Which one you first choose? በቅድሚያ የሚፈልጉት

Saturday, April 4, 2015

አሸባብ ተጨማሪ ጥቃት በናይሮቢ እንደሚያደርስ ዛተ





የሶማሊያዉ ፅንፈኛ እስላማዊ ቡድን አሸባብ ኬንያ ላይ ተጨማሪ ጥቃት ሊያደርስ እንደሚችል ዛሬ አስጠነቀቀ። የቡድኑ ቃል አቀባይ ሼኽ አሊ መሐሙድ ራጂ ለፅንፈኛዉ ቡድን ያደላል ለተባለዉ ራዲዮ አንዳሉት በሰጡት ቃል፤ የኬንያ ወታደሮች ሶማሊያ ዉስጥ እስካሉ ድረስ ለኬንያ ዜጎች ደህንነቱ የሚያስተማምን ስፍራ አይኖርም ሲሉ መዛታቸዉን የጀርመን የዜና ወኪል DPA ዘግቧል። የቡድኑ ታጣቂዎች ትናንት በኬንያ ዩኒቨርሲቲ ዉስጥ 16 ሰዓት በፈጀዉ የጥቃት ርምጃቸዉ 147 ሰዎችን ገድለዋል። የአሸባብ ቃል አቀባይ ሌሎች ተጨማሪ አስከፊ ጥቃቶች እንደሚቀጥሉ ነዉ ያመለከቱት። አያይዘዉም ከናይሮቢ በስተምስራቅ 350 ኪሌ ሜትር ርቀት ላይ ጋሪሳ ከተማ በሚገኘዉ የሞይ ዩኒቨርሲቲ ታጣቂዎቹ የገደሉት ክርስቲያኖቹን መርጠዉ ነዉ ብለዋል። እማኞች እንደገለፁትም ስለቁርዓን ተጠይቀዉ መመለስ ያልቻሉ በጥይት ተገድለዋል። ጥቂት ተማሪዎች በበኩላቸዉ አንዳንድ ጥቅሶችን በመናገራቸዉ ነፍሳቸዉ መትረፉን መግለፃቸዉን ዘገባዉ አመልክቷል። የከተማዋ ኗሪዎች ስጋት እንደገባቸዉ ነዉ የተገለፀዉ። ከኗሪዎቹ አንዱ ይህን ይገልፃሉ፤

«አብዛኞቻችን ፍርሃት ገብቶናል፤ የፀጥታ ጥበቃ ሁኔታዉ ተጠናክሮ በቦታዉ የመኖሩን አስተማማኝነት ካላመንበት በቀር፤ መንግሥት ምን ሊያደርግ እንደሚችል አናዉቅም።»

የኬንያ ቀይ መስቀል በጥቃቱ ለተጎዱ 79 ሰዎች የደም እርዳታ ጠይቋል። የኬንያ መንግሥት አራት ታጣቂዎችን መገደላቸዉን ገልጿል። በጥቃቱ አቀነባባሪነት የተጠረጠረዉን በጋሪሳ የቁርዓን መምህር የነበረዉን ሞሀመድ ዱልያዳይን ለጠቆመም 20 ሚሊዮን የኬንያ ሽልንግ ማለትም 212 ሺ ዶላር እንደሚሰጥም አስታዉቋል

No comments:

Post a Comment

wanted officials