አገራት ጋር ያለው የንግድ ግንኙነት ገደብ ሊበጅለት እንደሚገባ የጠቆሙት ህዝብ ግንኙነቱ የትኛው ጎረቤት አገር እንደሆነ አልገለፁም፡፡ ይሁንና ኤርትራን ማለታቸው እንደሆነ ይታመናል፡፡

No comments:
Post a Comment