Which one you first choose? በቅድሚያ የሚፈልጉት

Tuesday, April 7, 2015

በአለማቀፍ ድርጅቶች እርዳታ ከአንድ መቶ በላይ ኢትዮጵያውያን ከየመን ወደ አገራቸው ተመለሱ

በአለማቀፍ ድርጅቶች እርዳታ ከአንድ መቶ በላይ ኢትዮጵያውያን ከየመን ወደ አገራቸው ተመለሱ

መጋቢት ፳፱(ሃያ ዘጠኝ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-አለማቀፉ የስደተኞች ድርጅት _IOM ባወጣው ዘገባ ህይወታቸው በአደገኛ ሁኔታ ውስጥ የነበሩ 131 ኢትዮጵያውያንን ከጅቡቲ ወደ አገራቸው መልሷቸዋል።
ከተመላሾቹ መካከል 100 ያህሉ ኢትዮጵያውያ ወደ የመን ለመጓዝ በዝግጅት ላይ እንደነበሩ ድርጅቱ አስታውቋል። 28 ኢትዮጵያውያን ደግሞ ከየመን ወደ ጅቡቲ በባህር ላይ ጉዞ አድርገው የደረሱ ናቸው።
በሰላም ወደ አገራቸው ከተመሰሉት መካከል አንድ እርጉዝ ሴት እና 37 ወላጅ አልባ ታዳጊዎች እንደሚገኙበት ድርጅቱ ገልጿል።
አይ ኦ ኤም በብዙ ሺ የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያን በየመን በሚካሄደው ጦርነት የተነሳ መውጫ አጥተው እየተሰቃዩ ነው  ብሏል። ከተለያዩ መንግስታት የቀረቡለትን ጥያቄዎች ግምት ውስጥ በማስገባት ድርጅቱ 11 ሺ የሚሆኑ የውጭ አገር ዜጎችን ከየመን ለማውጣት
እንቅስቃሴ እንደሚጀምርም አስታውቋል። አንዳንድ አገሮች በየመን ላይ ያየር ጥቃት ከምትፈጽመዋ ሳውዲ አረቢያ ፈቃድ እየጠየቁ ለተወሰኑ ሰአታት አውሮፕላን እየላኩ ዜጎቻቸውን ለማስወጣት ችለዋል።
የኢህአዴግ መንግስት ኢትዮጵያውያኑን የማስወጣቱን ሃላፊነት ለአይ ኦ ኤም ሳይሰጥ እንዳልቀረ ምረጃዎች ያመለክታሉ።
የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ቴዎድሮስ አድሃኖም በቻይና የባህር ሃይል ሰራተኞች ድጋፍ ወደ አገራቸው የገቡ 30 ሰዎችን ” የመጀመሪያው ዙር ስደተኞች ወደ አገራቸው ገብተዋል” ብለው ከሳምንት በፊት ቢያስታውቁም፣ ከዚያ በሁዋላ መስሪያ ቤታቸው ያለው ነገር የለም።

አንዲት ወጣት አይነስውር ድልድዩን ስትሻገር ገደል ውስጥ ገብታ ህይወቷ አልፏ

“ቀጨኔ መደሀኒዓለም አካባቢ ያለ ድልድይ ለዓይነስውራን ሞት ምክንያት እየሆነ መምጣቱን ሸገር ሬዲዮ ዘገበ።

መጋቢት ፳፱(ሃያ ዘጠኝ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-እንድ ራዲዮው ዘገባ  ትናንትና አንዲት ወጣት አይነስውር ድልድዩን ስትሻገር ገደል ውስጥ ገብታ ህይወቷ አልፏል። 
ይህ  ቀጭኔ መድህኒ ዓለም አካባቢ ያለው ድልድይ በቀኝና በግራ በኩል አደጋ መከላከያ ድጋፍ የሌለው በመኾኑ ለሰዎች መጥፋት ምክንያት እየሆነ መምወጣቱን የ አካባቢው ነዋሪዎች ተናግረዋል። አካል ጉዳተኞችን ለአደጋ የሚያጋልጡ ከደረጃ በታች የሆኑ ድልድዮች  በከተማው የተለያዩ ቦታዎች በብዛት  እንደሚገኙ ይታወቃል።
ድልድዮቹን በባለቤትነት ወስዶ ያስራው የመንገዶች ባለስልጣንም ሆነ የክፍለ ከተማው መስተዳድር በጉዳዩ ዙሪያ እስካሁን ያሉት ነገር የለም።  በኢትዮጵያ 1.2ሚሊዮን ዓይነስውራን  የሚኖሩ ሲሆን፤ ከአዲስ አበባ ነዋሪዎች ደግሞ 1ነጥብ 4 በመቶ ያህሉ ያህሉ
ዓይነስውራን መሆናቸውን መረጃዎች ያሳያሉ
Image result for blind girl in ethiopia

Civic organizations are forced to fed the ruling Political party ideology

የኢትዮጵያ የበጎ አድራጎት ድርጅቶችና ማህበራት ኤጀንሲ የኢህአዴግን ርዕዮተ-ዓለም በግዳጅ ለሀገር በቀል የሲቪል ሶሳይቲ ከፍተኛ የሥራ መሪዎች በመስጠት ላይ መሆኑ ተሰማ

መጋቢት ፳፰(ሃያ ስምንት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ኤጀንሲው በአዳማ ስብስባ እንደሚያካሂድና አንድ የድርጅቱ ከፍተኛ የሥራ መሪ እንዲገኝ በስልክ በተነገራቸው መሠረት በአዳማ መገኘታቸውን የተናገሩት አንድ የስብሰባው ተሳታፊ ፣ በዚህ ስብሰባ ላይ ምግባረሰናይ ድርጅቶችን አላሰራ ባሉት ሕጎችና አሰራሮች ዙሪያ ምክክር ይደረጋል የሚል ሃሳብ ይዘው በቦታው ቢገኙም የገጠማቸው ግን ፈጽሞ ያላሰቡት መሆኑን ተናግረዋል፡፡
በዚሁ ስብሰባ ላይ ስለሕገመንግስቱ ማለትም የፌዴራል ስርዓት ጠቀሜታ፣ ስለሰብዓዊና ዴሞክራሲዊ መብቶች መከበር፣ ስለብዝሃነት እንዲሁም መንግስትና ሃይማኖት ስለመለያየታቸውና ስለሃይማኖት አክራሪነት ጉዳዮች፣ ስለልማታዊ ዴሞክራሲያዊ መስመር፣ስለኪራይ ሰብሳቢነት፣ ስለኒዮሊበራል ሃይላት ኪሳራና የመሳሰሉ የፖለቲካ ትምህርት በአስገዳጅ መልኩ እንዲወስዱ የተደረገ ሲሆን በጉዳዩ ላይ በቡድን እንዲወያዩና ሃሳባቸውንም በቡድን መሪያቸው በኩል እንዲያቀርቡ መደረጉን አስረድተዋል፡፡
የስብሰባው ተሳታፊዎች በሁኔታው ብዙዎቹ ቢበሳጩም በኤጀንሲው የፖለቲካ ሹመኞች ላለመጠመድ ሲሉ በስብሰባው ለመቆየት መገደዳቸውን አስታውቀዋል፡፡ «የእነሱ ምርጫ በመድረሱ ብቻ ስንት ሥራ ጥለን የሰለቸ ፖለቲካቸውን ስንጋት ለሶስት ቀናት መቆየታችን እጅግ አበሳጭቶኛል» ብለዋል የስብስባው ተሳታፊ ምንጫችን፡፡
ኤጀንሲው ስብሰባ ሲጠራ በምን አጀንዳ ላይ ውይይት እንደሚደረግ በደብዳቤ መግለጽ የነበረበት ሲሆን ምናልባት ሰዎች ላይገኙ ይችላሉ በሚል ነገሩን ሚስጢር ሳያደርገው እንዳልቀረ ስብሰባውን የተከታተሉት ምንጫችን አስተያየታቸውን ሰጥተዋል፡፡ኢህአዴግ በምርጫ 97 አስከፊ ሽንፈትን ከቀመሰ በሃላ በድንጋጤ ካወጣቸው አሳሪ ሕጎች አንዱ የሆነው የበጎ አድራጎት ድርጅቶችና ማኅበራት አዋጅ ቁጥር 621/2001 በሀገር ውስጥና በውጪ ሀገር ድርጅቶችና መንግስታት ተቃውሞ ሲገጥመው የቆየና ለበርካታ ድርጅቶችና መፍረስና መዳከም መንስኤ በመሆኑ በዚህ አዋጅ ላይ አንዳች ማሻሻያ ይኖራል የሚል ተስፋ አድርገው የነበረ ቢሆንም በተቃራኒው ሕጉ የተቀደሰ እንዲሁም «የኒዮሊበራል ሃይላትን ያበሳጨ» መሆኑ ተነግሮአቸው መመለሳቸውን እንዳሳዘናቸው አስታውቀዋል፡፡ ኤጀንሲው በሁለት ዙር ከመጋቢት 24 እስከ 30/ 2007 ዓ.ም በአዳማ በጠራው ስብሰባ ላይ የተገኙ የኢትዮጵያዊያን ነዋሪዎች በጎ አድራጎት ድርጅቶችና ማህበራት የስራ መሪዎች ፣ በዚህ ስብሰባ ለምን እንዲሳተፉ እንደተፈለገ ግራ ቢገባቸውም ሕገመንግስቱ የወረቀት ነብር ከመሆን በዘለለ አፈጻጸም ላይ ከፍተኛ ችግር መኖሩን በግልጽ አስቀምጠዋል፡፡
በተለይ ሙስና እና የመልካም አስተዳደር ችግሮች ከጊዜ ወደጊዜ እየተባባሱ መምጣታቸውን የጠቀሱት እነዚሁ ተወያዮች ከፍተኛ የሀገሪቱ ባለስልጣናት ከችግሩ ጸድተው አርአያ መሆን ስላልቻሉ ከታች ያለውን ሙስናና የኪራይ ሰብሳቢነት እንዲሁም የመልካም አስተዳደር ችግሮች እንዲቀረፉ ማድረግ እንዳልቻሉና በአሁኑ ወቅት ሀገሪቱ በአሳሳቢ ሁኔታ ላይ እንደምትገኝ አስቀምጠዋል፡፡
ልማትን በተመለከተ በገዥው ፓርቲ ብዙ እንደሚነገርለት ነገር ግን ልማቱ በሰዎች ሕይወት የማይገለጽና  ሰብዓዊ ልማትን ያላካተተ መሆኑን፣ የመንገዶችና የህንጻዎች መሰራት ብቻውን ፋይዳ እንደሌለው ተወያዮቹ ማንሳታቸውን ጉባኤውን የተከታተሉት ምንጫችን ጠቁመዋል፡፡ በኢትዮጵያ ሰብዓዊና ዴሞክራሲያዊ መብቶች ጥሰት መኖሩ፣ የሰብዓዊና የዴሞክራሲያዊ መብቶች ባልተከበሩበት ማህበረሰብ ውስጥ ደግሞ ሀገራዊ መግባባት ፈጥሮ በልማት ጉዳይ አንድ አቋም ለመያዝ እንደማይቻል መነገሩን ጠቅሰዋል፡፡
መንግስትና ሃይማኖት የተለያዩ መሆናቸውንና አንዱ በአንዱ ጣልቃ እንደማገባ ሕገመንግስቱ ቢደነግግም መንግስት ግን ሁሉን ለመቆጣጠር ካለው ፍላጎት የተነሳ የመብት ጥያቄ በማንሳታቸው ሲደራደራቸው የነበሩትን የሙስሊም ወገኖች «አክራሪ» የሚል ታፔላ ተለጥፎላቸው ዘብጥያ መወርወራቸው የመንግስትን ግልጽ ጣልቃ ገብነትና ሕገመንግስታዊ ጥሰት በግልጽ ያሳየ ነው ሲሉ አስረድተዋል፡፡ ገዥው ፓርቲ እና ተቃዋሚዎች አሁንም በጠላትነት መንፈስ እንደሚተያዩና በምንም ጉዳይ የጋራ መግባባት መፍጠር እንዳልቻሉም የተነሳ ሲሆን ለዚህ ኪሳራ ደግሞ ትልቁን ሃላፊነት የሚወስደው በመንግስትነት 24 ዓመታት የዘለቀው ገዥው ፓርቲ ነው ብለዋል፡፡ ከ200 በላይ ሀገር በቀል የሲቪል ሶሳይቲ አባላት የተገኙበት ሁለተኛው ዙር ስብሰባ እስከመጋቢት 30 ቀን 2007 ዓ.ም እንደሚቀጥል ታውቋል፡፡ በተመሳሳይ ዜና በቅርቡ ሲሲአርዴ የተባለው መንግስታዊ ያልሆነ ድርጅት በቅርቡ ባደረገው ጠቅላላ ጉባኤ ላይ በክብር እንግድነት  የተገኙት አቶ  አባዱላ ገመዳ መንግስት ለበጎ አድራጎት ድርጅቶች ቀና አመለካከት እንዳለው ገልጸዋል።  ከገለጻቸው በሁዋላ የማሪ
ስቶፕስ አማካሪ የሆኑት አቶ ጌታቸው በቀለ ” እርስዎ መንግስትና በጎ አድራጎት ማህበራቱ በጋራ እንደሚሰሩ ፣ የበጎ አድራጎት ማህበራት ህግ ከጊዜ ወደ ጊዜ እንደ አስፈላጊነቱ ማስተካከያ እና ማሻሻያ እየተደረገ መሆኑን ይገልጻሉ፣ ነገር ግን ጠ/ሚኒስትሩ የሚናገሩት እርስዎ ያሉትን የሚንድ ነው፣ የምትናገሩት የግላችሁን አቋም ሳይሆን የመንግስት አቋምን ይመስለኛል።እንዴት ነው የመንግስት ባለስጣናት ሆናችሁ ሁለት የተለያዩ ነገሮችን የምትናገሩት?” በማለት ጠይቀዋል። በእንግሊዝኛ  በተዘጋጀው ውይይት ላይ ንግግራቸውን በአማርኛ ያቀረቡት አባ ዱላ ገመዳ፣ አማርኛ ፣ ኦሮምኛ ፣ ትግርኛና እንግሊዝኛ እንደሚናገሩ ይሁን እንጅ በቋንቋቸው መናገራቸው ስለሚያስደስታቸው በአማርኛ ለመናገር መምረጣቸውን ለተነሳው ጥያቄ መልስ ሰጥተዋል።
አቶ አባዱላ ”  ብዙ ችግሮችን የሚፈጥሩ አምነስቲ፣ ሂውማን ራይትስ ወች የሚባሉት ድርጅቶች በእኛና በሩዋንዳ ላይ የማይሉት ነገር የለም። እኛ የትልልቆቹ አገራት ፍላጎት ማስፈጸሚያ አንሆንም ስንል የማይሉት ነገር የለም። እነሱ መንግስት መሆን ስለሚፈልጉ ነው። እኛ ራሳችንን ከቻልን ብዙ ስራ የሚያጣ ብዙ ቢሮ የሚዘጋበት አለ። ጠ/ሚኒስትሩ የእነሱ አላማ አስፈጻሚ አትሁኑ ነው ብለው የመከሩት። አንድ መቶ ሚሊዮን ዶላር ለዚች አገር ምንም አይደለም። ከዚህ የተሻለ ደረጃ ላይ ያለች አገር ነው ያለችን። እናም የእነሱ አላማ ማስፈጸሚያ እንዳትሆኑ ተጠንቀቁ ” ሲሉ በበጎ አድራጎት ላይ የተሰማሩትን አስጠንቅቀዋል።

በአዲስ አበባ ከተማ ዉስጥ ማንኛዉም አዲስ የእምነት ተቋም እንዳይገነባ መመርያ ወጣ


  • 2536
     
    Share
አቡበከር አህመድ እንደዘገበው:-
መንግስት በሴኩላሪዝም ስም ህብረተሰቡን በተለይ ሙስሊሙን ማህበረሰብ ከእምነቱ ለማስወጣት የሚያደርጋቸውን ጥረቶች አጠናከሮ የቀጠለ ሲሆን የዚህ እቅድ አንደ አካል የሆነውን ድርጊቱን ማንኛዉም አይነት የእምነት አዲስ ተቋማት በአዲስ አበባ ከተማ ዉስጥ እንዳይገነቡ በሚል መመሪያ ማዉጣቱን ምንጮች አስታዉቀዋል።
Ethiopia-Addis-Ababa-2
በየትኛዉ እምነት አማኞች ፈጣሪያቸውን በአንድነት የሚያመልኩበት ቦታና የእምነቶቻቸውን ጥሪ የሚያደርጉበት ቦታ የእምነት የእምነት ተቋማቸዉ ሆኖ እያለ ከተማዋ እጅጉን እያሰፋችበት በሚገኘው በዚህ ወቅት ላይ ይህ አይነቱ ወሳኔ መተላለፉ መንግስት ህብረተሰቡን ከእምነቱ ለማራቅ ያለውን ፍላጎት የሚያሳይ ነው ተብሎ እየተተቸ ነው::
ዉሳኔው ሌላ መመሪያ እስኪመጣ ድረስ እንዲሰራበት የተላለፈ ሲሆን በአሁኑ ወቅትም በቅርቡ በተለያዩ እምነቶች ለእምነት ተቋም መገንቢያ ተብለው የተከለሉ ቦታዎችን መንጠቅ እንደተጀመረም ምንጮች አካተዉ ገልፀዋል።

የኢትዮጵያ አማጺያን በደቡብ ሱዳን ተቃዋሚዎች የቀረበባቸውን ክስ አጣጣሉ

የኢትዮጵያ አማጺያን በደቡብ ሱዳን ተቃዋሚዎች የቀረበባቸውን ክስ አጣጣሉ



የኢትዮጵያ መንግስትን በጦር ሀይል ለመጣል ሚታገሉት “የኢትዮጵያ የተባበሩት አርበኞች ግንባር” በደቡብ ሱዳን ግጭት ውስጥ ከፕሬዘዳንት ሳልቫኪር ሀይል ጎን ተሰልፎ የተቃዋሚውን የሪክ ማቻርን ሀይሎች ይወጋል በሚል የቀረበባቸውን ክስ ውድቅ አደረጉ.
በሪክ ማቻር የሚመሩት የደቡብ ሱዳን ተቃዋሚዎች በቅርቡ እንዳስታወቁት ከሆነ በምእራብ ኢትዮጵያ ጋምቤላ ክልል ሚንቀሳቀሰውና በቀድሞው የአካባቢው አስተዳዳሪ በሆኑት በቶዋት ፓልቻይ የሚመራው የኢትዮጵያ አርበኞች ግንባር ኢትዮጵያን ለመውጋት በደቡብ ሱዳን መን ግስት ስልጠና ይሰጠዋል የመሳሪያና የቴክኒክ ድጋፍ ይደረግለታል የሚል ክስ ሲያቀርቡበት ቆይተዋል.
ቡድኑ ከዚህ በተጨማሪም በደቡብ ሱዳን ግጭት ውስጥ ራሱን አስገብቶ ከሳልቫኪር ሀይል ጋር በመወገን እኛን በጦር ይወጋል ሲሉም አማጺያኑ ጨምረው ይከሳሉ.
ይህን ተከትሎ ከኢትዮጵያ መንግስት በኩል የተሰጠ አስተያየት አለመኖሩን የገለጸው ሱዳን ትሪብዩን የወሬ ምንጭ የአርበኞች ግንባሩ ሀላፊ ቶዋት ፓልቻይ በሰጡት ምላሽ የተባለው ክስ መሰረተ ቢስ እንደሆነ ተናግረዋል ሲል ዘግቧል.
ቶዋት ፓልቻይ ለሱዳን ትሪብዩን በላኩት ደብዳቤ እንዳረጋገጡት ከሆነ ቡድናቸው በተጠለለበት ሀገር የውስጥ ጉዳይ ምንም አይነት ጣልቃ ገብነት እንደማያደርግና የተባለው በሙሉ ተራ ፕሮፓጋንዳ መሆኑን ነው የተናገሩት
ትርጉም አሰግድ ታመነ
Read More at Sudan Tribune

Sunday, April 5, 2015

ወቅቱ የተግባራዊ ትግል ነው!አርበኖች ግንቦት 7

pg7-logoለገዛ ራሱ፣ ለኢትዮጵያ ሕዝብ እና ለኢትዮጵያ ቅን የሚመኝ እያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ ዜጋ ህወሓትን ለማስወገድ ተግባራዊ ትግል ውስጥ መሳተፍ የሚኖርበት ወቅት ላይ እንገኛለን። በዚህ ወሳኝ ወቅት ከዳር ሆኖ መታዘብ ዘረኛውን፣ አምባገነኑን፣ ፋሽስቱን ህወሓት እንደመደገፍ ይቆጠራል።
ዛሬ እያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ ህሊናውና አቅሙ በሚፈቅድለት የትግል ዘርፍ የመሰማራት ሰፊ እድል ተፈጥሮለታል። በዚህም መሠረት የህወሓትን አፈና በጠነከረ ክንድ ለመመከት የቆረጡ ኢትዮጵያዊያን ወደ በረሃዎችና ተራራዎች አቅንተዋል። ብዙዎች በመንገዱ ላይ ያሉ ጋሬጣዎችን ተቋቁመው እየተቀላቀሏቸው ነው። በደል የመረራቸው ሌሎች በርካታ ኢትዮጵያዊያን በተለያዩ የኢትዮጵያ ክልሎች በቡድን ለነፃነታቸው ዘብ ቆመው በህወሓትና አገልጋዮቹ ላይ እርምጃ መውሰድ ጀምረዋል። ይህ የሚበረታታ እና ተቀናጅቶ ሊጠናከር የሚገባው ጉዳይ ነው።
አሁን ያለንበት ጊዜ ልዩ የትግል ወቅት ነው። ትናንት በከተሞች ይካሄድ የነበረው ፀረ ወያኔ ትግል ዓይነተኛ መታወቂያው ሕዝባዊ ተቃውሞ ነበር። ዛሬ ግን ይህ ሁኔታ ተቀይሯል። በተለይ በአገዛዙ ፈቃድ የሚደረጉ ተቃውሞዎች ፋይዳ ቢስ ሆነዋል። በአገዛዙ ፈቃድ በሚደረጉ ተቃውሞዎች ለውጥ እንደማይመጣ የኢትዮጵያ ሕዝብ በማያሻማ ሁኔታ ተረድቷል። ስለሆነም ትግሉ ወደ ሕዝባዊ እምቢተኝነት አድጓል።
ዛሬ ከዚህ በፊት ያልተሞከሩ የትግል ስልቶች ተግባራዊ እየሆኑ ነው። በዚህ ረገድ የሙስሊም ኢትዮጵያዊያን የተቀናጁ ርምጃዎች በአርዓያነት የሚጠቀሱና የሁሉም ኢትዮጵያዊያን ድጋፍ የሚሹ ናቸው። እነዚህ የሕዝባዊ እምቢተኝነት ተግባራት የእምነት አጥር ሳይለያየን ፍትህ የተጠማን ዜጎች ሁሉ ልንተገብራቸው የሚገቡ ናቸው።
ለምሳሌ፣ ተንቀሳቃሽ ስልኮችን በተወሰኑ ቀናት መዝጋት በተቀናጀ ሁኔታ ከተደረገ ከፍተኛ ውጤት ሊያመጣ የሚችል፤ በሙስሊም ወገኖቻችን ግንባር ቀደም መሪነትና አስተባባሪነት ተሞክሮ በኢትዮጵያ ተጨባጭ ሁኔታ ተግባራዊ ሊደረግ የሚችል መሆኑ የታየ አንድ የትግል ስልት ነው።
በአሁኑ ወቅት ተግባራዊ በመደረግ ላይ ያለው ሣንቲሞችን የመሰብሰብ ዘመቻም ሌላ ከዚህ በፊት ያልተሞከረ፤ በተጨማሪ እርምጃዎች ከታገዘ ህወሓት መራሹ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ የሀገሪቱን ገንዘብ መቆጣጠር የማይችልበት ደረጃ ላይ ሊያደርስ የሚችል ጉልበት ያለው ስልት ነው። ውሳኔው ሣንቲሞችን ብቻ ሳይሆን የወረቀት ኖቶችንም ሲያካትት በዝውውር ላይ የሚኖረውን ገንዘብ ብዛት የሚቆጣጠረው ህወሓት ሳይሆን በደል ያንገሸገሸው ሕዝብ ይሆናል። በባንኮች ያለ ተቀማጭ ገንዘብ በማውጣትም የህወሓት የፋይናንስ ተቋማትን ማሽመድመድ ሌላ ተግባራዊ ሊደረግ የሚችል ስልት ነው። በእነዚህ እርምጃዎች የተለማመደ ሕዝብም ወደ ግዢ እቀባ፤ ለተወሰኑ ቀናት ከቤት አለመውጣት ብሎም “ግብር አልከፍልም” ወደማለት ሊሸጋገር ይችላል።
እንዲህ ዓይነቱ ስልቶች ውጤታማ እንዲሆኑ ግን የመላው ሕዝብ ተሳትፎ እና የተቀናጀ አሠራርን ይፈልጋል። ለምሳሌ፣ ሰብስቡ ሲባል መሰብሰብን፤ በትኑ ሲባል መበተን ይጠይቃል። እንዲህ ዓይነት የተቀናጁ የጋራ እርምጃዎች በአምባገኑ የህወሓት አገዛዝ ላይ ከሚያደርሱት ጥቃት በተጨማሪ በኢትዮጵያዊያን መካከል ያለውን መግባባት ያጠናክራሉ። እንዲህ ዓይነት የተቀናጁ የጋራ እርምጃዎች በማኅበረሰብ ቡድኖች መካከል አዎንታዊ መስተጋብር ለመፍጠር የሚኖራቸው ሚና ከፍተኛ ነው።
አሁን አገራችን የምትገኝበት ሁኔታ በጥሞና ሲጤን የኢትዮጵያ ሕዝብ ሳይነጋገር መግባባት፣ እርስ በርሱ መናበብ የሚችልበት ደረጃ ላይ እየደረሰ መሆኑ መረዳት ይቻላል። ይህ ስነልቦናዊ ዝግጅት ደረጃ በደረጃ ጠንከር ያሉ እርምጃዎችን ለመውሰድ ያዘጋጀናል።
በማናቸውም የጋራ እርምጃዎች ለግል ጥቅሞቻቸው ቅድሚያ የሚሰጡ፤ ራሳቸው “ብልጥ” አድርገው በማየት በተፈጠረው ሁኔታ መጠቀም የሚፈልጉ፤ በሌላው ድካም ለማትረፍ የሚሯሯጡ ሰዎች መኖራቸው የማይቀር ነው። ህወሓት ለሃያ አራት ዓመታት ኮትኩቶ ያሳደገው የአድርባይነት ባህልም ሌላው እንቅፋት ሊሆን እንደሚችል መገመት ቀላል ነው። ድህነት ደግሞ በገዢዎች ላይ ጨክነን የመነሳት አቅማችንን እንደሚያዳክም የታወቀ ነው። ሆኖም ግን የኢትዮጵያ ሕዝብ ከፊቱ የቀረበለት ምርጫ “ባርነት ወይስ ነፃነት” መሆኑን የተገነዘበበት ጊዜ ላይ ደርሰናል።
በዚህም ምክንያት ለህወሓት ባርነት ከመገዛት ነፃነትን የሚመርጥ ዜጋ ሁሉ ዋጋ ለመክፈል መዘጋጀት ይኖርበታል። ለሁላችንም የሚሆን የትግል ዘርፍ መኖሩ የሕዝቡን ተሳትፎ ከፍ ያደርገዋል። የሁለገብ ትግል ስትራቴጂ ጥቅሙም እዚህ ላይ ነው። ማንም የማንም ነፃ አውጭ አይደለም። ሁላችንም ተባብረን ሁላችንንም ነፃ እናወጣለን።
አርበኖች ግንቦት 7፡ የአንድነትና የዲሞክራሲ ንቅናቄ “ትግላችን ዘርፈ ብዙ ነው፤ ተግባራዊ ትግል የሚደረገውን በሁሉም ቦታዎች ነው፤ እርጃዎቻችን እናቀናጅ፤ ወቅቱ የተግባራዊ ትግል ነው” ይላል።
ድል ለኢትዮጵያ ሕዝብ!

Saturday, April 4, 2015

የኢትዮጵያ አየር መንገድ በንብ መንጋ ተሸብሮ ዋለ


በንብ መንጋ የኢትዮጵያ አየር መንጋ ሲታመስ እንደዋለ የዜና ምንጮች ገለጹ፡፡ በነበረው የንብ መንጋ 5 ሰዎች ለከፍተኛ ጉዳት ተዳርገው በሃያት ሆስፒታል እርዳታ እየተደረገላቸው ሲሆን በአብዛኛው እዛው የመጀመሪያ እርዳታ ተደርጎላቸዋል፡፡ ብዙሃኑ የመተንፈሻ እክል አጋጥሞቸው የመተንፈሻ ኦክሲጅን ተገጥሞላቸው ነበር፡፡መነሻው እዛው አየር መንገዱ አካባቢ ካለው ቱቦ ይሆናል በማለት ጉዳዩ የሚመለከታቸው የአር መንገዱ ሰራተኛ ገልጸዋል፡፡
እንደኔ አስተያየት ከሆነ በኢንጂነር ይልቃል አላግባብ የሆነ የጉዞ እገዳ ምክንያት ቁጣቸውን ለመግለጽ አምላክ የላካቸው መልክተኞች ይሆናሉ ብዬ እገምታለው እንካን የኢትዮጵያ ህዝብ ግፍ የደረሰበት ቀርቶ በወያኔ ላይ እንስሳት እንካን የግፍ አገዛዝ በቃ በማለት ቁጣቸውን በዛሬው እለት አሳይተዋል ፡፡ 




 የናንተን አስተያየት ደግሞ አክሉበት

ህወሃት መሪ ያጣ ድርጅት ነው። Abebe Gellaw


914e2-tplf_failing

ህወሃት መሪ ያጣ ድርጅት ነው። እኔ ለህወሃቶች የምመኝላቸው፣ እውነተኛ እራእይ ያለው መሪ እንዲያገኙ ነው።
ለነገ ሳይስቡ ዛሬ ሆድን በኪሳራ ከሞምላት፣ እራስን ከማወደስ፣ ሌሎችን ከማኮሰስ፣ አፈናቅሎ ከመውረስ፣ አምታቶ ከመዝረፍ፣ በሃሰት ከመክሰስ፣ ህዝብን ፈርቶ ከመኖር፣ በደካማ ዜጎች ስቃይ ከመደሰት፣ በዘርና በጎጥ ከመከፋፈል፣ በባዶው ከመጎረር፣ የሃሰት ክብርና ዲግሪ ከጥቁር ገበያ በርካሹ ከመሰብሰብ፣ ጥራት የሌላቸው የሰው አሻንጉሊቶች ከመሰብሰብ የሚያድን መሪ ያስፈልጋቸዋል።
ህወሃቶች ቆራጥ መሪ ሲያገኙ የትናንቱ ስህተታቸው ሁሉ ፍንትው ብሎ ይታያቸዋል። የበደሉትን ሁሉ ይቅርታ ይለምናሉ። አገር ማለት ሁሉም ያልአድርኦ በዜግነቱ ተከብሮ ከማንም ሳይበልጥ ከማንም ሳያንስ ሊኖርበት የሚገባው ምድር መሆኑ ይገለጥላቸዋል። ህወሃቶች መሪ ሲያገኙ ወደ ገደል ቁልቁል ከማብረር ይድናሉ። ፍሬን ይይዛሉ! ቆም ብለው ያስባሉ…
“ውድ የኢትዮጵያ ህዝብ ሆይ! በነጻነት ስም፣ ለችግር፣ ለመከራ፣ ለስደት፣ ለእስራት፣ ለግድያ፣ ለግፍ፣ ለዝርፊያ፣ ለአድልኦ፣ ለስርአት አልባነት፣ ተዘርዝሮ ለማያልቅ በደልና ግፍ ዳርገንሃል። ለሁላችንም የሚሆን አዲስ ምዕራፍ መክፈት ግድ ሆኖብናል። ይቅርታህን እንለምናለን!” የሚል ደፋር መሪ ያሳፈልጋቸዋል። የኢትዮጵያ ህዝብ ሁል ግዜም ይቅር ባይ ነው።
መንደር መሃል እንደነጋበት ጅብ መሄጃ ከማጣቱ በፊት ህወሃት ደፋር መሪ እንዲኖረው እመኝለታለሁ። የእነ መለስን ስህተት ከሚደግም መሪ ይልቅ እወነተኛ ራእይ ያለው ቆራጥ መሪ ያስፈልገዋል። አርቆ አሳቢ፣ ከአድልኦ እና ጠባብነት የጸዳ ከዛሬ ከንቱነት ይልቅ ለመጪው ትውልድ ሁሉ የሚያስብ መሪ..

የወያኔ አገልጋዮች ፕ/ መስፍን ላይ ጥቃት አደረሱ!!! የት ሂዱ ነው?

የት ሂዱ ነው?

ዓለም ሁሉ ጠላን፤ በየትም አገር እየሄድን ‹‹የሙጢኝ!›› ከራሳችን መሬት በጉልበት እየተነቀልን፣ ከራሳችን ቤት እየተባረርን፤ ከተወለድንበትና ከአደግንበት አካባቢ እየተፈናቀልን፣ ጭራውን ቆልምሞ እንደሚሮጥ ባለቤቱ እንዳባረረው ውሻ በአገኘነው አቅጣጫ እየሮጥን፣ እጃችንን እያርገበገብን ‹‹የሙጢኝ!›› እንላላን፤ የፈራነውን ሞት በየመንገዱ እናገኘዋለን፤ ሞትን ሸሽተን ሞትን ያጋጥመናል፤ የሞቱ ልዩነት አይታየንም፤ በየመንገዱ የሚያጋጥመው ሞት የውርደት ሞት ነው፤ የብቸኛነት ሞት ነው፤ ዘመድ-ወዳጅ ለቀብር የማይገኝበት ሞት ነው፤ ሠለስት፣ አርባ፣ ሙታመት የማይወጣበት ሞት ነው፤ ባዕድ ምስጥ ያላሳደገውን አካል የሚበላበት ነው፤ የሞት ሞት ነው፡፡
ኢትዮጵያውያንን ሁሉ ከአገር አስወጥቶ ባዶ መሬት ብቻ ይፈልግ ይመስል የወያኔ ሎሌዎች በማስፈራራት ሁሉም አገሩን እየተወላቸው እንዲሄድ ያቀዱ ይመስላል፤ ጥንት ኢሰመጉ በምሠራበት ጊዜ በየጊዜው በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ መንገድ ሰዎችን በማስፈራራት ሰላማቸውን ለመረበሽ ወደስደት ወይም ወደወንጀል ተግባር የሚመሩ የወያኔ አባለች ነበሩ፤ አሁን እንደገና ብቅ ማለት ጀምረዋል፤ ሕጋዊ ሥርዓት እየላላ ጉልበተኞች በግላቸው ለዘረፋና ለቅሚያ እየተሰማሩ ይመስላል፡፡
ስለራሴ ላውራ፤ ከእኔ የሚፈልጉት ምን እንደሆነ እርግጠኛ አይደለሁም፤ የሚፈልጉት የምኖርበትን አፓርትመንት እንደሆነም አላውቅም፤ በእኔ ቤት ያለ ሀብት የሚባል ለወያኔ አገልጋዮች የሚጠቅም ሁለት የገብረ ክርስቶስ ስዕሎች ብቻ ናቸው፤ (በዚህ አጋጣሚ እነዚህን ስዕሎች ለመግዛት የሚፈልግ ያነጋግረኝ)፤ ከዚህ ሌላ ለወያኔ ዋጋ የሌላቸው መጻሕፍት ናቸው፤ ስለዚህም አሁን በእኔ ላይ የተሰነዘረው ጥቃት እኔን ወደስደት ለመግፋት የሚደረግ ሙከራ ይሆናል፤ በ1992 ግድም ተሞክሮ ነበር፤ አልሠራም፤ ዛሬ ይበልጥ አይሠራም፤ ለማናቸውም ምክንያቱን በትክክል ለማወቅ ባልችልም በእኔ ላይ ዘመቻ መጀመሩን አንድ በቅርብ ከማውቀው ወያኔ በትክክል ተረድቻለሁ፤ ይህንን ዘመቻ በመምራት ላይ ያለውንም ሰው ማንነት ተነግሮኛል፡፡
ይህ አገር የአንድ ጉልበተኛ ቡድን ነው ብዬ አልቀበልም፤ የአባቶቼና የእናቶቼ፣ የኤቶቼና የቅድማያቶቼ አጥንትና ደም የገነባው አገር ነው፤ ማንም ለስደት አይዳርገኝም፤ ማንም አስፈራርቶ ኢትዮጵያዊነት መብቴን መግፈፍ አይችልም፤ አልፈቅድለትም፤ በግልጽ በማያጠራጥር ቋንቋ ኑሮዬም፣ ሕይወቴም፣ ሞቴም እዚሁ ነው፤ ከኢትዮጵያ አፈር የሚለየኝ የለም፡፡
እኔን ለማጥቃት ላሰፈሰፉት ወያኔዎችና ሎሌዎቻቸው አንድ እውነት ልንገራቸው፤– በፈለጉትና በተመቻቸው መንገድ በእኔ ላይ በጉልበታቸው ግፍ ቢፈጽሙ ነገ በነሱ ላይ የባሰ ግፍ እንደሚደርስባቸው ይወቁት፤ ሁልጊዜም ከሕግ የወጣ ጉልበተኛነት ጉልበተኛነትን ያነግሣል፤ በመግደል ድል ይገኛል ብለው የሚያምኑ ወያኔዎች ትንሽ ቆም ብለው ያስቡ፤ በመሞትም ድል ይገኛል፤ በመሞትም ማሸነፍ ይቻላል፡፡
በእኔ ላይ የዘመተው ወያኔ ወይም ሎሌ ማናቸውም ሥራ ውጤት እንዳለው ማወቅ አለበት፤ አንድ ነገር አድርጎ ምንም ዓይነት ውጤት አያስከትልም ብሎ ማሰብ ድንቁርና ነው፤ ይህ የሳይንስ ሕግ ነው፤ For every action there is a reaction ይላል!

አሸባብ ተጨማሪ ጥቃት በናይሮቢ እንደሚያደርስ ዛተ





የሶማሊያዉ ፅንፈኛ እስላማዊ ቡድን አሸባብ ኬንያ ላይ ተጨማሪ ጥቃት ሊያደርስ እንደሚችል ዛሬ አስጠነቀቀ። የቡድኑ ቃል አቀባይ ሼኽ አሊ መሐሙድ ራጂ ለፅንፈኛዉ ቡድን ያደላል ለተባለዉ ራዲዮ አንዳሉት በሰጡት ቃል፤ የኬንያ ወታደሮች ሶማሊያ ዉስጥ እስካሉ ድረስ ለኬንያ ዜጎች ደህንነቱ የሚያስተማምን ስፍራ አይኖርም ሲሉ መዛታቸዉን የጀርመን የዜና ወኪል DPA ዘግቧል። የቡድኑ ታጣቂዎች ትናንት በኬንያ ዩኒቨርሲቲ ዉስጥ 16 ሰዓት በፈጀዉ የጥቃት ርምጃቸዉ 147 ሰዎችን ገድለዋል። የአሸባብ ቃል አቀባይ ሌሎች ተጨማሪ አስከፊ ጥቃቶች እንደሚቀጥሉ ነዉ ያመለከቱት። አያይዘዉም ከናይሮቢ በስተምስራቅ 350 ኪሌ ሜትር ርቀት ላይ ጋሪሳ ከተማ በሚገኘዉ የሞይ ዩኒቨርሲቲ ታጣቂዎቹ የገደሉት ክርስቲያኖቹን መርጠዉ ነዉ ብለዋል። እማኞች እንደገለፁትም ስለቁርዓን ተጠይቀዉ መመለስ ያልቻሉ በጥይት ተገድለዋል። ጥቂት ተማሪዎች በበኩላቸዉ አንዳንድ ጥቅሶችን በመናገራቸዉ ነፍሳቸዉ መትረፉን መግለፃቸዉን ዘገባዉ አመልክቷል። የከተማዋ ኗሪዎች ስጋት እንደገባቸዉ ነዉ የተገለፀዉ። ከኗሪዎቹ አንዱ ይህን ይገልፃሉ፤

«አብዛኞቻችን ፍርሃት ገብቶናል፤ የፀጥታ ጥበቃ ሁኔታዉ ተጠናክሮ በቦታዉ የመኖሩን አስተማማኝነት ካላመንበት በቀር፤ መንግሥት ምን ሊያደርግ እንደሚችል አናዉቅም።»

የኬንያ ቀይ መስቀል በጥቃቱ ለተጎዱ 79 ሰዎች የደም እርዳታ ጠይቋል። የኬንያ መንግሥት አራት ታጣቂዎችን መገደላቸዉን ገልጿል። በጥቃቱ አቀነባባሪነት የተጠረጠረዉን በጋሪሳ የቁርዓን መምህር የነበረዉን ሞሀመድ ዱልያዳይን ለጠቆመም 20 ሚሊዮን የኬንያ ሽልንግ ማለትም 212 ሺ ዶላር እንደሚሰጥም አስታዉቋል

የሀገራት የጦር ጡንቻ አቅም ሪፖርት ይፋ ሆነ



ግብጽ 13 ተኛ ስትባል ኢትዮጵያ 46 ተኛ ላይ ተቀምጣለች የፈረንጆቹ 2015 የአለም ሀገራት የጦርና ወታደራዊ አቅም በግሎባል ፋየር ፓወር ተቋም አማካኝነት ማክሰኞ እለት ይፋ ተደርጓል. ተቋሙ በዘንድሮው ሪፖርቱ ከ 50 ባላነሱ የመመዘኛ መስፈርቶች የመዘናቸውን የአለም 106 ሀገራት የወታደራዊ ጡንቻ አቅም በደረጃ ማስቀመጡን አስታውቋል.
የሀገራት የወታደር ቁጥር, ለጦር ሰራዊታቸው የሚመድቡት አጠቃላይ በጀት, የጦር መሳሪያዎቻቸው ብዛት, ጥራትና አይነት … ወዘተ የመሳሰሉ አተቃላይ የሚሊታሪ አቅም መመዘኛ መስፈርቶችን ተጠቅሙ ተቋሙ ሪፖርቱን ይፋ ማድረጉን ገልጿል. በዚህ የደረጃ ሰንጠረዥ ላይ ቁንጮ በመሆን የምትመራዋ ሀገር እንደተለመደው ልእለ ሀያሏ አሜሪካ ስትሆን ራሺያ, ቻይና, ህንድ, እንግሊዝ, ፈረንሳይ, ጀርመን, ቱርክ, ደቡብ ኮሪያና, ጃፓን ተከታዮቹን ዘጠኝ ደረጃዎች በመያዝ የአለም አስር ባለትልቅ የጦር አቅም አገሮች ተሰኝተዋል. አሜሪካ ይህን የቀዳሚነት ደረጃ ስትቀዳጅ 612 ቢሊዮን ዶላር አመታዊ የጦር ሰራዊት በጀት በመመደብ (ሰባት በመቶ መቀነሷ ቢነገርም) ቀዳሚ ስትሆን; ሁለተኛዋ ራሺያ የምትመድበው 88 ቢሊዮን ዶላር (መጨመሩ ይነገራል); ሶስተኛ ደረጃ ላይ ምትገኘው ቻይና ከምትመድበው 130 ቢሊዮን ዶላር (ይህም መጨመሩ ይነገራል) እንዲሁም ሌሎች ሀገራት ከሚመድቡት ወታደራዊ በጀት በእጅጉ የሚያስከነዳ መጠን ያለው ብር ሀገሪቱ ፈሰስ ታደርጋለች ተብሏል. ብቻዋን ከ 19 የማያንስ የጦር አውሮፕላን ተሸካሚ መርከብ ያላት አሜሪካ ቀሪው አለም በድምሩ ካለው 12 ጋር ሲነጻጸር በእጅጉ ይልቃል. ሀገሪቱ በዚህ ብቻም አይደለም 1.4 ሚሊዮን ቋሚ ወታደር 13 ሺ የጦር አውሮፕላን ስምንት ሺህ ታንክ 7506 ተተኳሽ ኒውክሌር እንዲሁም ከ 75 የማያንስ ባህር ሰርጓጅ መርከብ በመያዝ ጭምር ከአቻዎቿ ፍጹም ብልጫ ወስዳ ነው. ከአለም ጠንካራ ጦር ባለቤት ከሆኑ 35 ሀገራት ውስጥ በ 13 ተኛ ደረጃ ላይ የተቀመጠችው ግብጽ ከአፍሪካ ቀዳሚዋ ባለጡንቻ  ሀገር ናት ተብሏል. 4.4 ቢሊዮን ዶላር በጀት; 468 ሺህ ወታደር; 4700 ታንክ; 1100 የጦር አውሮፕላንና; አራት ባህር ሰርጓጅ መርከብ ያላትና በአባይ ወንዝ ዙሪያ ሁሌም ከኛ ጋር ፍጥጫ የማያጣት ግብጽ ከአለም አስራ ሶስተኛዋ ባለጠንካራ ጦር ተሰኝታለች. በዚህ የደረጃ ሰንጠረዥ ላይ ከአለም በ 46 ተኛ ደረጃ ላይ ምትገኘዋ እናት ኢትዮጵያችን 340 ሚሊዮን ዶላር ወታደራዊ በጀት; 2300 ታንክ; 81 የጦር አውሮፕላን; 182 ሺህ ወታደር ይዛ 27 ተኛ ላይ ካለችው አልጄሪያ; 32 ተኛ ላይ ከተቀመጠችው ደቡብ አፍሪካ; እንዲሁም 41 ኛ ላይ ከምትገኘው ናይጄሪያ ለጥቃ ከአፍሪካ የአራተኛ ደረጃነትን (ከአለም 46 ተኛ) ልትይዝ እንደቻለች ሪፖርቱ ይፋ አድርጓል. ይህን የደረጃ ሰንጠረዝ በሚመለከት ተቋሙ መገምገሚያ መስፈርቱ በአብዛኛው የጦር ሰራዊት ብዛትን ወይ የመሳሪያ ቁጥርን የተመረኮዘ ነው በሚል የተተቸ ሲሆን አንዳንዶች እንዳሉትም የጦር አቅም ዋነኛ መመዘኛው አይምሬውና እጅግ አውዳሚው መሳሪያ ኒውክሌር በመሆኑ እሱን የታጠቁ ሀገራት በሰንጠረዙ ሊቀድሙ ይገባል የሚል አስተያታቸውን ነው የሰጡት 

ኤርትራ በዓረብ ሊግ የቀረበላትን የጦርነት ትብብር ወድቅ አደረገች



በየመን እየተንቀሳቀሱ ያሉ አማፅያን በቅርቡ ዋና ከተማዋን ሰነዓን በመቆጣጠር ፕሬዝዳንቱን ለስደት መዳረጋቸውን ተከትሎ የአረብ ሀገራት በሳዑዲ የሚመራ ወታደራዊ ጥቃትን በአማፅያኑ ላይ እያደረሱ ነው። ኤርትራም በወታደራዊ ጥቃቱ ላይ ተሳትፎ እንድታደርግ በአረብ ሊግ ጥያቄ ቢቀርብላትም ፕሬዝዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ ግን ጥያቄውን ውድቅ አድርገውታል።
ዜናውን ያሰራጨው ገሲካ አፍሪካ ኦንላይን ፕሬዝዳንቱ የአረብ ሊግን ጥያቄ ለምን ውድቅ እንዳደረጉ የገለፀው ነገር የለም። በጥቃቱ ላይ ሰፊ ተሳትፎ ያላት ሳዑዲ አረብያ የተለያዩ ሀገራት በሎጀስቲክና በቀጥተኛ ወታደራዊ ጥቃት እንዲሳተፉ ጥያቄ እያቀረበች ሲሆን ሱዳን በበኩሏ ጥያቄውን በመቀበል እግረኛ ጦሯን ብሎም የውጊያ አውሮፕላንን የምታሳትፍ መሆኗን ገልፃለች።
ሱዳን ትሪብዩን ባሰራጨው ዘገባ ሱዳን ስድስት ሺህ የእግረኛ ጦርን ለማሳተፍ ቃል ገብታለች። የሳዑዲን ጥሪ በመቀበል በየመን አመፅያን ላይ ለሚደርሰው ወታደራዊ ጥቃት ትብብራቸውን የገለፁት ሀገራት ዮርዳኖስ፣ ግብፅ፣ ሞሮኮ፣ ፓኪስታንና ሱዳን ናቸው። አማፅያኑን በገንዘብና በሎጂስቲክ ትደግፋለች በሚል ኢራን ክስ እየቀረበባት ነው።
ኤርትራ በዓረብ ሊግ በኩል የቀረበላትን ጥሪ ውድቅ የማድረጓ ምክንያት ተደርጐ በፖለቲካ ተንታኞች እየተገለፀ ያለው ሀገሪቱ ከኢራን ጋር ያላትን የጠበቀ ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት ላለማሻከር ነው።

wanted officials