Which one you first choose? በቅድሚያ የሚፈልጉት

Saturday, April 25, 2015

የአውሮፓ ህብረት በኢትዮጵያ የሚካደውን ምርጫ አስመልከቶ የተለያዩ አስተያዮችን ሲቀበል ዋለ

የአውሮፓ ህብረት በኢትዮጵያ የሚካደውን ምርጫ አስመልከቶ የተለያዩ አስተያዮችን ሲቀበል ዋለ

ሚያዝያ ፲፭(አስራ አምስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ህብረቱ የተለያዩ የፖለቲካ እና ሲቪክ ማህበራት መሪዎችን በመጋበዝ በኢትዮጵያ ወቅታዊ ሁኔታ ላይ ከ4 ሰአት በላይ ውይይት አድርጓል።
የአውሮፓ ህብረት የእንግሊዝ ተወካይ፣ ወ/ሮ ጁሊ ዋርድ፣ በህብረቱ የፖርቱጋል ተወካይ ወ/ሮ አና ጎሜዝ፣ የስዊድኖቹ፣ ሶራያ ፖስትና ቦዲል ሲቢሎስ እንዲሁም የስፔን ተወካይ ሚ/ር ጆርዲ ሴባሲቲያ  እና ሌሎችም የህብረቱ ባለስልጣናት በውይይቱ ላይ ተገኝተዋል።
“ካርቶን ዲሞክራሲ፣ በኢትዮጵያ የሚታየውን አምባገነን አገዛዝና ምርጫ” በሚል ርዕስ የተካሄደው ውይይት በ3 ክፍሎች ተካሂዷል።
የኦጋዴን ነጻነት ግንባር፣ የኦሮሞ ነጻነት ግንባር፣ የአርበኞች ግንቦት7 ለአንድነትና ዲሞክራሲ ፣ የሲዳማ ነጻነት ንቅናቄ እንዲሁም የአኝዋክ ሰርቫይቫል ተወካዮች በኢህአዴግ የብሄር ፖለቲካ ምክንያት የደረሰውን ፖለቲካዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ችግሮች ዙሪያ አስተያየታቸውን አቅርበዋል።
 

No comments:

Post a Comment

wanted officials