Which one you first choose? በቅድሚያ የሚፈልጉት

Tuesday, February 12, 2019

"አሁንም የታገቱ ሰዎች አሉ" ብ/ጀኔራል አሳምነዉ ፅጌ

ብ/ጀኔራል አሳምነዉ ፅጌ


በተደጋጋሚ ግጭቶች ከተከሰቱና በሰው ህይወትና በንብረት ላይ ጉዳት ከደረሰ በኋላ የክልሉና የፌደራል መንግሥት የፀጥታ ኃይሎች በአካባቢው እንዲሰማሩ ተደርገዋል።
በተጨማሪም በምዕራብና ማዕከላዊ ጎንደር ውስጥ ባሉ አካባቢዎች ከተፈቀደላቸው አካላት ውጪ የጦር መሳሪያ ይዞ መንቀሳቀስ እንደማይቻል ክልከላ ተጥሏል።
በእነዚህ አካባቢዎች ስላለው የፀጥታ ሁኔታና ተያያዥ ጉዳዮች የአማራ ክልል የሠላምና የህዝብ ደህንነት ግንባታ ቢሮ ሃላፊ ከሆኑት ከብ/ጀኔራል አሳምነዉ ፅጌ ጋር ቆይታ አድርገናል።
ጎንደር፡ የአስቸኳይ ጊዜ ወይስ የመሣሪያ እገዳ?
ቢቢሲ በአሁኑ ሰዓት አጠቃላይ በክልሉ ያለዉ የጥታ ሁኔታ ምን ይመስላል?
ብ/ጀኔራል አሳምነዉ ቀደም ሲል ከነበረዉ አሁን አንጻራዊ ሰላማዊ ነው። ይህም በቀጠናዉ ሰፊ የሆነ የሠራዊትና የፀጥታ አካላት ስምሪት ስለነበረ ነው። ነገር ግን ሙሉ በሙሉ ነገሮች ተስተካክለዋል ማለት አይደለም።
ቢቢሲ፦ ችግሩን ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ መፍታት ያልተቻለበት ምክንያት ምንድን ነው?
ብ/ጀኔራል አሳምነዉ የተነሱ ጥያቄዎች የአገራችን ሕገ መንግሥት በሚፈቅደዉ መሰረት በየደረጃዉ ያሉ አካላት የህዝቡን ስሜትና ፍላጎት መነሻ አድርጎ ተወሰኗል። በህግ በኩል ይሄ ነው የሚቀረው ተብሎ የሚታሰብ ነገር አይደለም።
ከዚህ ዉጭ ግን ይህ ሁኔታ በዚህ መንገድ እንዳይቀጥል የተለየ ፍላጎት ያላቸዉ ወገኖች አሉ። ስለዚህ በዚያ አካባቢ ባለዉ እንቅስቃሴ ላይ የተለያዩ ኃይሎች ፍላጎት ማሳደራቸዉና ግጭት እንዲቀጥል ፍላጎት ብቻ ሳይሆን አጥብቀው እየሰሩበት በመሆኑ እንቅስቃሴው በፈለግነው መንገድና ህዝቡ ይጠቅመኛል ብሎ ባሰበዉ መንገድ ሊቋጭ አልቻለም። አሁን ግን በዚያ መንገድ ለማቀራረብና ችግሩን ለማስተካከል ጥረት እየተደረገ ነዉ።
ቢቢሲችግሩን ከመቆጣጠር አኳያ አሁን ታዲያ ምን ሰራችሁ?
ብ/ጀኔራል አሳምነዉ የቆየ ችግር እንደሆነ ይታወቃል። ህዝባዊ ባይሆንም የሆነ መነሻ አለዉ። ስለዚህ ይህን መነሻ አድርገን እየሰራን ነው። አንደኛ በሁለቱ ህዝቦች መካከል እርቀ ሰላም እንዲወርድ፤ ችግሩ የሁለቱ ህዝቦች እንዳልሆነ በሚያሳይ መንገድ ብቻ ሳይሆን መነሻዉን በግልጽ ለህብረተሰቡ በማሳየት ህብረተሰቡ እንዲሳተፍበት እየተደረገ ነው።
ሁለተኛ ከቀውሱ ማናችንም ተጠቃሚ አይደለንም። እነዚህ ህዝቦች አሁን ብቻ ሳይሆን ወደፊት አብረው የሚቀጥሉ ናቸዉ። በብዙ መንገድ አንድ መሆናቸዉን የሚያሳዩ ቁርኝቶች አሉ።
"የቅማንትን ሕዝብ እንወክላለን የሚሉ ፅንፈኞች ከሌሎች ጋር በቅንጅት እየሰሩ ነው" ጄኔራል አሳምነው
ስለዚህ አካባቢው ላይ የተጠነሰሰ ችግር ሳይሆን የተላከ ፕሮጀክት ስለሆነ ይህን ፕሮጀክት ለማምከን ደግሞ ህዝቡ እንዲገነዘብ እየተደረገ ነው። ይህ ራሱ አንዱ መነሻ ነው። ምክንያቱም ያው ችግሩን ካወቅኸዉ ለመፍትሔውም ተቃረብክ ማለት ነዉ።
ከዚህ ውጪ ለችግሩ መነሻ ናቸዉ በተባሉ ኃይሎችና ለጸጥታ መሰናክል ናቸው በተባሉ ግለሰቦች ላይ ርምጃ ለመውሰድ አስፈላጊው ዝግጅት ተደርጓል። ተጠናክሮም ይቀጥላል። ስለዚህ ህብረተሰቡ ይህንንም ሽምግልናውንም ከራሱ ልምድና ተሞክሮ ያገኘዉን ነገር አጠናክሮና አደራጅቶ ሰላማዊ ሁኔታውን ያመጣዋል ብለን ተስፋ እናደረጋለን። በዚያ መንገድ ደግሞ እየሄድን ነዉ።
ቢቢሲ፦ በምዕራብ ጎንደር ያለው ችግር ወደ ሌሎች የክልሉ አካባቢዎች ሊዛመት ይችላል የሚል ስጋት አለዎት?
ብ/ጀኔራል አሳምነዉ ጎንደር ለአስተዳደራዊ ሁኔታ ተብሎ የተከፈለ ስለሆነ አንድ ቦታ ላይ ያለዉ ስሜት ሌላ ቦታ ይነበባል። አንድ ቦታ ያለው መልካም ነገር ሌላ ቦታ መልካም ነገር ይዞ ይመጣል። ስለዚህ የአንዱ ተጽዕኖ ሌላው ጋ ሊኖር አይችልም ልንል አንችልም። በጋራ አንድ መስመር የሚጠቀሙ ናቸው።
ስለዚህ አንዱ ቦታ በተነሳዉ ግጭት ምክንያት ተንቀሳቅሰው መስራት ካልቻሉ ችግሩ ሌላም ቦታ ተጽዕኖ አሳድሯል ማለት ነው። አሁን ባለው ሁኔታ ግን ተጽዕኖው አይደለምና በሌላው አካባቢ፤ ችግሩ በተከሰተበት ስፍራም እየቀነሰ ስለሆነ ተጽዕኖው የለም ማለት ይቻላል። ህብረተሰቡም ከውድቀቱ እየተማረ ስለመጣ በራሱ ሰላሙን ለማስጠበቅ እየሰራ ነው። ነገር ግን አካባቢውን ማበጣበጥ የሚፈልጉ ኃይሎች አርፈዉ ይቀመጣሉ ብለን አናስብም።
ቢቢሲ፦ እነዚህ ይሎች ግን እነማን ናቸዉ?
ብ/ጀኔራል አሳምነዉ እሱን ሌላ ጊዜ እንነጋገረዋለን። ግን ዞሮ ዞሮ ይሄ አካባቢ ድንበር ነው፤ ታውቀዋለህ አይደል? በአብዛኛው ሱዳን ጋር እንዋሰናለን ሌላም ጋር እንዋሰናለን። አንዳንድ አካባቢዎች የይገባኛል ጥያቄ ከታሪክም ከሌላም በለው እዚህ አካባቢ ችግር እንዲከሰት ያደርጋል።አንዳንድ አካባቢ ደግሞ ይሄ ህዝብ በርካታ ጥያቄዎች ኑረውት በተገቢው መንገድ እንዳያቀርብ ደግሞ አንቅፋት ለመፍጠር የሚፈልጉ ኃይሎች አሉ። ይህን በተደጋጋሚ ተነጋግረንበታል ህዝቡ በራሱ መንገድ ይፈታዋል።
ቢቢሲ፦ ሰሞኑን በተለይ ከጎንደር መተማና ከጎንደር ሁመራ በሚወስዱት መንገዶች ላይ መሳሪያ ይዞ መንቀሳቀስ ተከልክሏል። ከክልከላዉ በላም ግን እገታዎች እንደተፈጸሙ እየተነገረ ነዉ። እዴት ይህን መከላከል አልተቻለም?
ብ/ጀኔራል አሳምነዉ እነዚህ መንገዶች ዓለም አቀፍ መንገዶች ናቸዉ። እነኝህን መንገዶች በራሳችን ፍላጎት መከላከያ በበላይነት ብቻ ሳይሆን በወሳኝነት እንዲቆጣጠራቸው አድርገናል። ሌላውን ሥራ ደግሞ እኛ እንድንሰራ ተደረጓል። ይህም የተልዕኮ ግልጽነት እንዲኖርና በተልዕኮ ላይ አሻሚነትና አወዛጋቢነት እንዳይከሰት ነው።
ከጄኔራሎቹ ሹመት ጀርባ?
ክልከላዉ የተካሄደውም አጠቃላይ እንቅስቃሴውን ሰላማዊ ለማድረግና የሚፈጠሩ እገታዎችን ለመከላከል ታስቦ ነዉ። ይሁን እንጂ ይህ ችግር አልተቀረፈም። ሰሞኑን ሚኒባስ የያዙ ሹፌሮችና ረዳቶች ታግተዋል። ጭልጋ አካባቢም የተወሰነ ችግር ገጥሞናል። ይሄ የቆየና የሚጠበቅ ነዉ አዲስ ነገር አይደለም። መልሰን ለማስተካከል እየሰራን ነው። እነዚህ ብቻ ሳይሆኑ ሌሎችም የምንጠብቃቸው ችግሮች አሉ።
ቢቢሲ፦ የታገቱት ሰዎችስ የት እንደደረሱ ይታቃል?
ብ/ጀኔራል አሳምነዉ ይገኙበታን የተባሉበትን ቦታ መለየት ተችሏል። አንዳንዶቹን የመከላከያ ሠራዊት ደረሶ እርምጃ በመውሰድ ወደ ቤተሰቦቻቸዉ እንዲቀላቀሉ ተደርጓል። አንዳንዶቹን ደግሞ ፍለጋና ክትትል ላይ ናቸው።
ቢቢሲ፦ ካሁን በፊት ወታደራዊ ስልጠና የሚሰጥባቸዉ ቦታዎች መገኘታቸዉን ገልጸዉ ነበር። እነዚህ ቦታዎች አሁንም በእናንተ ቁጥጥር ስር ናቸው?
ብ/ጀኔራል አሳምነዉ ይህ የአደባባይ ሚስጢር ነው። አሁን ግን መንግሥት እየተቆጣጠረው ነው። የአካባቢው መልክዐ ምድር አስቸጋሪ ነው። አንዱን ስተቆጣጠረው ሌላ ቦታ ሊከሰት ይችላል። ስለዚህ ይሔ እስካሁን የቀጠለበት ሁኔታ ነው ያለው። ይህ ደግሞ በእንዲህ አይነት መልክዐ ምድር የሚያጋጥም ነው። ካሁን በፊት የነበሩትን ተቆጣጥረናል። ነገር ግን ሌሎች አካባቢዎች እስካሁን አሉ። በአብዛኛው ከሱዳን ድንበር ጋር ተያይዞ የቆየ ባህልም ስላለ እሱን ተጠቅሞ የመንቀሳቀስ ነገር አለ እንጅ፤ በአብዛኛው የጎንደር አካባቢ ጠንካራ ይዞታ የላቸውም።
ቢቢሲ በክልሉ በተለይ አሁን ችግሩ በሚነሳባቸዉ አካባቢዎች በተለያየ ጊዜ የግልም ሆነ የቡድን መሳሪያ በተደጋጋሚ በግለሰቦች እጅ ይያዛል፤ ወደ ሌላ አካባቢ ሲንቀሳቀስም በቁጥጥር ስር እንደሚውሉ ይነገራል። ለመሆኑ የእነዚህ መሳሪያዎች ምንጭ ከየት እንደሆነ ይታወቃል?
መከላከያ የኢህአዴግ የመጨረሻ ምሽግ?
ብ/ጀኔራል አሳምነዉ፦ አናቅም ይህንን ነገር።
ቢቢሲ፦ ስለዚህ ክልሉ ስጥ ከገቡ በኋላ ነ ማለት ነ መረጃ የሚደርሳችሁ?
ብ/ጀኔራል አሳምነዉ እውነት ነዉ።
ቢቢሲሕገወጥ የመሳሪያ ዝውወውሩን ከምንጩ ለማድረቅና ምንጩን ከመፈለግ አንጻርስ ምን ሰርታችኋል?
ብ/ጀኔራል አሳምነዉ በእሱ ላይም እየሰራን ነው።
ቢቢሲ፦ በክልሉ በተከሰተ ግጭት ምክያት የተፈናቀሉ ሰዎች ወደ ቀያቸው እንዲመለሱ እየተሰራ ያለ ራ አለ?
ብ/ጀኔራል አሳምነዉ ከሰላም ማስከበሩ በተጓዳኝነት እየተሰራ ያለዉ ሥራ አንዱ እሱ ነው። ህብረተሰቡ የማሳ ዝግጅቱ ጊዜ ሳያልፍበት ወደ አካባቢዉ እንዲመለስ ይፈለጋል። አሁን የሰፈሩትም በቅርብ ርቀት ነው። ግን ደግሞ የጸጥታ ዋስትና እንዲኖራቸዉ ይፈልጋሉ፤ ይህንን እየሰራን ነዉ። በቅርቡ አብዛኛዉ ይመለሳል።
ቢቢሲበመጨረሻ የሚሉት ነገር ካለ?
ብ/ጀኔራል አሳምነዉ የአንድ አካባቢ ችግርና ቀውስ የሃገርም ችግር የሃገርም ቀውስ ተደርጎ መወሰድ አለበት። የትኛዉም አካባቢ የሚደርስ የዜጎች መፈናቀል ሁላችንንም አንገት ሊያሰደፋን ካልሆነ በስተቀር አንዱ የሚጠቀምበት ሌላዉ የሚጎዳበት ተደርጎ መወሰድ የለበትም።
በተለይ በሰለጠነዉ በዚህ በ21ኛዉ ክፍለ ዘመን በጎሳና በዘር ላይ የተመሰረተ ፖለቲካና እጅግ ኋላ ቀር በሆነ አካሄድ ብዙዎቻችን እየተጎዳን እንገኛለን፣ አገሪቱም እየተጎዳች ትገኛለች፣ አካባቢያችንም በዚህ ዙሪያ እየታመሰ ይገኛል።
ስለዚህ በዚህ አይነት ምስቅልቅልና የፖለቲካ ኪሳራ መጨረሻ ላይ ሁላችንም ተጎጂዎች እንጅ ተጠቃሚዎች አንሆንም። የተለያዩ የሃገራችን ምሁራን የተሳተፉበት ተቋማት፣ የሀገራችን ታላላቅ ሰዎች፣ የቢዝነስ ሰዎች፣ ሁላችንም ያገባናል የምንል ሁሉ በዚህ ጉዳይ ላይ አጽንኦት ሰጥተን እንድንመክርበት በዚህ አጋጣሚ ማሳሰብ እንፈልጋለን።
ይሄ ሁኔታ መቀየሩ አይቀርም፤ ግን ደግሞ ታሪካችንን ሳያበላሽ መቀየሩ ሁላችንንም ይጠቅማል። በዚህ መልኩ ለሚሳተፉም ፈጣሪ ልቦና እንዲሰጣቸዉ፣ ሌሎች ደግሞ በመልካም ሁኔታ ላይ እንዲንቀሳቀሱ፣ ሁላችንም እንድንረዳዳ በዚህ አጋጣሚ ጥሪዬን ለማስተላለፍ እወዳለሁ።

No comments:

Post a Comment

wanted officials